YouVersion Logo
Search Icon

መዝ​ሙረ ዳዊት 61

61
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ ስለ ኤዶ​ታም የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1ነፍሴ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ት​ገዛ አይ​ደ​ለ​ች​ምን?
መድ​ኀ​ኒቴ ከእ​ርሱ ዘንድ ናትና።
2እርሱ አም​ላኬ መድ​ኀ​ኒ​ቴም ነውና፤
እርሱ ረዳቴ ነው ሁል​ጊ​ዜም አል​ታ​ወ​ክም።
3እስከ መቼ በሰው ላይ ትቆ​ማ​ላ​ችሁ?
እና​ንተ ሁላ​ችሁ እን​ዳ​ዘ​ነ​በለ ግድ​ግዳ
እንደ ፈረ​ሰም ቅጥር ትገ​ድ​ሉ​ታ​ላ​ችሁ።
4ነገር ግን ክብ​ሬን ይሽሩ ዘንድ መከሩ፥
በጥ​ሜም ሮጥሁ፤#ዕብ. “ሐሰ​ትን ይወ​ድ​ዳሉ” ይላል።
በአ​ፋ​ቸው ይባ​ር​ካሉ፥ በል​ባ​ቸ​ውም ይረ​ግ​ማሉ።
5ነገር ግን ነፍሴ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትገ​ዛ​ለች፥
ተስ​ፋዬ ከእ​ርሱ ዘንድ ናትና።
6እርሱ አም​ላኬ መድ​ኃ​ኒ​ቴም ነውና፤
እርሱ ረዳቴ ነውና፥ አል​ታ​ወ​ክም።
7መድ​ኃ​ኒቴ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤
ክብ​ሬም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፥
የረ​ድ​ኤቴ አም​ላክ፥ ተስ​ፋ​ዬም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።
8የአ​ሕ​ዛብ ማኅ​በር ሁላ​ችሁ፥ በእ​ርሱ ታመኑ፥
ልባ​ች​ሁ​ንም በፊቱ አፍ​ስሱ፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረዳ​ታ​ችን ነው።
9ነገር ግን የሰው ልጆች ሁሉ ከንቱ ናቸው፥
የሰው ልጆ​ችም ሐሰ​ተ​ኞች ናቸው፤
በሚ​ዛ​ንም ይበ​ድ​ላሉ፥
እነ​ር​ሱስ በፍ​ጹም ከንቱ ናቸው።
10ዐመ​ፃን ተስፋ አታ​ድ​ርጉ፥
ቅሚ​ያ​ንም አት​ተ​ማ​መ​ኑት፤
ባለ​ጠ​ግ​ነት ቢበዛ ልባ​ች​ሁን አታ​ኩሩ።
11እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንድ ጊዜ ተና​ገረ፥
እኔም ይህን ብቻ ሰማሁ፤
ይቅ​ርታ#ዕብ. “ኀይል” ይላል። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና፥
12አቤቱ፥ ኀይ​ልም#ዕብ. “ምሕ​ረት” ይላል። ያንተ ነው፤
አንተ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ እንደ ሥራው ትከ​ፍ​ለ​ዋ​ለ​ህና።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Videos for መዝ​ሙረ ዳዊት 61