መዝሙረ ዳዊት 61
61
ለመዘምራን አለቃ ስለ ኤዶታም የዳዊት መዝሙር።
1ነፍሴ ለእግዚአብሔር የምትገዛ አይደለችምን?
መድኀኒቴ ከእርሱ ዘንድ ናትና።
2እርሱ አምላኬ መድኀኒቴም ነውና፤
እርሱ ረዳቴ ነው ሁልጊዜም አልታወክም።
3እስከ መቼ በሰው ላይ ትቆማላችሁ?
እናንተ ሁላችሁ እንዳዘነበለ ግድግዳ
እንደ ፈረሰም ቅጥር ትገድሉታላችሁ።
4ነገር ግን ክብሬን ይሽሩ ዘንድ መከሩ፥
በጥሜም ሮጥሁ፤#ዕብ. “ሐሰትን ይወድዳሉ” ይላል።
በአፋቸው ይባርካሉ፥ በልባቸውም ይረግማሉ።
5ነገር ግን ነፍሴ፥ ለእግዚአብሔር ትገዛለች፥
ተስፋዬ ከእርሱ ዘንድ ናትና።
6እርሱ አምላኬ መድኃኒቴም ነውና፤
እርሱ ረዳቴ ነውና፥ አልታወክም።
7መድኃኒቴ በእግዚአብሔር ነው፤
ክብሬም በእግዚአብሔር ነው፥
የረድኤቴ አምላክ፥ ተስፋዬም እግዚአብሔር ነው።
8የአሕዛብ ማኅበር ሁላችሁ፥ በእርሱ ታመኑ፥
ልባችሁንም በፊቱ አፍስሱ፥
እግዚአብሔር ረዳታችን ነው።
9ነገር ግን የሰው ልጆች ሁሉ ከንቱ ናቸው፥
የሰው ልጆችም ሐሰተኞች ናቸው፤
በሚዛንም ይበድላሉ፥
እነርሱስ በፍጹም ከንቱ ናቸው።
10ዐመፃን ተስፋ አታድርጉ፥
ቅሚያንም አትተማመኑት፤
ባለጠግነት ቢበዛ ልባችሁን አታኩሩ።
11እግዚአብሔር አንድ ጊዜ ተናገረ፥
እኔም ይህን ብቻ ሰማሁ፤
ይቅርታ#ዕብ. “ኀይል” ይላል። የእግዚአብሔር ነውና፥
12አቤቱ፥ ኀይልም#ዕብ. “ምሕረት” ይላል። ያንተ ነው፤
አንተ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ትከፍለዋለህና።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 61: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in