YouVersion Logo
Search Icon

መዝ​ሙረ ዳዊት 56

56
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ አታ​ጥፋ። ከሳ​ኦል ፊት ሸሽቶ በዋሻ በነ​በ​ረ​በት ጊዜ የዳ​ዊት ቅኔ።
1ይቅር በለኝ፥ አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፥
ነፍሴ አን​ተን ታም​ና​ለ​ችና፤
ኀጢ​አት እስ​ክ​ታ​ልፍ ድረስ
በክ​ን​ፎ​ችህ ጥላ እታ​መ​ና​ለሁ።
2ወደ ልዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥
ወደ​ሚ​ረ​ዳኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጮ​ኻ​ለሁ።
3ከሰ​ማይ ልኮ አዳ​ነኝ፥
ለረ​ገ​ጡ​ኝም ውር​ደ​ትን ሰጣ​ቸው፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር​ነ​ቱ​ንና ጽድ​ቁን ላከ።
4ነፍ​ሴን ከአ​ን​በ​ሶች መካ​ከል አዳ​ናት።
ደን​ግ​ጬም ተኛሁ፤
የሰው ልጆች ጥር​ሳ​ቸው ጦርና ፍላጻ ነው፥
አን​ደ​በ​ታ​ቸ​ውም የተ​ሳለ ሾተል ነው።
5 # ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. በቅ​ርብ ነው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ማ​ያት ላይ ከፍ ከፍ አለ፥
ክብ​ሩም በም​ድር ሁሉ ላይ ነው።
6ለእ​ግ​ሮቼ ወጥ​መ​ድን አዘ​ጋጁ፥
ሰው​ነ​ቴ​ንም አጐ​በ​ጡ​አት፤
ጕድ​ጓ​ድን በፊቴ ቈፈሩ፥ በው​ስ​ጡም ወደቁ።
7ልቤ ጽኑዕ ነው፥ አቤቱ ልቤ ጽኑዕ ነው፥
አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ፥ እዘ​ም​ራ​ለ​ሁም።
8ክብሬ ይነሣ፥ በበ​ገ​ናና በመ​ሰ​ንቆ ይነሣ፤
እኔም ማልጄ እነ​ሣ​ለሁ።
9አቤቱ፥ በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፥
በወ​ገ​ኖ​ችም ዘንድ እዘ​ም​ር​ል​ሃ​ለሁ፤
10ምሕ​ረ​ትህ እስከ ሰማይ ድረስ ከፍ ብላ​ለ​ችና፥
ጽድ​ቅ​ህም እስከ ደመ​ናት ድረስ።
11እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ማ​ያት ላይ ከፍ ከፍ አለ፥
ክብ​ሩም በም​ድር ሁሉ ላይ ነው።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. በቅ​ርብ ነው።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Videos for መዝ​ሙረ ዳዊት 56