መዝሙረ ዳዊት 55
55
ለመዘምራን አለቃ ከቅዱሳን ስለ ራቁ ሕዝብ ፍልስጥኤማውያን በጌት በያዙት ጊዜ የዳዊት ቅኔ።
1አቤቱ፥ ሰው ረግጦኛልና ይቅር በለኝ፤
ሁልጊዜም ሰልፍ አስጨንቆኛል።
2ሁልጊዜ ቀኑን ሁሉ ጠላቶች ረገጡኝ፥
የሚዋጉኝ በዝተዋልና ፈራሁ።
3እኔ ግን አቤቱ በአንተ ታመንሁ።
4በእግዚአብሔር ቃሉን አከብራለሁ፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “በእግዚአብሔር ቃሉን አመሰግናለሁ” ይላል።
በእግዚአብሔር ታመንሁ፥ አልፈራም፤ ሰው ምን ያደርገኛል?
5ሁልጊዜ ቃሎችን ይጸየፉብኛል፤
በእኔ ላይም የሚመክሩት ሁሉ ለክፉ ነው።
6ይሸምቁብኛል፥ ይሸሸጉኝማል፥
እነርሱም ተረከዜን ይመለካከታሉ፥
ሁልጊዜም ነፍሴን ይሸምቁባታል።
7በምንም ምን አታድናቸውም፤
አሕዛብን በመዓትህ ትጥላቸዋለህ።
8አምላኬ ሆይ፥ ሕይወቴን እነግርሃለሁ፤
እንባዬንም እንደ ትእዛዝህ በፊትህ አኖርሁ።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “አኖርህ” ይላል።
9በጠራሁህ ጊዜ ጠላቶች ወደ ኋላቸው ይመለሱ፤
አንተ አምላኬ እንደ ሆንህ እነሆ፥ ዐወቅሁ።
10በእግዚአብሔር ቃሌን አከብራለሁ፤
የተናገርሁትም በእግዚአብሔር ዘንድ ይከብራል።#ከዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. ይለያል።
11በእግዚአብሔር ታመንሁ፥ አልፈራም፥ ሰው ምን ያደርገኛል?
12አቤቱ፥ የምስጋና ስእለት የምሰጥህ ከእኔ ዘንድ ነው፤
13ነፍሴን ከሞት፥ ዐይኖቼን ከዕንባ፥ እግሮቼንም ከድጥ አድነሃልና፥
በሕያዋን ሀገር#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ብርሃን” ይላል። እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው ዘንድ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 55: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in