YouVersion Logo
Search Icon

መዝ​ሙረ ዳዊት 41

41
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ የቆሬ ልጆች ትም​ህ​ርት።
1ዋሊያ ወደ ውኃ ምን​ጮች እን​ደ​ሚ​ና​ፍቅ፥
እን​ዲሁ ነፍሴ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትና​ፍ​ቃ​ለች።
2ነፍሴ ወደ ሕያው አም​ላኬ ተጠ​ማች፤
መቼ እደ​ር​ሳ​ለሁ? የአ​ም​ላ​ኬ​ንስ ፊት መቼ አያ​ለሁ?
3ዘወ​ትር፥ “አም​ላ​ክህ ወዴት ነው?” ይሉ​ኛ​ልና
እን​ባዬ በቀ​ንና በሌ​ሊት ምግብ ሆነኝ።
4ይህን ሳስብ ነፍሴ በእኔ ውስጥ ፈሰ​ሰች፥
ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወደ ምስ​ጋና መኖ​ሪያ ስፍራ እገ​ባ​ለ​ሁና፤
በዓ​ልን የሚ​ያ​ደ​ርጉ ሰዎች በም​ስ​ጋ​ናና በደ​ስታ ቃል ሲያ​መ​ሰ​ግኑ ተሰሙ።
5ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝ​ኛ​ለሽ? ለም​ንስ ታው​ኪ​ኛ​ለሽ?
የፊ​ቴን መድ​ኀ​ኒት አም​ላ​ኬን አመ​ሰ​ግ​ነው ዘንድ
በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመኚ።
6ነፍሴ በእኔ ውስጥ ታወ​ከች፤
ስለ​ዚህ አቤቱ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ምድር፥
በአ​ር​ሞ​ን​ኤ​ምም በታ​ናሹ ተራራ አስ​ብ​ሃ​ለሁ።
7በፍ​ዋ​ፍ​ዋ​ቴህ ድምፅ ቀላይ ቀላ​ይን ትጠ​ራ​ዋ​ለች፤
ማዕ​በ​ል​ህና ሞገ​ድህ ሁሉ በላዬ አለፈ።
8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀን ይቅ​ር​ታ​ውን ያዝ​ዛል፥
በሌ​ሊ​ትም እር​ሱን ይና​ገ​ራል፤#ዕብ. “በሌ​ሊ​ትም ዝማ​ሬው በእኔ ዘንድ ይሆ​ናል” ይላል።
ከእኔ ዘንድ የሕ​ይ​ወቴ ብፅ​ዐት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።
9እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ሁት፥ “አንተ አም​ላኬ#ዕብ. “ዐለቴ” ይላል። ነህ፤ ለምን ረሳ​ኸኝ?
ጠላ​ቶቼ ሲያ​ስ​ጨ​ን​ቁኝ ለምን ተው​ኸኝ? ለም​ንስ አዝኜ እመ​ለ​ሳ​ለሁ?”
ጠላ​ቶቼ ሁሉ አጥ​ን​ቶ​ቼን እየ​ቀ​ለ​ጣ​ጠሙ ሰደ​ቡኝ።
10ሁል​ጊዜ፥ “አም​ላ​ክህ ወዴት ነው?” ይሉ​ኛ​ልና።
11ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝ​ኛ​ለሽ? ለም​ንስ ታው​ኪ​ኛ​ለሽ?
የፊ​ቴን መድ​ኀ​ኒት አም​ላ​ኬን አመ​ሰ​ግ​ነው ዘንድ
በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመኚ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Videos for መዝ​ሙረ ዳዊት 41