YouVersion Logo
Search Icon

መዝ​ሙረ ዳዊት 40

40
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1ለድ​ሃና ለም​ስ​ኪን የሚ​ያ​ስብ ብፁዕ ነው፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከክፉ ቀን ያድ​ነ​ዋል።
2እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጠ​ብ​ቀ​ዋል፥ ሕያ​ውም ያደ​ር​ገ​ዋል፥
በም​ድር ላይም ያስ​መ​ሰ​ግ​ነ​ዋል፥
በጠ​ላ​ቶቹ እጅ አሳ​ልፎ አይ​ሰ​ጠ​ውም።
3እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በደ​ዌው አልጋ ሳለ ይረ​ዳ​ዋል፤
መኝ​ታ​ው​ንም ሁሉ ከበ​ሽ​ታው የተ​ነሣ ይለ​ው​ጥ​ለ​ታል።
4እኔስ፥ “አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፤
አን​ተን በድ​ያ​ለ​ሁና ለነ​ፍሴ አስ​ተ​ስ​ር​ይ​ላት” አልሁ።
5ጠላ​ቶ​ቼም በላዬ ክፋ​ትን ይና​ገ​ራሉ፦
“መቼ ይሞ​ታል? ስሙስ መቼ ይሻ​ራል?” ይላሉ።
6ከን​ቱን የሚ​ና​ገር ይግ​ባና ይይ፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “እኔን ለማ​የት ቢገባ ከን​ቱን ይና​ገ​ራል” ይላል።
ልቡ በላዩ ላይ ኀጢ​አ​ትን ሰበ​ሰበ፤
ወደ ሜዳ ይወ​ጣል ይና​ገ​ራ​ልም፥ በእ​ኔም ላይ ይተ​ባ​በ​ራል።
7ጠላ​ቶ​ቼም ሁሉ ይጠ​ቃ​ቀ​ሱ​ብ​ኛል፥
በእኔ ላይም ክፋ​ትን ይመ​ክ​ራሉ።
8የበ​ደ​ልን ነገር በእኔ አወጡ።#በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ይለ​ያል።
የተኛ ሰው ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አይ​ነ​ቃ​ምን?
9ደግሞ የሰ​ላሜ ሰው የታ​መ​ን​ሁ​በት፥
እን​ጀ​ራ​ዬን የበላ በእኔ ላይ ተረ​ከ​ዙን አነሣ።
10አንተ ግን አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፥
እመ​ል​ስ​ላ​ቸ​ውም ዘንድ አስ​ነ​ሣኝ።
11ስለ​ዚህ እንደ ወደ​ድ​ኸኝ ዐወ​ቅሁ።
ጠላ​ቶቼ በእኔ ደስ አላ​ላ​ቸ​ውም።
12እኔን ግን ስለ የዋ​ህ​ነቴ ተቀ​በ​ል​ኸኝ፥
በፊ​ት​ህም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጸ​ና​ኸኝ።
13የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።
ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለም
ይሁን፥ ይሁን።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Videos for መዝ​ሙረ ዳዊት 40