መዝሙረ ዳዊት 39
39
ለመዘምራን አለቃ የዳዊት መዝሙር።
1እግዚአብሔርን በትዕግሥት ደጅ ጠናሁት፥
እርሱም ተመልሶ ሰማኝ፥ የልመናዬንም ቃል ሰማኝ።
2ከጥፋት ጕድጓድ ከረግረግ ጭቃም አወጣኝ፥
እግሮቼንም በዓለት ላይ አቆማቸው፥
አረማመዴንም አጸና።
3አዲስ ምስጋናን በአፌ ጨመረ፥ ይህም የአምላካችን ምስጋናው ነው፤
ብዙዎች አይተው ይፍሩ፥
በእግዚአብሔርም ይታመኑ።
4መታመኛው የእግዚአብሔር ስም የሆነ፥
ወደ ከንቱ ነገር፥ ወደ ቍጣና ወደ ሐሰትም፥
ያልተመለከተ ሰው ብፁዕ ነው።
5አቤቱ አምላኬ፥ ብዙ ተአምራትህን አደረግህ፥
አሳብህንም ምንም የሚመስለው የለም፤
አወራሁ፥ ተናገርሁ፥ ከቍጥርም በዛ።
6መሥዋዕትንና ቍርባንን አልወደድሁም፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “አልወደድህም” ይላል።
ሥጋህን አንጻልኝ፤#ዕብ. “ጆሮህን ክፈትልኝ” ይላል።
የሚቃጠለውንና ስለ ኀጢአት የሚቀርበውን መሥዋዕት አልወደድሁም።#ዕብ. “አልወደድህም” ይላል።
7በዚያን ጊዜ አልሁ፥ “እነሆ፥ መጣሁ፤
ስለ እኔ በመጽሐፍ ራስ ተጽፎአል፤
8አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ መከርሁ፥#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ወደድሁ” ይላል።
ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው።”
9በታላቅ ጉባኤ ጽድቅህን አወራሁ፤
እነሆ፥ ከንፈሮችን አልከለክልም፤
አቤቱ፥ አንተ ጽድቄን ታውቃለህ።
10ቅንነትህን#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “እውነትህን” ይላል። በልቤ ውስጥ አልሰወርሁም፥
ማዳንህንም ተናገርሁ፤ ይቅርታህንና ምሕረትህን ከታላቅ ጉባኤ አልሰወርሁም።
11አቤቱ አንተ ይቅርታህን ከእኔ አታርቅ፤
ቸርነትህና እውነትህ ዘወትር ያግኙኝ።
12ቍጥር የሌላት ክፋት አግኝታኛለችና፤
ኀጢአቶቼ ተገናኙኝ፥ ማየትም ተስኖኛል፤
ከራሴ ጠጕር ይልቅ በዙ፥ ልቤም ተወኝ።
13አቤቱ፥ ታድነኝ ዘንድ ፍቀድ፤
አቤቱ፥ እኔን ለመርዳት ተመልከት።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ፍጠን” ይላል።
14ነፍሴን ለማጥፋት የሚወድዱ ይፈሩ፥
በአንድነትም ይጐስቍሉ፤
በእኔ ላይ ክፋትን ለማድረግ የሚወድዱ
ወደ ኋላቸው ይመለሱ፥ ይፈሩም።#ዕብ. “ይጐስቍሉም” ይላል።
15እሰይ፥ እሰይ የሚሉኝ
እፍረታቸውን ወዲያውኑ ይከፈሉ።
16አቤቱ፥ የሚፈልጉህ ሁሉ
በአንተ ደስ ይበላቸው፥ ሐሤትንም ያድርጉ፤
ሁልጊዜ ማዳንህን የሚወዱ
ዘወትር፦ እግዚአብሔር ታላቅ ነው ይበሉ።
17እኔ ድሃና ምስኪን ነኝ፥
እግዚአብሔር ግን ያስብልኛል፤
አንተ ረዳቴና መድኀኒቴ ነህ፤
አምላኬ ሆይ፥ አትዘግይ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 39: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in