መዝሙረ ዳዊት 38
38
ለመዘምራን አለቃ ለኤዶታም የዳዊት መዝሙር።
1“በአንደበቴ እንዳልስት አፌን#ግሪክ ሰባ. ሊ. “መንገዴን” ይላል። እጠብቃለሁ፤
ኃጥኣን በፊቴ በተቃወሙኝ ጊዜ
በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ” አልሁ፤
2ዝም አልሁ ራሴንም አዋረድሁ፥
ለበጎ ነገርም ዝም አልሁ፥
ቍስሌም ታደሰብኝ።
3ልቤም በውስጤ ሞቀብኝ፤
ከመናገሬም የተነሣ እሳት ነደደ፥
በአንደበቴም ተናገርሁ፦
4“አቤቱ፥ ፍጻሜዬን አስታውቀኝ” አልሁ፥
የዘመኔ ቍጥሮች ምን ያህል ናቸው?
ዐውቅ ዘንድስ ለምን ወደ ኋላ እላለሁ?
5እነሆ፥ ዘመኖቼን አስረጀሃቸው፤
አካሌም በፊትህ እንደ ኢምንት ነው።
ነገር ግን የሰው ልጅ ሁሉ ከንቱ ነው።
6ሰው ሁሉ እንደ ጥላ ይመላለሳል፥
ነገር ግን በከንቱ ይታወካሉ።#ዕብራይስጥ በነጠላ ቁጥር።
ያከማቻሉ የሚሰበስቡለትንም አያውቁም።
7አሁንስ ተስፋዬ ማን ነው? እግዚአብሔር አይደለምን?
ትዕግሥቴም ከአንተ ዘንድ ነው።
8ከኀጢአቴ ሁሉ አዳንኸኝ፥#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “አድነኝ” ይላል።
ለሰነፎችም ስድብ አደረግኸኝ።
9ዝም አልሁ አፌንም አልከፈትሁም።
አንተ ፈጥረኸኛልና፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሠርተህልኛልና” ይላል።
10መቅሠፍትህን ከእኔ አርቅ፥
ከእጅህ ብርታት የተነሣ አልቄአለሁና።
11በተግሣጽህ ስለ ኀጢአቱ ሰውን ዘለፍኸው፥
ሰውነቱንም እንደ ሸረሪት አቀለጥኻት፤
ነገር ግን ሰዎች ሁሉ በከንቱ ይታወካሉ።#ዕብ. “ሰው ሁሉ ከንቱ ነው” ይላል።
12አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ፥ ልመናዬንም አድምጥ፥
ልቅሶዬንም አድምጥ፥ ቸልም አትበለኝ፤
እኔ በምድር ላይ መጻተኛ ነኝና፥
እንደ አባቶችም ሁሉ እንግዳ ነኝና።
13ወደማልመለስበት ሳልሄድ ዐርፍ ዘንድ ተወኝ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 38: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in