መዝሙረ ዳዊት 141
141
በዋሻ በነበረ ጊዜ የዳዊት ትምህርት።
1በቃሌ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፤
በቃሌ ወደ እግዚአብሔር ለመንሁ።
2ልመናዬን በፊቱ አፈስሳለሁ፤
መከራዬንም በፊቱ እናገራለሁ።
3ሰውነቴ በላዬ ላይ ባለቀች ጊዜ
አቤቱ፥ መንገዴን አንተ ታውቃለህ፤
በምሄድባት በዚያች መንገድ ወጥመድን ሰወሩብኝ።
4ወደ ቀኝም ተመልሼ አየሁ፥
የሚያውቀኝም አጣሁ፤
መሸሸጊያም የለኝም፥
ስለ ሰውነቴም የሚመራመር የለም።
5አቤቱ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፦
“አንተ ተስፋዬ ነህ፥
በሕያዋንም ምድር አንተ ዕድል ፋንታዬ ነህ” አልሁ።
6እጅግ ተዋርጃለሁና ወደ ልመናዬ ተመልከት፤
በርትተውብኛልና ከከበቡኝ አድነኝ።
7አቤቱ፥ ስምህን አመሰግን ዘንድ
ሰውነቴን ከእሥራት አውጣት፤
ዋጋዬን እስክትሰጠኝ ድረስ
ጻድቃን እኔን ይጠብቃሉ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 141: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in