መዝሙረ ዳዊት 114
114
ሃሌ ሉያ።
1እግዚአብሔር የልመናዬን ድምፅ ሰምቶአልና ወደድሁት።
2ጆሮውን ወደ እኔ አዘንብሎአልና
በዘመኔ ሁሉ እጠራዋለሁ።
3የሞት ጣር ያዘኝ፥
የሲኦልም ሕማም አገኘኝ፤ ጭንቀትና መከራ አገኘኝ።
4የእግዚአብሔርንም ስም ጠራሁ፦
አቤቱ፥ ነፍሴን አድናት።
5እግዚአብሔር መሓሪና ጻድቅ ነው።
አምላካችን ይቅር ባይ ነው።
6እግዚአብሔር ሕፃናትን#ዕብ. “የዋሃንን” ይላል። ይጠብቃል፤
ተቸገርሁ እርሱም አዳነኝ።
7ነፍሴ ሆይ፥ ወደ ዕረፍትሽ ተመለሺ፥
እግዚአብሔር ረዳትሽ ነውና፤
8ነፍሴን ከሞት፥ ዓይኔንም ከእንባ፥
እግሬንም ከድጥ አድኖአልና።
9በሕያዋን ሀገር እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው ዘንድ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 114: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in