YouVersion Logo
Search Icon

መዝ​ሙረ ዳዊት 112

112
ሃሌ ሉያ።
1የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪ​ያ​ዎች ሆይ፥ አመ​ስ​ግ​ኑት፥
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም አመ​ስ​ግኑ።
2ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙ ቡሩክ ይሁን።
3ከፀ​ሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግ​ቢ​ያው ድረስ
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙ ይመ​ስ​ገን።
4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ላይ ልዑል ነው፥
ክብ​ሩም ከሰ​ማ​ያት በላይ ነው።
5እንደ አም​ላ​ካ​ችን እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማን ነው?
በል​ዕ​ልና የሚ​ኖር።
6በሰ​ማ​ይና በም​ድር የተ​ዋ​ረ​ዱ​ትን የሚ​ያይ፤
7ድሃ​ውን ከም​ድር የሚ​ያ​ነሣ፥
ምስ​ኪ​ኑ​ንም ከመ​ሬት ከፍ ከፍ የሚ​ያ​ደ​ርግ፤
8ከአ​ለ​ቆች ጋር ከሕ​ዝ​ቡም አለ​ቆች ጋር ያኖ​ረው ዘንድ
9መካ​ኒ​ቱን በቤቱ የሚ​ያ​ኖ​ራት፥
ደስ የተ​ሰ​ኘ​ችም የል​ጆች እናት የሚ​ያ​ደ​ር​ጋት።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Video for መዝ​ሙረ ዳዊት 112