መዝሙረ ዳዊት 111
111
ሃሌ ሉያ።
1እግዚአብሔርን የሚፈራ፥
ትእዛዙንም እጅግ የሚወድድ ሰው ብፁዕ ነው።
2ዘሩ በምድር ላይ ኀያል ይሆናል፤
የጻድቃን ትውልዶች ይባረካሉ።
3ክብርና ባለጠግነት በቤቱ ነው፥
ጽድቁም ለዘለዓለም ይኖራል።
4ለቅኖች ብርሃን በጨለማ ወጣ፤
እግዚአብሔር#“እግዚአብሔር” የሚለው በግእዝ ብቻ። መሓሪና ይቅር ባይ ነው፤#“አምላካችንም” የሚለው በግእዝ ብቻ። አምላካችንም ጻድቅ ነው።
5ርኅሩኅ፥ ይቅር ባይና ቸር#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ደግ ሰው ይራራል ያበድራልም” ይላል። ሰው
ነገሩን በፍርድ ይፈጽማል።
6ለዘለዓለም አይታወክም፤
የጻድቅ መታሰቢያ ለዘለዓለም ይኖራል።
7ከክፉ ነገርም አይፈራም፤
በእግዚአብሔር ለመታመን ልቡ የጸና ነው።
8በጠላቶቹ ላይ እስኪያይ ድረስ
ልቡ ጽኑዕ ነው፥ ለዘለዓለምም አይታወክም።
9በተነ፥ ለችግረኞችም ሰጠ፤
ጽድቁ ለዘለዓለም ዓለም ይኖራል፤
ቀንዱም በክብር ከፍ ከፍ ይላል።
10ኀጢአተኛም አይቶ ይቈጣል፥
ጥርሱንም ያፋጫል፥ ይቀልጣልም፤
የኃጥኣንም ምኞት ትጠፋለች።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 111: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in