YouVersion Logo
Search Icon

መዝ​ሙረ ዳዊት 111

111
ሃሌ ሉያ።
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ፥
ትእ​ዛ​ዙ​ንም እጅግ የሚ​ወ​ድድ ሰው ብፁዕ ነው።
2ዘሩ በም​ድር ላይ ኀያል ይሆ​ናል፤
የጻ​ድ​ቃን ትው​ል​ዶች ይባ​ረ​ካሉ።
3ክብ​ርና ባለ​ጠ​ግ​ነት በቤቱ ነው፥
ጽድ​ቁም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል።
4ለቅ​ኖች ብር​ሃን በጨ​ለማ ወጣ፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር#“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” የሚ​ለው በግ​እዝ ብቻ። መሓ​ሪና ይቅር ባይ ነው፤#“አም​ላ​ካ​ች​ንም” የሚ​ለው በግ​እዝ ብቻ። አም​ላ​ካ​ች​ንም ጻድቅ ነው።
5ርኅ​ሩኅ፥ ይቅር ባይና ቸር#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ደግ ሰው ይራ​ራል ያበ​ድ​ራ​ልም” ይላል። ሰው
ነገ​ሩን በፍ​ርድ ይፈ​ጽ​ማል።
6ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ታ​ወ​ክም፤
የጻ​ድቅ መታ​ሰ​ቢያ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል።
7ከክፉ ነገ​ርም አይ​ፈ​ራም፤
በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመ​ታ​መን ልቡ የጸና ነው።
8በጠ​ላ​ቶቹ ላይ እስ​ኪ​ያይ ድረስ
ልቡ ጽኑዕ ነው፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም አይ​ታ​ወ​ክም።
9በተነ፥ ለች​ግ​ረ​ኞ​ችም ሰጠ፤
ጽድቁ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ዓለም ይኖ​ራል፤
ቀን​ዱም በክ​ብር ከፍ ከፍ ይላል።
10ኀጢ​አ​ተ​ኛም አይቶ ይቈ​ጣል፥
ጥር​ሱ​ንም ያፋ​ጫል፥ ይቀ​ል​ጣ​ልም፤
የኃ​ጥ​ኣ​ንም ምኞት ትጠ​ፋ​ለች።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in