YouVersion Logo
Search Icon

ኦሪት ዘኍ​ልቍ 26

26
ሁለ​ተ​ኛው የእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ቈጠራ
1እን​ዲ​ህም ሆነ፦ መቅ​ሠ​ፍቱ ከሆነ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴ​ንና ካህ​ኑን አል​ዓ​ዛ​ርን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦ 2“ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለ​ውን፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ወደ ሰልፍ የሚ​ወ​ጣ​ውን ሁሉ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት ቍጠሩ።” 3ሙሴና ካህኑ አል​ዓ​ዛ​ርም በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ በኢ​ያ​ሪኮ ፊት ለፊት በሞ​ዓብ ሜዳ ላይ እን​ዲህ ብለው ነገ​ሩ​አ​ቸው፦ 4“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ከሃያ ዓመት ጀምሮ፥ ከዚ​ያም በላይ ያለ​ውን ሕዝብ ቍጠሩ።” ከግ​ብፅ ምድር የወጡ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እነ​ዚህ ናቸው።
5የእ​ስ​ራ​ኤል በኵር ሮቤል፤ የሮ​ቤል ልጆች፤ ከሄ​ኖኅ የሄ​ኖ​ኃ​ው​ያን ወገን፤ ከፈ​ሉስ የፈ​ሉ​ሳ​ው​ያን ወገን። 6ከአ​ስ​ሮን የአ​ስ​ሮ​ና​ው​ያን ወገን፤ ከከ​ርሚ የከ​ር​ማ​ው​ያን ወገን። 7እነ​ዚህ የሮ​ቤ​ላ​ው​ያን ወገ​ኖች ናቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ቈ​ጠ​ሩት አርባ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበሩ። 8የፈ​ሉ​ስም ልጆች፤ ኤል​ያብ። 9የኤ​ል​ያ​ብም ልጆች፥ ናሙ​ኤል፥ ዳታን፥ አቤ​ሮን፤ እነ​ዚ​ህም ከማ​ኅ​በሩ የተ​መ​ረጡ ነበሩ፤ ከቆሬ ወገን ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ባመፁ ጊዜ ሙሴ​ንና አሮ​ንን ተጣሉ፤ 10ማኅ​በ​ሩም በሞቱ ጊዜ ምድ​ሪቱ አፍ​ዋን ከፍታ ከቆሬ ጋር ዋጠ​ቻ​ቸው፤ በዚ​ያም ጊዜ እሳ​ቲቱ ሁለት መቶ አም​ሳ​ውን ሰዎች አቃ​ጠ​ለ​ቻ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ለም​ል​ክት ሆኑ። 11የቆሬ ልጆች ግን አል​ሞ​ቱም።
12የስ​ም​ዖ​ንም ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፤ ከና​ሙ​ሄል የና​ሙ​ሄ​ላ​ው​ያን ወገን፥ ከኢ​ያ​ሚን የኢ​ያ​ሚ​ና​ው​ያን ልጆች ወገን፥ ከያ​ክን የያ​ክ​ና​ው​ያን ልጆች ወገን፥ 13ከዛራ የዛ​ራ​ው​ያን ልጆች ወገን፥ ከሳ​ው​ኡል የሳ​ው​ኡ​ላ​ው​ያን ወገን። 14እነ​ዚህ የስ​ም​ዖ​ና​ው​ያን ወገ​ኖች ናቸው፤ ቍጥ​ራ​ቸ​ውም ሃያ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ።
15የይ​ሁዳ ልጆች ኤርና አው​ናን፥ ሴሎ​ምና ፋሬስ ዛራም፤ ዔርና አው​ና​ንም በከ​ነ​ዓን ምድር ሞቱ። 16የይ​ሁ​ዳም ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፤ ከሴ​ሎም የሴ​ሎ​ማ​ው​ያን ወገን፥ ከፋ​ሬስ የፋ​ሬ​ሳ​ው​ያን ወገን፥ ከዛራ የዛ​ራ​ው​ያን ወገን። 17የፋ​ሬ​ስም ልጆች፤ ከኤ​ስ​ሮም የኤ​ስ​ሮ​ማ​ው​ያን ወገን፥ ከያ​ሙ​ሔል የያ​ሙ​ሔ​ላ​ው​ያን ወገን። 18እነ​ዚህ የይ​ሁዳ ወገ​ኖች ናቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ቈ​ጠ​ሩት ሰባ ስድ​ስት ሺህ አም​ስት መቶ ነበሩ።
19የይ​ሳ​ኮር ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፤ ከቶላ የቶ​ላ​ው​ያን ወገን፥ ከፉሓ የፉ​ሓ​ው​ያን ወገን፤ 20ከያ​ሱብ የያ​ሱ​ባ​ው​ያን ወገን፥ ከሥ​ምራ የሥ​ም​ራ​ው​ያን ወገን። 21እነ​ዚህ የይ​ሳ​ኮር ወገ​ኖች ናቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ቈ​ጠ​ሩት ስድሳ አራት ሺህ አራት#ዕብ. “ሦስት መቶ” ይላል። መቶ ነበሩ። 22የዛ​ብ​ሎን ወገ​ኖች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ ከሳ​ሬድ የሳ​ሬ​ዳ​ው​ያን ወገን፥ ከኤ​ሎኒ የኤ​ሎ​ኒ​ያ​ው​ያን ወገን፥ ከያ​ሕ​ል​ኤል የያ​ሕ​ል​ኤ​ላ​ው​ያን ወገን። 23እነ​ዚህ የዛ​ብ​ሎን ወገ​ኖች ናቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ቈ​ጠ​ሩት ስድሳ ሺህ አም​ስት መቶ ነበሩ።
24የጋድ ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፤ ከሳ​ፎን የሳ​ፎ​ና​ው​ያን ወገን፥ ከሐጊ የሐ​ጋ​ው​ያን ወገን፥ ከሱኒ የሱ​ኒ​ያ​ው​ያን ወገን፤ 25ከኤ​ዜን የኤ​ዜ​ና​ው​ያን ወገን፥ ከሳ​ድፍ የሳ​ዳ​ፋ​ው​ያን#ዕብ. “ከዔር የዔ​ራ​ው​ያን” ይላል። ወገን፤ 26ከአ​ሮ​ሐድ የአ​ሮ​ሐ​ዳ​ው​ያን ወገን፥ ከአ​ሩ​ሔል የአ​ሩ​ሔ​ላ​ው​ያን ወገን። 27እነ​ዚህ የጋድ ልጆች ወገ​ኖች ናቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ቈ​ጠ​ሩት አርባ አራት ሺህ#ዕብ. “አርባ ሺህ ...” ይላል። አም​ስት መቶ ነበሩ።
28የአ​ሴር ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፤ ከኢ​ያ​ምን የኢ​ያ​ም​ና​ው​ያን ወገን፥ ከኢ​ያሱ የኢ​ያ​ሱ​ያ​ው​ያን ወገን፥ ከበ​ርያ የበ​ር​ያ​ው​ያን ወገን። 29ከኮ​ቤር ልጆች፤ ከከ​ቤር የከ​ቤ​ራ​ው​ያን ወገን፥ ከሜ​ል​ክ​ያል የሜ​ል​ክ​ያ​ላ​ው​ያን ወገን። 30የአ​ሴ​ርም የሴት ልጁ ስም ሳራ ነበረ። 31እነ​ዚህ የአ​ሴር ልጆች ወገ​ኖች ናቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ቈ​ጠ​ሩት አርባ ሦስት ሺህ#ግሪ​ኩና ዕብ. “አምሳ ሦስት ሺህ ...” ይላል። አራት መቶ ነበሩ።
32የዮ​ሴፍ ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፤ ምና​ሴና ኤፍ​ሬም። 33የም​ናሴ ልጆች፤ ከማ​ኪር የማ​ኪ​ራ​ው​ያን ወገን፤ ማኪ​ርም ገለ​ዓ​ድን ወለደ፤ ከገ​ለ​ዓድ የገ​ለ​ዓ​ዳ​ው​ያን ወገን። 34የገ​ለ​ዓድ ልጆች እነ​ዚህ ናቸው፤ ከአ​ክ​ያ​ዝር የአ​ክ​ያ​ዝ​ራ​ው​ያን ወገን፥ ከኬ​ሌግ የኬ​ሌ​ጋ​ው​ያን ወገን፥ 35ከኢ​ሳ​ር​ያል የኢ​ሳ​ር​ያ​ላ​ው​ያን ወገን፥ ከሴ​ኬም የሴ​ኬ​ማ​ው​ያን ወገን፥ 36ከሲ​ማ​ኤር#ዕብ. “ሸሚዳ” ይላል። የሲ​ማ​ኤ​ራ​ው​ያን ወገን፥ ከኦ​ፌር የኦ​ፌ​ራ​ው​ያን ወገን። 37የኦ​ፌ​ርም ልጅ ሰለ​ጰ​ዓድ ሴቶች ልጆች እንጂ ወን​ዶች ልጆች አል​ነ​በ​ሩ​ትም፤ የሰ​ለ​ጰ​ዓ​ድም የሴ​ቶች ልጆቹ ስም መሐላ፥ ኑኃ፥ ሄግላ፥ ሚልካ፥ ቴርሳ ነበረ። 38እነ​ዚ​ህም የም​ናሴ ወገ​ኖች ናቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ቈ​ጠ​ሩት አምሳ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ።
39በየ​ወ​ገ​ና​ቸው የኤ​ፍ​ሬም ልጆች እነ​ዚህ ናቸው፤ ከሱ​ቱላ የሱ​ቱ​ላ​ው​ያን ወገን#ዕብ. “ከቤ​ኬር የቤ​ኬ​ራ​ው​ያን ወገን” የሚል ይጨ​ም​ራል። ከጣ​ናህ የጣ​ና​ሃ​ው​ያን ወገን። 40እነ​ዚህ የሱ​ቱላ ልጆች ናቸው፤ ከዔ​ዴን#ዕብ. “ከኤ​ራን” ይላል። የዔ​ዴ​ና​ው​ያን ወገን። 41እነ​ዚህ የኤ​ፍ​ሬም ልጆች ወገ​ኖች ናቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ቈ​ጠ​ሩት ሠላሳ ሁለት ሺህ አም​ስት መቶ ነበሩ። በየ​ወ​ገ​ና​ቸው የዮ​ሴፍ ልጆች እነ​ዚህ ናቸው።
42የብ​ን​ያም ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፤ ከበ​ዓሌ የበ​ዓ​ላ​ው​ያን ወገን፥ ከአ​ሲ​ቤር የአ​ሲ​ቤ​ራ​ው​ያን ወገን፥ ከአ​ኪ​ራን የአ​ኪ​ራ​ና​ው​ያን ወገን፥ 43ከሶ​ፋን የሶ​ፋ​ና​ው​ያን ወገን፥#ዕብ. “ከሑ​ፋም የሑ​ፋ​ማ​ው​ያን ወገን” የሚል ይጨ​ም​ራል። 44የበ​ዓ​ሌም ልጆች አዴ​ርና ኖሐ​ማን፤ ከአ​ዴር የአ​ዴ​ራ​ው​ያን ወገን፥ ከኖ​ሐ​ማን የኖ​ሐ​ማ​ና​ው​ያን ወገን። 45በየ​ወ​ገ​ና​ቸው የብ​ን​ያም ልጆች እነ​ዚህ ናቸው። ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ቈ​ጠ​ሩት አርባ አም​ስት ሺህ ስድ​ስት መቶ ነበሩ።
46በየ​ወ​ገ​ና​ቸው የዳን ልጆች እነ​ዚህ ናቸው፤ ከሰ​ምዒ፥ የሰ​ም​ዒ​ያ​ው​ያን ወገን፤ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው የዳን ወገ​ኖች እነ​ዚህ ናቸው። 47የሰ​ም​ዒ​ያ​ው​ያን ወገ​ኖች ሁሉ ቍጥ​ራ​ቸው ስድሳ አራት ሺህ#ግእዝ “ሰባ አም​ስት ሺህ” ይላል። አራት መቶ ነበሩ።
48የን​ፍ​ታ​ሌም ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፤ ከአ​ሴ​ሔል የአ​ሴ​ሔ​ላ​ው​ያን ወገን፥ ከጎ​ሄኒ የጎ​ሄ​ና​ው​ያን ወገን፥ 49ከየ​ሴር የየ​ሴ​ራ​ው​ያን ወገን፥ ከሴ​ሌም የሴ​ሌ​ማ​ው​ያን ወገን። 50በየ​ወ​ገ​ና​ቸው የን​ፍ​ታ​ሌም ወገ​ኖች እነ​ዚህ ናቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ቈ​ጠ​ሩት አርባ አም​ስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።
51ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የተ​ቈ​ጠ​ሩት እነ​ዚህ ናቸው፤ ስድ​ስት መቶ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበሩ።
52እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ 53“ለእ​ነ​ዚህ በየ​ስ​ማ​ቸው ቍጥር ምድ​ሪቱ ርስት ሆና ትከ​ፈ​ላ​ለች። 54ለብ​ዙ​ዎቹ ብዙ ርስ​ትን ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ለጥ​ቂ​ቶ​ችም ጥቂት ርስ​ትን ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ። ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው እንደ ቍጥ​ራ​ቸው መጠን ርስ​ታ​ቸ​ውን ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ። 55ነገር ግን ምድ​ሪቱ በየ​ስ​ማ​ቸው በዕጣ ትከ​ፋ​ፈ​ላ​ለች፤ እንደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው ነገድ ይወ​ር​ሳሉ። 56በብ​ዙ​ዎ​ችና በጥ​ቂ​ቶች መካ​ከል ርስ​ታ​ቸ​ውን በዕጣ ትከ​ፍ​ላ​ለህ።
57የሌዊ ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው የተ​ቈ​ጠ​ሩት እነ​ዚህ ናቸው፤ ከጌ​ድ​ሶን የጌ​ድ​ሶ​ና​ው​ያን ወገን፥ ከቀ​ዓት የቀ​ዓ​ታ​ው​ያን ወገን፥ ከሜ​ራሪ የሜ​ራ​ራ​ው​ያን ወገን። 58እነ​ዚህ የሌዊ ልጆች ወገ​ኖች ናቸው፤ የሎ​ቢኒ ወገን፥ የኬ​ብ​ሮን ወገን፥ የሞ​ሓሊ ወገን፥ የሐ​ሙሲ ወገን፥ 59የቆሬ ወገን፥ የቀ​ዓት ወገን። ቀዓ​ትም እን​በ​ረ​ምን ወለደ። በግ​ብፅ ሀገር እነ​ዚ​ህን ሌዋ​ው​ያ​ንን የወ​ለ​ደ​ቻ​ቸው የሌዊ ልጅ የእ​ን​በ​ረም ሚስት#ዕብ. “እር​ስዋ በግ​ብፅ ከሌዊ የተ​ወ​ለ​ደች የሌዊ ልጅ ነበ​ረች” ይላል። ስም ዮካ​ብድ ነበረ። ለእ​ን​በ​ረ​ምም አሮ​ን​ንና ሙሴን እኅ​ታ​ቸ​ው​ንም ማር​ያ​ምን ወለ​ደ​ች​ለት። 60ለአ​ሮ​ንም ናዳብ፥ አብ​ዩድ፥ አል​ዓ​ዛ​ርና ኢታ​ምር ተወ​ለ​ዱ​ለት። 61በሲና በረሃ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ከሌላ እሳት ባቀ​ረቡ ጊዜ ናዳ​ብና አብ​ዩድ ሞቱ። 62ከአ​ንድ ወርም ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያሉ ወን​ዶች ሁሉ ከእ​ነ​ርሱ የተ​ቈ​ጠሩ ሃያ ሦስት ሺህ ነበሩ። ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች መካ​ከል ርስት አል​ተ​ሰ​ጣ​ቸ​ው​ምና ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጋር አል​ተ​ቈ​ጠ​ሩም።
63በሞ​ዓብ ሜዳ ላይ በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ በኢ​ያ​ሪኮ ፊት ለፊት ሲቈ​ጥሩ፥ ሙሴና ካህኑ አል​ዓ​ዛር የቈ​ጠ​ሩ​አ​ቸው የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እነ​ዚህ ናቸው። 64ነገር ግን ሙሴና ካህኑ አሮን በሲና ምድረ በዳ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በቈ​ጠ​ሩ​አ​ቸው ጊዜ ከነ​በ​ሩት ከእ​ነ​ዚያ መካ​ከል አን​ድም ሰው አል​ነ​በ​ረም። 65እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እነ​ርሱ፥ “በእ​ው​ነት በም​ድረ በዳ ይሞ​ታሉ” ብሎ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና። ከዮ​ፎኒ ልጅ ከካ​ሌብ፥ ከነ​ዌም ልጅ ከኢ​ያሱ በቀር ከእ​ነ​ርሱ አንድ ሰው ስንኳ አል​ቀ​ረም። #ምዕ. 26 ከዕብ. ልዩ​ነት አለው ፤ ምዕ. 26 ከቍ. 15 እስከ 23 በዕብ. ከቍ. 19 እስከ 27 ፤ ምዕ. 26 ከቍ. 24 እስከ 27 በዕብ. ከቍ. 15 እስከ 18 ፤ ምዕ. 26 ከቍ. 28 እስከ 31 በዕብ. ከቍ. 44 እስከ 47 ፤ ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ግእዝ ከቍ. 32 እስከ 47 ዕብ. ከቍ. 28 እስከ 43።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Video for ኦሪት ዘኍ​ልቍ 26