YouVersion Logo
Search Icon

ኦሪት ዘሌ​ዋ​ው​ያን 5

5
የኀ​ጢ​አት ማስ​ተ​ስ​ረያ መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ቀ​ር​ብ​ባ​ቸው ምክ​ን​ያ​ቶች
1“አንድ ሰው ቢበ​ድል፥ የሚ​ያ​ም​ለ​ው​ንም ቃል ቢሰማ፥ ምስ​ክ​ርም ሆኖ አንድ ነገር አይቶ እንደ ሆነ፥ ወይም ዐውቆ እንደ ሆነ ያነን ባይ​ና​ገር በደ​ሉን ይሸ​ከ​ማል፤ 2ርኩስ ነገ​ርን፥ የሞ​ተ​ውን፥ አውሬ የነ​ከ​ሰ​ውን፥ ወይም የበ​ከተ፥ ወይም የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀስ የእ​ን​ስ​ሳን በድን የነካ፥ ከእ​ር​ሱም ያነሣ ሰው ቢኖር፤ 3ወይም ርኩ​ስ​ነ​ቱን ሳያ​ውቅ ርኩ​ስን ሰው ቢነካ፥ በማ​ና​ቸ​ውም ርኵ​ሰት ቢረ​ክስ፥ ነገሩ በታ​ወቀ ጊዜ በደል ይሆ​ን​በ​ታል። 4ሰው ሳያ​ስብ ክፉን ወይም መል​ካ​ምን ያደ​ርግ ዘንድ ሳያ​ስብ በከ​ን​ፈሩ ተና​ግሮ ቢምል፥ ሳያ​ስብ የማ​ለ​ውም ከዚህ ባንዱ ነገር ቢሆን፥ በታ​ወ​ቀው ጊዜ ከዚህ ነገር በአ​ንዱ በደ​ለኛ ይሆ​ናል። 5ከእ​ነ​ዚህ ነገ​ሮች በአ​ን​ዲቱ በደ​ለኛ ቢሆን፥ የሠ​ራ​ውን ኀጢ​አት ይና​ዘ​ዛል። 6እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ መበ​ደ​ሉና ስለ ሠራው ኀጢ​አት ከበ​ጎቹ ነውር የሌ​ለ​ባ​ትን እን​ስት በግ ወይም ከፍ​የ​ሎች እን​ስት ፍየል ያመ​ጣል፤ ካህ​ኑም ስለ ኀጢ​አቱ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይሰ​ረ​ይ​ለ​ታል።
7“ስለ ሠራው ኀጢ​አት የበግ መግዣ ገን​ዘብ በእጁ ባይ​ኖ​ረው ግን፥ ሁለት ዋኖ​ሶች ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች፥ አን​ዱን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ር​ባል። ወደ ካህ​ኑም ያመ​ጣ​ቸ​ዋል፤ 8ካህ​ኑም አስ​ቀ​ድሞ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት የሆ​ነ​ውን ያቀ​ር​ባል፤ ራሱ​ንም ከአ​ን​ገቱ ይቆ​ለ​ም​መ​ዋል፤ ነገር ግን አይ​ቈ​ር​ጠ​ውም። 9ከኀ​ጢ​አ​ቱም መሥ​ዋ​ዕት ደም በመ​ሠ​ዊ​ያው ግድ​ግዳ ላይ ይረ​ጨ​ዋል፤ የተ​ረ​ፈ​ው​ንም ደም ከመ​ሠ​ዊ​ያው በታች ያን​ጠ​ፈ​ጥ​ፋል፤ እርሱ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ነውና። 10እንደ ሥር​ዐ​ቱም ሁለ​ተ​ኛ​ውን ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ያዘ​ጋ​ጀ​ዋል። ካህ​ኑም ስለ ሠራው ኀጢ​አት ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይሰ​ረ​ይ​ለ​ታል።
11“ሁለት ዋኖ​ሶች ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች ለማ​ም​ጣት ገን​ዘብ በእጁ ባይ​ኖ​ረው፥ ስለ ሠራው ኀጢ​አት የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ዐሥ​ረኛ ክፍል መል​ካም የስ​ንዴ ዱቄት ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ነውና ዘይት አያ​ፈ​ስ​ስ​በ​ትም፤ ዕጣ​ንም አይ​ጨ​ም​ር​በ​ትም። 12ወደ ካህ​ኑም ያመ​ጣ​ዋል፤ ካህ​ኑም ስለ መታ​ሰ​ቢ​ያው ለእ​ርሱ እፍኝ ሙሉ ይዘ​ግ​ናል፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ሳት በተ​ቃ​ጠ​ለው ቍር​ባን ላይ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ይጨ​ም​ረ​ዋል፤ እር​ሱም የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ነው። 13ካህ​ኑም ከእ​ነ​ዚያ በአ​ን​ዳ​ቸው ስለ ሠራው ኀጢ​አት ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይቅር ይባ​ል​ለ​ታል። የተ​ረ​ፈ​ውም እንደ እህሉ ቍር​ባን ለካ​ህኑ ይሆ​ናል።”
ስለ በደል መሥ​ዋ​ዕት
14እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ረው፦ 15“ሰው ቢዘ​ነጋ፥ ሳያ​ው​ቅም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በተ​ቀ​ደ​ሰው በማ​ና​ቸ​ውም ነገር ኀጢ​አ​ትን ቢሠራ፥ ለበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከመ​ን​ጋዉ ነውር የሌ​ለ​በ​ትን እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን በብር ሰቅል የተ​ገ​መ​ተ​ውን አውራ በግ ለበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል። 16በተ​ቀ​ደሰ ነገር ላይ ስለ ሠራው ኀጢ​አት ዕዳ ይከ​ፍ​ላል፤ አም​ስ​ተ​ኛ​ው​ንም እጅ ይጨ​ም​ር​በ​ታል፤ ለካ​ህ​ኑም ይሰ​ጠ​ዋል። ካህ​ኑም በበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት አውራ በግ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይቅር ይባ​ል​ለ​ታል።
17“ሰው ባለ​ማ​ወቅ ኀጢ​አት ቢሠራ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ አት​ሥሩ ካላ​ቸው ትእ​ዛ​ዛት አን​ዲ​ቱን ቢተ​ላ​ለፍ፥ ቢታ​ወ​ቀው፥ ኀጢ​አት ስለ​ሆ​ነ​ች​በ​ትም ንስሓ ቢገባ፥#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ቢተ​ላ​ለፍ ባያ​ው​ቅም ያ ሰው በደ​ለኛ ነው ፤ ኀጢ​አ​ቱ​ንም ይሸ​ከ​ማል” ይላል። 18ነውር የሌ​ለ​በ​ትን በሰ​ቅል የተ​ገ​መ​ተ​ውን አውራ በግ ከመ​ን​ጋው ለበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ወደ ካህኑ ያመ​ጣ​ዋል፤ ካህ​ኑም ሳያ​ውቅ ስለ ሳተው ስሕ​ተት ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይቅር ይባ​ል​ለ​ታል። 19እርሱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ንስሓ ገብ​ቶ​አ​ልና።”#ምዕ. 5 ቍ. 19 በዕብ. እና በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. “እር​ሱም የበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ነው ፤ በእ​ው​ነት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በደ​ለኛ ሆኖ​አ​ልና” ይላል።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in