YouVersion Logo
Search Icon

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 20

20
ጌታ​ችን ስለ መነ​ሣቱ
1ከሳ​ም​ን​ቱም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያዉ ቀን ማር​ያም መግ​ደ​ላ​ዊት በማ​ለዳ ገና ጨለማ ሳለ ወደ መቃ​ብር መጣች፤ ድን​ጋ​ዩ​ንም ከመ​ቃ​ብሩ አፍ ተነ​ሥቶ አገ​ኘ​ችው። 2ፈጥ​ናም ወደ ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስና ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ይወ​ደው ወደ ነበ​ረው ወደ​ዚያ ወደ ሌላዉ ደቀ መዝ​ሙር መጥታ፥ “ጌታ​ዬን ከመ​ቃ​ብር ወስ​ደ​ው​ታል፤ ወዴ​ትም እንደ ወሰ​ዱት አላ​ው​ቅም” አለ​ቻ​ቸው። 3ጴጥ​ሮ​ስና ያ ሌላዉ ደቀ መዝ​ሙ​ርም ወጥ​ተው ወደ መቃ​ብሩ ሄዱ። 4ሁለ​ቱም በአ​ን​ድ​ነት ሲሮጡ ያ ሌላዉ ደቀ መዝ​ሙር ጴጥ​ሮ​ስን ቀድ​ሞት ወደ መቃ​ብሩ ደረሰ። 5ጐን​በስ ብሎም ሲመ​ለ​ከት በፍ​ታ​ዉን ተቀ​ምጦ አየ፤ ነገር ግን ወደ ውስጥ አል​ገ​ባም። 6ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም ተከ​ት​ሎት ደረ​ሰና ወደ መቃ​ብሩ ገባ፤ 7በፍ​ታ​ዉ​ንም በአ​ንድ ወገን ተቀ​ምጦ አየ፤ በራሱ ላይ የነ​በ​ረው መጠ​ም​ጠ​ሚ​ያም ሳይ​ቃ​ወስ ለብ​ቻው ተጠ​ቅ​ልሎ አየ፤ ከበ​ፍ​ታዉ ጋርም አል​ነ​በ​ረም። 8ከዚ​ህም በኋላ አስ​ቀ​ድሞ ወደ መቃ​ብሩ የደ​ረ​ሰው ሌላዉ ደቀ መዝ​ሙር ገባ፤ አይ​ቶም አመነ፤ 9ከሙ​ታን ተለ​ይቶ ይነሣ ዘንድ እንደ አለው በመ​ጻ​ሕ​ፍት የተ​ጻ​ፈ​ውን ገና አላ​ወ​ቁም ነበ​ርና። 10ከዚ​ህም በኋላ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ተመ​ል​ሰው ወደ ቤታ​ቸው ገቡ።
ለማ​ር​ያም መግ​ደ​ላ​ዊት እንደ ተገ​ለጠ
11ማር​ያም ግን ከመ​ቃ​ብሩ በስ​ተ​ውጭ እያ​ለ​ቀ​ሰች ቆማ ነበረ፤ እያ​ለ​ቀ​ሰ​ችም ወደ መቃ​ብሩ ጐን​በስ ብላ ተመ​ለ​ከ​ተች። 12ሁለት መላ​እ​ክ​ት​ንም ነጭ ልብስ ለብ​ሰው የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ሥጋ በነ​በ​ረ​በት ቦታ አንዱ በራ​ስጌ፥ አን​ዱም በግ​ርጌ ተቀ​ም​ጠው አየች። 13እነ​ዚያ መላ​እ​ክ​ትም፥ “አንቺ ሴት፥ ምን ያስ​ለ​ቅ​ስ​ሻል?” አሉ​አት፤ እር​ስ​ዋም፥ “ጌታ​ዬን ከመ​ቃ​ብር ውስጥ ወስ​ደ​ው​ታል፤ ወዴ​ትም እንደ ወሰ​ዱት አላ​ው​ቅም” አለ​ቻ​ቸው። 14ይህ​ንም ተና​ግራ ወደ ኋላዋ መለስ ስትል ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ቆሞ አየ​ችው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እንደ ሆነ አላ​ወ​ቀ​ችም። 15ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አንቺ ሴት፥ ምን ያስ​ለ​ቅ​ስ​ሻል? ማን​ንስ ትሺ​ያ​ለሽ?” አላት፤ እር​ስዋ ግን የአ​ት​ክ​ልት ቦታ ጠባቂ መስ​ሎ​አት፥ “ጌታዬ፥ አንተ ወስ​ደ​ኸው እንደ ሆነ ሄጄ ወደ እኔ እን​ዳ​መ​ጣ​ውና ሽቱ እን​ድ​ቀ​ባው#“ሽቱ እን​ድ​ቀ​ባው” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። ወዴት እንደ አኖ​ር​ኸው ንገ​ረኝ” አለ​ችው። 16ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ማር​ያም!” አላት፤ እር​ስ​ዋም መለስ ብላ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ቋንቋ፥ “ረቡኒ!” አለ​ችው፤ ትር​ጓ​ሜ​ዉም “መም​ህር” ማለት ነው። 17ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አት​ን​ኪኝ፤ ገና ወደ አባቴ አላ​ረ​ግ​ሁ​ምና፤ ነገር ግን ወደ ወን​ድ​ሞች ሂጂና፦ ወደ አባቴ፥ ወደ አባ​ታ​ችሁ ወደ አም​ላኬ፥ ወደ አም​ላ​ካ​ች​ሁም አር​ጋ​ለሁ አለ ብለሽ ንገ​ሪ​አ​ቸው” አላት። 18ማር​ያም መግ​ደ​ላ​ዊ​ትም ሄደች፤ ጌታን እንደ አየች፥ ይህ​ንም እን​ዳ​ላት ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ነገ​ረ​ቻ​ቸው።
ጌታ​ችን ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ እንደ ተገ​ለ​ጠ​ላ​ቸው
19ያም ከሳ​ም​ንቱ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን በመሸ ጊዜ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ አይ​ሁ​ድን ስለ ፈሩ ተሰ​ብ​ስ​በው የነ​በ​ሩ​በት ቤት ደጁ ተቈ​ልፎ ሳለ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ መጥቶ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ቆመና፥ “ሰላም ለእ​ና​ንተ ይሁን” አላ​ቸው። 20ይህ​ንም ብሎ እጆ​ቹ​ንና ጎኑን#በግ​እዙ “ወእ​ገ​ሪሁ” የሚል ይጨ​ም​ራል። አሳ​ያ​ቸው፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ጌታ​ች​ንን ባዩት ጊዜ ደስ አላ​ቸው። 21ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ዳግ​መኛ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሰላም ለእ​ና​ንተ ይሁን፤ አብ እኔን እንደ ላከኝ እን​ዲሁ እኔ እና​ን​ተን እል​ካ​ች​ኋ​ለሁ።” 22ይህ​ንም ብሎ እፍ አለ​ባ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “መን​ፈስ ቅዱ​ስን ተቀ​በሉ። 23#ማቴ. 16፥19፤ 18፥18። ኀጢ​ኣ​ታ​ቸ​ውን ይቅር ያላ​ች​ሁ​ላ​ቸው ይሰ​ረ​ይ​ላ​ቸ​ዋል፤ ይቅር ያላ​ላ​ች​ኋ​ቸው ግን አይ​ሰ​ረ​ይ​ላ​ቸ​ውም።”
ስለ ቶማስ
24ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በመጣ ጊዜ ዲዲ​ሞስ የሚ​ሉት ከዐ​ሥራ ሁለቱ#በአ​ን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ “ከዐ​ሥራ አንዱ ደቀ መዛ​ሙ​ርት” ይላል። ደቀ መዛ​ሙ​ርት አንዱ ቶማስ ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ጋር አል​ነ​በ​ረም። 25ሌሎች ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትም፥ “ጌታ​ች​ንን አየ​ነው” አሉት፤ እርሱ ግን፥ “የች​ን​ካ​ሩን ምል​ክት በእጁ ካላ​የሁ፥ ጣቴ​ንም ወደ ተቸ​ነ​ከ​ረ​በት ካል​ጨ​መ​ርሁ፥ እጄ​ንም ወደ ጎኑ ካላ​ገ​ባሁ አላ​ም​ንም” አላ​ቸው።
26ከስ​ም​ንት ቀን በኋ​ላም ዳግ​መኛ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ በው​ስጡ ሳሉ፥ ቶማ​ስም አብ​ሮ​አ​ቸው ሳለ በሩ እንደ ተዘጋ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ መጣ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ቆመና፥ “ሰላም ለእ​ና​ንተ ይሁን” አላ​ቸው። 27ከዚ​ህም በኋላ ቶማ​ስን፥ “ጣት​ህን ወዲህ አም​ጣና እጆ​ችን እይ፤ እጅ​ህ​ንም አም​ጣና ወደ ጎኔ አግባ፤ እመን እንጂ ተጠ​ራ​ጣሪ አት​ሁን” አለው። 28ቶማ​ስም፥ “ጌታዬ አም​ላ​ኬም” ብሎ መለሰ። 29ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ስለ አየ​ኸኝ አመ​ን​ህን? ብፁ​ዓ​ንስ ሳያዩ የሚ​ያ​ምኑ ናቸው” አለው።
30ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በዚህ መጽ​ሐፍ ያል​ተ​ጻፈ ብዙ ሌላ ተአ​ም​ራት በደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ፊት አደ​ረገ። 31ነገር ግን ይህ የተ​ጻፈ ኢየ​ሱስ እርሱ ክር​ስ​ቶስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ እንደ ሆነ እና​ንተ ታምኑ ዘንድ፥ አም​ና​ች​ሁም በስሙ የዘ​ለ​ዓ​ለም#“የዘ​ለ​ዓ​ለም” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። ሕይ​ወ​ትን ታገኙ ዘንድ ነው።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in