YouVersion Logo
Search Icon

ትን​ቢተ ሆሴዕ 7

7
1በሐ​ሰት አድ​ር​ገ​ዋ​ልና፥ ሌባም ገብ​ቶ​አ​ልና፥ በው​ጭም ወን​በ​ዴ​ዎች ቀም​ተ​ዋ​ልና እስ​ራ​ኤ​ልን እፈ​ውስ ዘንድ በወ​ደ​ድሁ ጊዜ የኤ​ፍ​ሬም ኀጢ​አ​ትና የሰ​ማ​ርያ ክፋት ተገ​ለጠ። 2ወን​ጀ​ላ​ቸ​ውን አንድ ያደ​ርጉ ዘንድ በል​ባ​ቸው እንደ አሰቡ ክፋ​ታ​ቸ​ውን ሁሉ ዐሰ​ብሁ፤#ዕብ. “እኔም ክፋ​ታ​ቸ​ውን ሁሉ እን​ዳ​ሰ​ብሁ በል​ባ​ቸው አያ​ስ​ቡም” ይላል። አሁ​ንም ክፋ​ታ​ቸው ከብ​ባ​ቸ​ዋ​ለች፤ በደ​ላ​ቸ​ውም በፊቴ አለች። 3ነገ​ሥ​ታቱ በክ​ፋ​ታ​ቸው፥ አለ​ቆ​ቹም በሐ​ሰ​ታ​ቸው ደስ ተሰኙ። 4ሁሉም አመ​ን​ዝ​ራ​ዎች ናቸው፤ ጋጋሪ እን​ደ​ሚ​ያ​ነ​ድ​ድ​በት እንደ ምድጃ ናቸው፤ ሁሉም እስ​ኪ​ቦካ ድረስ እሳ​ትን መቈ​ስ​ቈ​ስና እር​ሾን መለ​ወስ ይቈ​ያል። 5በን​ጉ​ሦ​ቻ​ችን ቀን አለ​ቆች ከወ​ይን ጠጅ ሙቀት የተ​ነሣ ታመሙ፤ እነ​ር​ሱም ከዋ​ዘ​ኞች ጋር እጆ​ቻ​ቸ​ውን ዘረጉ። 6እያ​ደቡ ልባ​ቸ​ውን እንደ ምድጃ አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ዋል፤ ጋጋ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ሌሊ​ቱን ሁሉ አን​ቀ​ላፋ፤ በጠ​ባም ጊዜ እንደ እሳት ነበ​ል​ባል ይነ​ድ​ዳል። 7ሁሉም እንደ ምድጃ ግለ​ዋል፤ ፈራ​ጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም በሉ፤ ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ወደቁ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም መካ​ከል የሚ​ጠ​ራኝ የለም።
8ኤፍ​ሬም ከሕ​ዝቡ ጋር ተደ​ባ​ለቀ፤ ኤፍ​ሬም እን​ዳ​ል​ተ​ገ​ላ​በጠ ቂጣ ነው።#ግእዝ “ኤፍ​ሬም ኅቡ​ኣ​ቲከ ገፍ​ት​ዐከ” ይላል። 9ጠላት ጕል​በ​ቱን በላው፤ እርሱ ግን አላ​ወ​ቀም፤ ሽበ​ትም ወጣ​በት፤ እር​ሱም ገና አላ​ስ​ተ​ዋ​ለም። 10የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ውር​ደ​ቱና ስድቡ#ዕብ. “ትዕ​ቢቱ” ይላል። በፊቱ ነው፤ ወደ አም​ላ​ካ​ቸው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን አል​ተ​መ​ለ​ሱም፤ በዚ​ህም ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ፈ​ለ​ጉ​ትም። 11ኤፍ​ሬ​ምም ልብ እን​ደ​ሌ​ላት እንደ ሰነፍ ርግብ ነው፤ ግብ​ፅን ጠሩ፤ ወደ አሦ​ርም ሄዱ። 12ሲሄ​ዱም አሽ​ክ​ላ​ዬን እዘ​ረ​ጋ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እንደ ሰማይ ወፎ​ችም አወ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ መከ​ራ​ቸ​ውን ሲሰሙ እገ​ሥ​ጻ​ቸ​ዋ​ለሁ። 13ከእኔ ፈቀቅ ብለ​ዋ​ልና ወዮ​ላ​ቸው! እኔ​ንም ስለ በደሉ ደን​ግ​ጠ​ዋል! እኔ ታደ​ግ​ኋ​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን በሐ​ሰት ተና​ገ​ሩ​ብኝ። 14በመ​ኝ​ታ​ቸው ላይ ሆነው ያለ​ቅሱ ነበር እንጂ በል​ባ​ቸው ወደ እኔ አል​ጮ​ኹም፤ ስለ እህ​ልና ስለ ወይን ይገ​ዳ​ደሉ ነበር፤#ዕብ. “በእ​ኔም ላይ ዐመፁ” የሚል ይጨ​ም​ራል። 15በእ​ኔም ዘንድ ተገ​ሠጹ፤ እኔም ክን​ዳ​ቸ​ውን አጸ​ናሁ፤ እነ​ርሱ ግን ክፉ ነገ​ርን መከ​ሩ​ብኝ። 16ወደ ከንቱ ነገር ተመ​ለሱ፤ እንደ ጠማማ ቀስ​ትም ሆኑ፤ አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውም ከም​ላ​ሳ​ቸው ስን​ፍና የተ​ነሣ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ፤ ይህም በግ​ብፅ ምድር ውስጥ መሳ​ለ​ቂያ ይሆ​ን​ባ​ቸ​ዋል።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in