ትንቢተ ሆሴዕ 6
6
የንስሓ ጥሪ
1በመከራቸው ጊዜ በማለዳ ወደ እኔ ይገሰግሳሉ፤ እንዲህም ይላሉ፥ “ኑ፤ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር እንመለስ፤ እርሱ ሰብሮናልና፥ እርሱም ይፈውሰናል፤ እርሱ መትቶናልና፥ እርሱም ይጠግነናል። 2ከሁለት ቀን በኋላ ያድነናል፤ በሦስተኛውም ቀን ያስነሣናል፤ በፊቱም በሕይወት እንኖራለን። 3እንወቀው፤ እናውቀውም ዘንድ እግዚአብሔርን እንከተል፤ እንደ ወገግታም ተዘጋጅቶ እናገኘዋለን፤ በምድርም ላይ እንደ መጀመሪያውና እንደ ኋለኛው ዝናብ ወደ እኛ ይመጣል።#ዕብ. “ምድርን እንደሚያጠጣ የበልግ ዝናብ” ይላል።
4“ምሕረታችሁ እንደ ማለዳ ደመና፥ በማለዳም እንደሚያልፍ ጠል ነውና ኤፍሬም ሆይ! ምን ላድርግልህ? ይሁዳ ሆይ! ምን ላድርግልህ? 5ስለዚህ ነቢያቶቻችሁን አጨድኋቸው፤#ዕብ. “በነቢያት እጅ አጨድኋቸው” ይላል። በአፌም ቃል ገደልኋቸው፤ ፍርዴም እንደ ብርሃን ይወጣል። 6ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን፥ ከሚቃጠልም መሥዋዕት ይልቅ እግዚአብሔርን ማወቅ እወድዳለሁና። 7እነርሱ ግን ቃል ኪዳንን እንደሚያፈርስ ሰው ሆኑ፤ በዚያም ላይ ከዱኝ። 8ገለዓድ ከንቱን የምትሠራና በደም የተቀባች ከተማ ናት፥ 9ሰውን እንደሚያደቡ ወንበዴዎች፥ እንዲሁ ካህናት በሴኬም መንገድ ላይ አድብተው ይገድላሉ፤ ዐመፅንም ያደርጋሉ። 10በእስራኤል ቤት የሚያሰፈራን ነገር አይቻለሁ፤ በዚያ የኤፍሬምንም ዝሙት አየሁ፤ እስራኤልም ረክሶአል። 11ይሁዳ ሆይ! የሕዝቤን ምርኮ በምመልስበት ጊዜ ለአንተ ደግሞ መከር ተወስኖልሃል።”
Currently Selected:
ትንቢተ ሆሴዕ 6: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in