ትንቢተ ሆሴዕ 5
5
ስለ ጣዖት አምልኮ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ
1ካህናት ሆይ! ይህን ስሙ፤ የእስራኤል ቤት ሆይ! አድምጡ፤ የንጉሥ ቤት ሆይ! ልብ አድርጉ፤ ለሚመለከት ወጥመድ፥ በታቦርም ላይ የተዘረጋ አሽክላ ሆናችኋልና ፍርድ በእናንተ ላይ ነው። 2የሚያድኑ አዳኞች ያጠምዱባት ዘንድ ተከሏት፤ እኔ ግን መካሪያችሁ ነኝ።#ዕብ. “ዐመፀኞች ዕርድ አብዝተዋል” ይላል። 3እኔ ኤፍሬምን አውቀዋለሁ፤ እስራኤልም ከእኔ አልራቀም፤ ኤፍሬም ዛሬ አመንዝሮአልና፤ እስራኤልም ረክሶአልና። 4ወደ አምላካቸው ይመለሱ ዘንድ ልባቸውን አላቀኑም፤ የዝሙት መንፈስ በውስጣቸው አለና፤ እግዚአብሔርንም አላወቁትምና። 5የእስራኤልም ትዕቢት በፊቱ ይመሰክራል፤ ስለዚህ እስራኤልና ኤፍሬም በኀጢአታቸው ይደክማሉ፤ ይሁዳም ከእነርሱ ጋር ይደክማል። 6እግዚአብሔርንም ለመሻት ከበጎቻቸውና ከላሞቻቸው ጋር ይሄዳሉ፤ ነገር ግን እርሱ ከእነርሱ ተለይቶአልና አያገኙትም። 7ዲቃሎችን ልጆች ወልደዋልና እግዚአብሔርን ከድተዋል፤ አሁንም ኵብኵባ እነርሱንና ርስታቸውን ይበላቸዋል።
ጦርነት በይሁዳና በእስራኤል መካከል
8በኮረብታ ላይ መለከትን ንፉ፤ በተራሮችም ላይ ጩኹ፤ ብንያም በተዋረደበት በቤትአዌን ዐዋጅ ንገሩ።#ዕብ. “በጊብዓ መለከትን፥ በራባ እንቢልታን ንፉና፦ ብንያም ሆይ! ከአንተ በኋላ እያላችሁ በቤት አዊን ላይ እሪ በሉ” ይላል። 9ኤፍሬም በዘለፋ ቀን ለጥፋት ይሆናል፤ በእስራኤልም ነገዶች የታመነውን ነገር አሳየሁ። 10የይሁዳ አለቆች ድምበርን እንደሚያፈርሱ ሆነዋል፤ እኔም መዓቴን እንደ ውኃ አፈስስባቸዋለሁ። 11ኤፍሬም የተገፋ ሆነ፤ በፍርድም ተረገጠ፤ ከንቱን ይከተል ዘንድ ጀምሮአልና። 12እኔም ለኤፍሬም እንደ ብል፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሀከክ” ይላል። ለይሁዳም ቤት እንደ ነቀዝ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ቀኖት” ይላል። እሆንበታለሁ። 13ኤፍሬምም ደዌውን አያት፤ ይሁዳም ሥቃዩን አያት፤ ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፤ ወደ ንጉሡም ወደ ኢያሪም መልእክተኛን ላከ፤ እርሱ ግን ፈጽሞ ይፈውሳችሁ ዘንድ አልቻለም፤ ከእናንተም ሕማም አልተወገደም። 14እኔም ለኤፍሬም እንደ ነብር፥ ለይሁዳም ቤት እንደ አንበሳ ደቦል እሆናለሁና፤ እኔም ነጥቄ እሄዳለሁ፤ እወስድማለሁ፤ የሚያድናቸውም የለም። 15እስኪጠፉ ድረስ፥#ዕብ. “በደላቸውን እስኪያውቁ ድረስ” ይላል። ፊቴንም እስኪሹ ድረስ እሄዳለሁ፤ ወደ ስፍራዬም እመለሳለሁ።
Currently Selected:
ትንቢተ ሆሴዕ 5: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in