YouVersion Logo
Search Icon

መጽ​ሐፈ ባሮክ 1

1
1የኬ​ል​ቅዩ ልጅ የአ​ሳ​ድዩ ልጅ የሴ​ዴ​ቅ​ያስ ልጅ የማ​ሴው ልጅ የኔ​ርዩ ልጅ ባሮክ ወደ ባቢ​ሎን የጻ​ፈው ነገር ይህ ነው፤ 2በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ዓመት ከወሩ በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ከለ​ዳ​ው​ያን ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን በያ​ዙ​አ​ትና በእ​ሳት በአ​ቃ​ጠ​ሏት ጊዜ፥ 3ባሮክ ይህን መጽ​ሐፍ በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​አ​ቄም ልጅ በኢ​ኮ​ን​ያን ጆሮና መጽ​ሐ​ፉን ለመ​ስ​ማት ከሕ​ዝቡ ዘንድ ወደ እርሱ በመ​ጣው ሕዝብ ሁሉ ጆሮ፥ 4በኀ​ያ​ላ​ኑና በል​ዑ​ላኑ ጆሮ፥ በሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎች ጆሮና ከታ​ላቁ ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ በባ​ቢ​ሎን በሶዲ ወንዝ አጠ​ገብ በሚ​ኖሩ ሕዝብ ሁሉ ጆሮ አነ​በበ። 5እነ​ር​ሱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አለ​ቀሱ፤ ጾሙ፤ ጸለ​ዩም። 6እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸ​ውም እንደ እየ​ች​ሎ​ታ​ቸው ገን​ዘብ ሰበ​ሰቡ፤ 7እር​ሱ​ንም ወደ ሰሉም ልጅ ወደ ኬል​ቅያ ልጅ ወደ ካህኑ ኢዮ​አ​ቄም፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከእ​ርሱ ጋር ወደ ነበ​ሩት ካህ​ና​ትና ወደ ሕዝቡ ሁሉ ላኩት። 8ከቤተ መቅ​ደስ የተ​ወ​ሰ​ደ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ዕቃ ወደ ይሁዳ ምድር ይመ​ልሱ ዘንድ በሲ​ባን ወር በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን በወ​ሰዱ ጊዜ ይህም ዕቃ የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ ሴዴ​ቅ​ያስ ያሠ​ራው የብር ዕቃ ነበር። 9ይኸ​ውም የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ኢኮ​ን​ያ​ን​ንና መኳ​ን​ን​ቱን፥ ምር​ኮ​ኞ​ቹ​ንና ኀያ​ላ​ኑን የሀ​ገ​ሩ​ንም ሕዝብ ይዞ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ባቢ​ሎን ከወ​ሰ​ዳ​ቸው በኋላ ነበር።
ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም የተ​ጻፈ ደብ​ዳቤ
10እን​ዲ​ህም አሉ፥ “እነሆ ገን​ዘብ ልከ​ን​ላ​ች​ኋል፤ በእ​ር​ሱም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፤ ዕጣ​ንም ግዙ​በት፤ ኅብ​ስ​ትም አዘ​ጋጁ፤ በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊ​ያም አቅ​ርቡ። 11ዘመ​ና​ቸው በም​ድር ላይ እንደ ሰማይ ዘመን ይሆን ዘንድ ስለ ባቢ​ሎን ንጉሥ ስለ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ሕይ​ወ​ትና ስለ ልጁ ስለ ብል​ጣ​ሶር ሕይ​ወት ጸልዩ። 12ለእ​ኛም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይ​ልን ይሰ​ጠን ዘንድ፥ ዐይ​ኖ​ቻ​ች​ን​ንም ያበ​ራ​ልን ዘንድ፥ በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ጥላ ሥርና በልጁ በብ​ል​ጣ​ሶር ጥላ ሥር በሕ​ይ​ወት እን​ኖር ዘንድ፥ ለብዙ ዘመ​ንም እን​ገ​ዛ​ላ​ቸው ዘንድ፥ በፊ​ታ​ቸ​ውም ባለ​ሟ​ል​ነ​ትን እና​ገኝ ዘንድ ጸልዩ። 13አም​ላ​ካ​ች​ንን በድ​ለ​ና​ልና፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መዓቱ መቅ​ሠ​ፍ​ቱም እስ​ከ​ዚች ቀን ድረስ ከእኛ አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ች​ምና ለእ​ኛም ወደ አም​ላ​ካ​ችን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸል​ዩ​ልን። 14ወደ እና​ንተ የላ​ክ​ና​ትን ይህ​ች​ንም ደብ​ዳቤ አን​ብ​ቡ​አት፤ በበ​ዓል ቀንና በተ​ወ​ደ​ደ​ውም ዕለት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ተና​ዘዙ።
የኀ​ጢ​አት ኑዛዜ
15“እን​ዲ​ህም በሉ፤ ጽድቅ ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ለእኛ ግን ለፊ​ታ​ችን ኀፍ​ረት ነው፤ ይህች ቀን ለይ​ሁዳ ሰዎ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለሚ​ኖሩ፥ 16ለን​ጉ​ሦ​ቻ​ች​ንና ለአ​ለ​ቆ​ቻ​ችን፥ ለካ​ህ​ኖ​ቻ​ች​ንና ለነ​ቢ​ያ​ቶ​ቻ​ችን፥ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንም ኀፍ​ረት እንደ ሆነች። 17በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በድ​ለ​ና​ልና፤ 18አል​ታ​ዘ​ዝ​ነ​ው​ምና የአ​ም​ላ​ካ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል አል​ሰ​ማ​ን​ምና፤ በሰ​ጠን በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ አል​ሄ​ድ​ን​ምና፤ 19አባ​ቶ​ቻ​ች​ንን ከግ​ብፅ ምድር ከአ​ወ​ጣ​በት ጊዜ ጀምሮ እስ​ከ​ዚች ቀን ድረስ አም​ላ​ካ​ች​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ታ​ዘ​ዝ​ነ​ውም፤ ቃሉ​ንም እን​ዳ​ን​ሰማ ከእ​ርሱ ራቅን። 20ወተ​ትና መዓር የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ውን ምድር ይሰ​ጠን ዘንድ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንን ከግ​ብፅ ምድር በአ​ወ​ጣ​በት ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለባ​ሪ​ያው ለሙሴ ያዘ​ዘው ይህ ክፉ ነገ​ርና መር​ገም እንደ ዛሬው ዕለት አገ​ኘን። 21ወደ እኛ እንደ ላካ​ቸው እንደ ነቢ​ያት ቃል የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ማ​ንም። 22በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ እና​ደ​ርግ ዘንድ ለባ​ዕ​ዳን አማ​ል​ክት እየ​ተ​ገ​ዛን እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችን በክፉ ልባ​ችን ፈቃድ ሄድን።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in