YouVersion Logo
Search Icon

ትን​ቢተ ኤር​ም​ያስ 52

52
የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ውድ​ቀት
1ሴዴ​ቅ​ያስ መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሃያ አንድ ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም አሚ​ጣል የተ​ባ​ለች የል​ብና ሰው የኤ​ር​ም​ያስ ልጅ ነበ​ረች። 2ኢዮ​አ​ቄ​ምም እን​ዳ​ደ​ረገ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረገ። 3ከፊ​ቱም አው​ጥቶ እስ​ኪ​ጥ​ላ​ቸው ድረስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በይ​ሁዳ ላይ ሆኖ​አ​ልና፤ ሴዴ​ቅ​ያ​ስም በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ። #ምዕ. 52 ቍ. 2 እና 3 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
4ሴዴ​ቅ​ያ​ስም በነ​ገሠ በዘ​ጠ​ነ​ኛው ዓመት በዐ​ሥ​ረ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርና ሠራ​ዊቱ ሁሉ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ መጥ​ተው ከበ​ቡ​አት፤ በዙ​ሪ​ያ​ዋም አራት ክንድ ግንብ ሠራ። 5ከተ​ማ​ዪ​ቱም እስከ ንጉሡ እስከ ሴዴ​ቅ​ያስ እስከ ዐሥራ አን​ደ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት ድረስ ተከ​ብባ ነበር። 6በአ​ራ​ተ​ኛ​ውም ወር በዘ​ጠ​ነ​ኛው ቀን በከ​ተ​ማ​ዪቱ ራብ ጸንቶ ነበር፤ ለሀ​ገ​ሩም ሰዎች እን​ጀራ ታጣ። 7ከተ​ማ​ዪ​ቱም ተሰ​በ​ረች፤ ሰል​ፈ​ኞ​ችም ሁሉ ሸሹ፤ በሁ​ለ​ቱም ቅጥር መካ​ከል ባለው በር ወደ ንጉሥ አት​ክ​ልት በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ በሌ​ሊት ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ወጡ። ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም በከ​ተ​ማ​ዪቱ ዙሪያ ነበሩ፤ በዓ​ረ​ባም መን​ገድ ሄዱ። 8የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም ሠራ​ዊት ንጉ​ሡን ተከ​ታ​ተ​ሉት፤ በኢ​ያ​ሪ​ኮም ሜዳ ሴዴ​ቅ​ያ​ስን ያዙ፤ ሠራ​ዊ​ቱም ሁሉ ከእ​ርሱ ዘንድ ተበ​ት​ነው ነበር። 9ንጉ​ሡ​ንም ይዘው የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ወዳ​ለ​ባት በኤ​ማት ምድር#“በኤ​ማት ምድር የሚ​ለው” በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ወዳ​ለ​ችው ወደ ዴብ​ላታ አመ​ጡት፤ እር​ሱም ፍር​ድን በእ​ርሱ ላይ ተና​ገረ። 10የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ የሴ​ዴ​ቅ​ያ​ስን ልጆች በፊቱ ገደ​ላ​ቸው፤ የይ​ሁ​ዳ​ንም አለ​ቆች ሁሉ ደግሞ በዴ​ብ​ላታ ገደ​ላ​ቸው። 11የሴ​ዴ​ቅ​ያ​ስ​ንም ዐይ​ኖች አወጣ፤ የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ በሰ​ን​ሰ​ለት አሰ​ረው፤ ወደ ባቢ​ሎ​ንም ወሰ​ደው፤ እስ​ኪ​ሞ​ትም ድረስ በግ​ዞት ቤት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በወ​ፍጮ ቤት” ይላል። አኖ​ረው።
12በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በዐ​ሥራ ዘጠ​ነ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ፊት የሚ​ቆ​መው የአ​ዛ​ዦች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጣ። 13የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤትና የን​ጉ​ሡን ቤት አቃ​ጠለ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ቤቶች ሁሉ ፥ ታላ​ላ​ቆ​ችን ቤቶች ሁሉ፥ በእ​ሳት አቃ​ጠለ። 14ከአ​ዛ​ዦ​ችም አለቃ ጋር የነ​በ​ረው የከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሠራ​ዊት ሁሉ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ቅጥር ሁሉ ዙሪ​ያ​ዋን አፈ​ረሱ። 15የአ​ዛ​ዦ​ቹም አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን የሕ​ዝ​ቡን ድኆች፥ በከ​ተ​ማም ውስጥ የቀ​ረ​ውን ሕዝብ፥ ሸሽ​ተ​ውም ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ የተ​ጠ​ጉ​ትን፥ የሕ​ዝ​ቡ​ንም ቅሬታ አመጣ።#ምዕ. 52 ቍ. 15 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 16የአ​ዛ​ዦ​ቹም አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን ከሀ​ገሩ ድኆች ወይን ተካ​ዮ​ችና አራ​ሾች እን​ዲ​ሆኑ አስ​ቀረ።
17ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የነ​በ​ሩ​ትን የናስ ዐም​ዶች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የነ​በ​ሩ​ትን መቀ​መ​ጫ​ዎ​ችና የና​ሱን ኩሬ ሰባ​በሩ፤ ናሱ​ንም ወደ ባቢ​ሎን ወሰዱ። 18ምን​ቸ​ቶ​ቹ​ንና መጫ​ሪ​ያ​ዎ​ችን፥ መኰ​ስ​ተ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ንና ድስ​ቶ​ችን፥ ጭል​ፋ​ዎ​ች​ንም፥ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በ​ት​ንም የናስ ዕቃ ሁሉ ወሰዱ። 19የአ​ዛ​ዦ​ችም አለቃ ጽዋ​ዎ​ቹን፥ ማን​ደ​ጃ​ዎ​ቹን፥ ድስ​ቶ​ቹ​ንና ምን​ቸ​ቶ​ቹን፥ መቅ​ረ​ዞ​ቹ​ንና ጭል​ፋ​ዎ​ቹን፥ መን​ቀ​ሎ​ች​ንም፥ የወ​ር​ቁን ዕቃ በወ​ርቅ፥ የብ​ሩ​ንም ዕቃ በብር አድ​ርጎ፥ ወሰደ። 20ንጉሡ ሰሎ​ሞን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ያሠ​ራ​ቸ​ውን ሁለ​ቱን ዐም​ዶች፥ አን​ዱ​ንም ኵሬ፥ ከመ​ቀ​መ​ጫ​ዎ​ቹም በታች የነ​በ​ሩ​ትን ዐሥራ ሁለ​ቱን የናስ በሬ​ዎች ወሰደ፤ ለእ​ነ​ዚህ የናስ ዕቃ​ዎች ሁሉ ሚዛን አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም። 21ዐም​ዶ​ቹም፥ የአ​ንዱ ዓምድ ቁመት ዐሥራ ስም​ንት ክንድ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ቁመቱ ሠላሳ አም​ስት ክንድ” ይላል። ነበረ፥ የዙ​ሪ​ያ​ውም መጠን ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበረ፤ ውፍ​ረ​ቱም ጋት ያህል ነበረ፤ ባዶም ነበረ። 22የና​ሱም ጕል​ላት በላዩ ነበረ፤ የአ​ን​ዱም ጕል​ላት ቁመት አም​ስት ክንድ ነበረ፤ በጕ​ል​ላ​ቱም ላይ በዙ​ሪ​ያው ሁሉ ከናስ የተ​ሠሩ መር​በ​ብና ሮማ​ኖች ነበ​ሩ​በት፤ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ዐምድ ደግሞ እን​ደ​ዚህ ያለ ነገ​ርና ሮማ​ኖች ነበ​ሩ​በት። 23በስተ ውጭም ዘጠና ስድ​ስት ሮማ​ኖች ነበሩ፤ በመ​ር​በ​ቡም ዙሪያ የነ​በሩ ሮማ​ኖች ሁሉ አንድ መቶ ነበሩ።
24የአ​ዛ​ዦ​ቹም አለቃ ታላ​ቅን ካህን ሠራ​ያን፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ካህን ሶፎ​ን​ያ​ስን፥ ሦስ​ቱ​ንም በረ​ኞች ወሰደ፤ 25ከከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም በሰ​ል​ፈ​ኞች ላይ ተሾ​መው ከነ​በ​ሩት አን​ዱን ጃን​ደ​ረባ፥ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ከሚ​ገ​ኙት በን​ጉሡ ፊት ከሚ​ቆ​ሙት ሰባ​ቱን ሰዎች፥ የሀ​ገ​ሩን ሕዝብ የሚ​ያ​ሰ​ል​ፈ​ውን የሠ​ራ​ዊ​ቱን አለቃ ጸሐፊ፥ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ከተ​ገ​ኙት የሀ​ገሩ ሕዝብ ስድሳ ሰዎ​ችን ወሰደ። 26የአ​ዛ​ዦ​ቹም አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን ወስዶ የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ወዳ​ለ​በት ወደ ዴብ​ላታ ወሰ​ዳ​ቸው። 27የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ መታ​ቸው፤ በኤ​ማ​ትም ምድር ባለ​ችው በዴ​ብ​ላታ ገደ​ላ​ቸው፤ እን​ዲሁ ይሁዳ ከሀ​ገሩ ተማ​ረከ።
28ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር የማ​ረ​ከው ሕዝብ ይህ ነው፤ በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት ሦስት ሺህ ሃያ ሦስት አይ​ሁድ፤ 29ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርም በዐ​ሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት ስም​ንት መቶ ሠላሳ ሁለት ነፍስ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ማር​ኮ​አል፤ 30በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በሃያ ሦስ​ተ​ኛው#ግእዝ “አሥራ ዘጠ​ነ​ኛው” ይላል። ዓመተ መን​ግ​ሥት የአ​ዛ​ዦቹ አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን ከአ​ይ​ሁድ ሰባት መቶ አርባ አም​ስት ነፍስ ማር​ኮ​አል፤ ሰዎ​ችም ሁሉ አራት ሺህ ስድ​ስት መቶ ነበሩ።#ምዕ. 52 ከቁ. 28 እስከ 30 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
ኢኮ​ን​ያን እንደ ተፈታ
31እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢኮ​ን​ያን በተ​ማ​ረከ በሠ​ላሳ ሰባ​ተ​ኛው ዓመት፥ በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በሃያ አም​ስ​ተ​ኛው#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በሃያ አራ​ተ​ኛው ቀን” ይላል። ቀን፥ የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ዮር​ማ​ሮ​ዴቅ በነ​ገሠ በአ​ን​ደ​ኛው ዓመት የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ የኢ​ኮ​ን​ያ​ንን ራስ ከፍ ከፍ አደ​ረገ፤ ከወ​ህ​ኒም አወ​ጣው፤ 32በመ​ል​ካ​ምም ተና​ገ​ረው፤ ዙፋ​ኑ​ንም ከእ​ርሱ ጋር በባ​ቢ​ሎን ከነ​በ​ሩት ነገ​ሥ​ታት ዙፋን በላይ አደ​ረ​ገ​ለት። 33በወ​ህ​ኒም ውስጥ ለብ​ሶት የነ​በ​ረ​ውን ልብስ ለወ​ጠ​ለት፥ ኢኮ​ን​ያ​ንም በሕ​ይ​ወቱ ዘመን ሁሉ በፊቱ ሁል​ጊዜ እን​ጀራ ይበላ ነበር። 34የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ በሕ​ይ​ወቱ ዘመን ሁሉ እስ​ኪ​ሞት ድረስ የዘ​ወ​ትር ድርጎ ዕለት ዕለት ይሰ​ጠው ነበር።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in