YouVersion Logo
Search Icon

ትን​ቢተ አሞጽ 6

6
የእ​ስ​ራ​ኤል ቅጣት
1ጽዮ​ንን ለሚ​ንቁ፥ በሰ​ማ​ር​ያም ተራራ ለሚ​ታ​መኑ ሰዎች ወዮ​ላ​ቸው፤ የአ​ሕ​ዛ​ብን አለ​ቆች ለቀ​ሙ​አ​ቸው። 2የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ፥ ወደ ካልኔ ተሻ​ግ​ራ​ችሁ ተመ​ል​ከቱ፤ ከዚ​ያም ወደ ኤማ​ት​ራባ እለፉ፤ ከዚ​ያም ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤም ጌት ውረዱ፤ እነ​ርሱ ከእ​ነ​ዚህ መን​ግ​ሥ​ታት ይበ​ረ​ታሉ፤ ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ከድ​ን​በ​ራ​ቸው ይሰ​ፋ​ልና። 3ክፉ ቀንን ለሚ​ፈ​ል​ጓት፥ የሐ​ሰት ሰን​በ​ታ​ትን ለሚ​ያ​ቀ​ራ​ር​ቡና አንድ ለሚ​ያ​ደ​ርጉ፥#ዕብ. “ክፉ​ውን ቀን ከእ​ና​ንተ ለም​ታ​ርቁ፥ የግ​ፍ​ንም ወን​በር ለም​ታ​ቀ​ርቡ” ይላል። 4ከዝ​ሆን ጥርስ በተ​ሠራ አልጋ ላይ ለሚ​ተኙ፥ በም​ን​ጣ​ፋ​ቸው ደስ ለሚ​ሰኙ፥ ከበ​ጎ​ችም መንጋ ጠቦ​ትን፥ ከጋ​ጥም ውስጥ ጥጃን ለሚ​መ​ገቡ፥ 5ከበ​ገ​ናው ድምፅ ጋር#ዕብ. “ከዳ​ዊት በገና ጋር” ይላል። አስ​ተ​ባ​ብ​ረው ለሚ​ያ​ጨ​በ​ጭቡ ሰዎች፤ ይኸ​ውም የማ​ያ​ልፍ ለሚ​መ​ስ​ላ​ቸ​ውና እን​ደ​ሚ​ያ​መ​ል​ጣ​ቸው ለማ​ያ​ውቁ፤ 6በጽዋ የቀላ ወይን ለሚ​ጠጡ፥ እጅግ በአ​ማረ ሽቱም ለሚ​ቀቡ፥ በዮ​ሴፍ ስብ​ራት ለማ​ያ​ስቡ ወዮ​ላ​ቸው።
7ስለ​ዚህ ከአ​ለ​ቆ​ቻ​ቸው አስ​ቀ​ድ​መው ይማ​ረ​ካሉ፤ ሯጮች የሚ​ሆኑ የኤ​ፍ​ሬም ፈረ​ሶ​ችም ያል​ቃሉ። 8ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “የያ​ዕ​ቆ​ብን ትዕ​ቢት አረ​ክ​ሳ​ለሁ፤ ሀገ​ሮ​ቹ​ንም ጠላሁ፤ ከተ​ሞ​ቹ​ንም ከሚ​ኖ​ሩ​ባ​ቸው ሰዎች ጋር አጠ​ፋ​ለሁ” ብሎ በራሱ ምሎ​አ​ልና። 9እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ ዐሥር ሰዎች በአ​ንድ ቤት ውስጥ ቢቀሩ እነ​ርሱ ይሞ​ታሉ፤ የቀ​ሩት ግን ይተ​ር​ፋሉ።#“የቀ​ሩት ግን ይተ​ር​ፋሉ” የሚ​ለው በዕብ. የለም። 10አጥ​ን​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ከቤት ያወጡ ዘንድ ቤተ​ሰ​ቦ​ቻ​ቸው በወ​ሰ​ዱ​አ​ቸው ጊዜ፥ ቤት ጠባ​ቂ​ውን በአ​ንተ ዘንድ የቀረ አለን? በአ​ለው ጊዜ እርሱ የለም ይላል። ያም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም እን​ዳ​ት​ጠራ ዝም በል ይለ​ዋል። 11እነ​ሆም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዝ​ዛል፤ ታላ​ቁ​ንም ቤት በማ​ፍ​ረስ፥ ታና​ሹ​ንም ቤት በመ​ሰ​ባ​በር ይመ​ታል። 12ፍር​ድን ወደ ቍጣ፥ የእ​ው​ነ​ት​ንም ፍሬ ወደ እሬት ለው​ጣ​ች​ኋ​ልና፥ በውኑ ፈረ​ሶች በጭ​ንጫ ላይ ይሮ​ጣ​ሉን? ወይስ በሬ​ዎች በዚያ ላይ ያር​ሳ​ሉን?#ግእዝ “ወያ​ረ​ም​ሙኑ እም​አ​ን​ስት” ይላል። 13በከ​ንቱ ነገር ደስ የሚ​ላ​ችሁ በኀ​ይ​ላ​ችን ቀን​ዶ​ችን አበ​ቀ​ልን የም​ትሉ አይ​ደ​ለ​ምን? 14“የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ እነሆ እኔ የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቋ​ች​ሁን ሕዝብ አስ​ነ​ሣ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፥” ይላል የሠ​ራ​ዊት አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እነ​ር​ሱም ከሐ​ማት መግ​ቢያ ጀም​ረው እስከ ዐረባ ወንዝ ድረስ ትገቡ ዘንድ አይ​ፈ​ቅ​ዱ​ላ​ች​ሁም።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in