YouVersion Logo
Search Icon

መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ቀዳ​ማዊ 9

9
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሰ​ሎ​ሞን ዳግ​መኛ እንደ ተገ​ለ​ጠ​ለት
(2ዜ.መ. 7፥11-22)
1ከዚ​ህም በኋላ ሰሎ​ሞን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት፥ የን​ጉ​ሡን ቤትና ሰሎ​ሞን ያደ​ር​ገው ዘንድ የወ​ደ​ደ​ውን ሁሉ ሠርቶ በፈ​ጸመ ጊዜ፥ 2እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በገ​ባ​ዖን ለሰ​ሎ​ሞን እንደ ተገ​ለ​ጠ​ለት ዳግ​መኛ ተገ​ለ​ጠ​ለት። 3እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “በፊቴ የጸ​ለ​ይ​ኸ​ውን ጸሎ​ት​ህ​ንና ልመ​ና​ህን ሰም​ቻ​ለሁ፤ እንደ ጸሎ​ት​ህም ሁሉ አደ​ረ​ግ​ሁ​ልህ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ስሜ በዚያ ያድር ዘንድ ይህን የሠ​ራ​ኸ​ውን ቤት ቀድ​ሻ​ለሁ፤ ዐይ​ኖ​ችና ልቤም በዘ​መኑ ሁሉ በዚያ ይሆ​ናሉ። 4ዳዊ​ትም አባ​ትህ በጽ​ድቅ፥ በን​ጹሕ ልብና በቅ​ን​ነት እንደ ሄደ አንተ ደግሞ በፊቴ ብት​ሄድ፥ ያዘ​ዝ​ሁ​ህ​ንም ሁሉ ብታ​ደ​ርግ፥ ሥር​ዐ​ቴ​ንም ሕጌ​ንም ብት​ጠ​ብቅ፥ 5እኔ፦ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ የሚ​ገዛ ሰውን ከአ​ንተ አላ​ጠ​ፋም ብዬ ለአ​ባ​ትህ ለዳ​ዊት እንደ ተና​ገ​ርሁ፥ የመ​ን​ግ​ሥ​ት​ህን ዙፋን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጸ​ና​ለሁ። 6ነገር ግን እና​ን​ተና ልጆ​ቻ​ችሁ እኔን ትታ​ችሁ ወደ ኋላ ብት​መ​ለሱ ለሙሴ በፊ​ታ​ችሁ የሰ​ጠ​ሁ​ትን ትእ​ዛ​ዜ​ንና ሥር​ዐ​ቴን ባት​ጠ​ብቁ፥ ሄዳ​ች​ሁም ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ብታ​መ​ልኩ፥ ብት​ሰ​ግ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፥ 7እስ​ራ​ኤ​ልን ከሰ​ጠ​ኋ​ቸው ምድር አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ለስ​ሜም የቀ​ደ​ስ​ሁ​ትን ይህን ቤት ከፊቴ እጥ​ለ​ዋ​ለሁ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ መካ​ከል ለጥ​ፋ​ትና ለተ​ረት ይሆ​ናሉ። 8ከፍ ከፍ ብሎ የነ​በ​ረ​ውም ይህ ቤት ባድማ ይሆ​ናል፤ በዚ​ያም የሚ​ያ​ልፍ ሁሉ እያ​ፍ​ዋጨ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ሀገ​ርና በዚህ ቤት ስለ ምን እን​ዲህ አደ​ረገ? ብሎ ይደ​ነ​ቃል። 9መል​ሰ​ውም፦ ከግ​ብፅ ምድር ከባ​ር​ነት ቤት አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ያወ​ጣ​ውን አም​ላ​ካ​ቸ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትተው ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ስለ ተከ​ተሉ፥ ስለ ሰገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፥ ስለ አመ​ለ​ኩ​አ​ቸ​ውም፥ ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመ​ጣ​ባ​ቸው ይላሉ።”#የምዕ. 9 ቍ. 9 የመ​ጨ​ረ​ሻው ዐረ​ፍተ ነገር በዕብ. የለም። ያን​ጊ​ዜም ሰሎ​ሞን የፈ​ር​ዖ​ንን ልጅ ከዳ​ዊት ከተማ አው​ጥቶ በዚያ ወራት ለራሱ በሠ​ራው ቤት አስ​ገ​ባት። 10ሰሎ​ሞ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤትና የን​ጉ​ሡን ቤት ሁለ​ቱን ቤቶች በሠ​ራ​በት በሃያ ዓመት ውስጥ፥ 11የጢ​ሮስ ንጉሥ ኪራም በዝ​ግ​ባና በጥድ እን​ጨት፥ በወ​ር​ቅና በሚ​ሻ​ውም ሁሉ ሰሎ​ሞ​ንን ረድ​ቶት ነበር። ያን​ጊ​ዜም ንጉሡ ሰሎ​ሞን በገ​ሊላ ምድር ያሉ​ትን ሃያ ከተ​ሞች ለኪ​ራም ሰጠው። 12ኪራ​ምም ሰሎ​ሞን የሰ​ጠ​ውን ከተ​ሞች ያይ ዘንድ ከጢ​ሮስ ወጣ፤ ወደ ገሊ​ላም ሄደ፤#“ወደ ገሊ​ላም ሄደ” የሚ​ለው በዕብ. የለም። ደስም አላ​ሰ​ኙ​ትም። 13እር​ሱም አለው፥ “ወን​ድሜ ሆይ! የሰ​ጠ​ኸኝ እነ​ዚህ ከተ​ሞች ምን​ድን ናቸው?” እስከ ዛሬም ድረስ ወሰን ብሎ ጠራ​ቸው። 14ኪራ​ምም መቶ ሃያ መክ​ሊት ወርቅ ለሰ​ሎ​ሞን አመጣ።
15ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤትና ቤተ መን​ግ​ሥ​ቱን፥ ሜሎ​ን​ንም፥ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ቅጥር፥ አሶ​ር​ንም፥ መጊ​ዶ​ንም፥ ጋዜ​ር​ንም ይሠራ ዘንድ ሠራ​ተ​ኞ​ችን መል​ምሎ ነበር። 16የግ​ብ​ፅም ንጉሥ ፈር​ዖን ወጥቶ ጋዜ​ርን ያዘ፤ በእ​ሳ​ትም አቃ​ጠ​ላት፤ በሜ​ር​ጎብ#ዕብ. “በከ​ተማ” ይላል። ይኖሩ የነ​በ​ሩ​ትን ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ን​ንም ገደ​ላ​ቸው፤ ለል​ጁም ለሰ​ሎ​ሞን ሚስት እነ​ዚ​ያን አገ​ሮች ትሎት አድ​ርጎ ሰጥ​ቶ​አት ነበር። 17ሰሎ​ሞ​ንም ጋዜ​ር​ንና የታ​ች​ኛ​ውን ቤቶ​ሮ​ንን፥ ባዕ​ላ​ት​ንም ሠራ፤ 18በም​ድረ በዳ ሀገር ያለ​ች​ውን ኤያ​ቴ​ር​ሞ​ትን ሠራ፤ 19ለሰ​ሎ​ሞ​ንም የነ​በ​ሩ​ትን የዕቃ ቤት ከተ​ሞች ሁሉ፤ የሰ​ረ​ገ​ላ​ው​ንም ከተ​ሞች፥ የፈ​ረ​ሰ​ኞ​ች​ንም ከተ​ሞች፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም፥ በሊ​ባ​ኖ​ስም፥ በመ​ን​ግ​ሥ​ቱም ምድር ሁሉ ሰሎ​ሞን ይሠራ ዘንድ የወ​ደ​ደ​ውን ሁሉ ሠራ። 20ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ዘንድ ያል​ነ​በ​ሩ​ትን ከአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንና ከኬ​ጤ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ከከ​ና​ኔ​ዎን፥ ከፌ​ር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ከኤ​ዌ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ከኢ​ያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንና ከጌ​ር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያን፥ የቀ​ሩ​ትን አሕ​ዛብ ሁሉ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ በም​ድ​ሪቱ የቀ​ሩ​ትን፥ 21የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ያጠ​ፉ​አ​ቸው ዘንድ ያል​ቻ​ሉ​ትን፥ ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ሰሎ​ሞን እሰከ ዛሬ ድረስ ገባ​ሮች አድ​ርጎ መለ​መ​ላ​ቸው። 22ሰሎ​ሞ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማን​ንም ገባር አላ​ደ​ረ​ገም፤ እነ​ርሱ ግን ተዋ​ጊ​ዎች፥ ሎሌ​ዎ​ችም፥ መሳ​ፍ​ን​ትም፥ አለ​ቆ​ችም፥ የሰ​ረ​ገ​ሎ​ችና የፈ​ረ​ሶች ባል​ደ​ራ​ሶች ነበሩ። 23ሰሎ​ሞ​ንም በሚ​ሠ​ራው ሥራ ላይ ሠራ​ተ​ኛ​ውን ሕዝብ የሚ​ያ​ዝዙ አለ​ቆች አም​ስት መቶ አምሳ ነበሩ።
24የፈ​ር​ዖ​ን​ንም ልጅ ከዳ​ዊት ከተማ ሰሎ​ሞን ወደ ሠራ​ላት ወደ ቤቷ አመ​ጣት፤ በዚያ ጊዜም ሚሎ​ንን ሠራት።
25ሰሎ​ሞ​ንም በየ​ዓ​መቱ ሦስት ጊዜ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንና የሰ​ላ​ሙን መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሠ​ራው መሠ​ዊያ ላይ ያሳ​ርግ ነበር፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ባለው መሠ​ዊያ ላይ ዕጣን ያሳ​ርግ ነበር፤ ቤቱ​ንም ጨረሰ።
26ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን በኤ​ዶ​ም​ያስ ምድር በኤ​ር​ትራ ባሕር ዳር በኤ​ላት አጠ​ገብ ባለ​ችው በጋ​ሴ​ዎ​ን​ጋ​ቤር መር​ከ​ቦ​ችን ሠራ። 27ኪራ​ምም በእ​ነ​ዚያ መር​ከ​ቦች ከሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋ​ዮች ጋር ባሕ​ሩን መቅ​ዘፍ የሚ​ያ​ውቁ መር​ከ​በ​ኞች አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን ላከ። 28ወደ አፌ​ርም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሶፌራ” ይላል። ደረሱ፤ ከዚ​ያም አራት መቶ ሃያ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “መቶ ሃያ” ይላል። መክ​ሊት ወርቅ ወሰዱ፤ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎ​ሞ​ንም ይዘው አገቡ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in