YouVersion Logo
Search Icon

መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ቀዳ​ማዊ 14

14
1በዚ​ያም ወራት የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ልጅ አብያ እጅግ ታመመ። 2ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ሚስቱ ሐኖ​ንን፥ “ተነሺ፥ ራስ​ሽን ለውጪ የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ሚስት እንደ ሆንሽ ማንም አይ​ወቅ፤ ወደ ሴሎም ሂጂ፤ ስለ​ዚ​ህም ሕፃን ከደ​ዌው ይድን እን​ደ​ሆነ ጠይቂ፤ እነሆ፥ በዚህ ሕዝብ ላይ እን​ደ​ም​ነ​ግሥ የነ​ገ​ረኝ ነቢዩ አኪያ በዚያ አለ። 3በእ​ጅ​ሽም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ዐሥር እን​ጀ​ራና የወ​ይን እሸት አን​ድም ማሠሮ ማር ይዘሽ ወደ እርሱ ሂጂ፤ በል​ጁም የሚ​ሆ​ነ​ውን ይነ​ግ​ር​ሻል” አላት። 4የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ሚስት እን​ዲሁ አደ​ረ​ገች፤ ተነ​ሥ​ታም እን​ጀራ፥ የወ​ይን ዘለ​ላና አንድ ማሠሮ ማር በመ​ያዝ ወደ ሴሎ ሄደች፤ ወደ አኪ​ያም ቤት ገባች። አኪያ ግን ስለ መሸ​ም​ገሉ ዐይ​ኖቹ ፈዝ​ዘው ነበ​ርና ማየት አል​ቻ​ለም። 5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አኪ​ያን፥ “እነሆ፥ ስለ ታመ​መው ልጅዋ ትጠ​ይ​ቅህ ዘንድ የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ሚስት ትመ​ጣ​ለች፤ ራስ​ዋ​ንም ለውጣ ወደ አንተ በገ​ባች ጊዜ እን​ዲ​ህና እን​ዲህ በላት” አለው።
6እር​ስ​ዋም በደጅ ስት​ገባ አኪያ የእ​ግ​ር​ዋን ኮቴ ሰማ፤ እን​ዲ​ህም አላት፥ “የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ሚስት ሆይ፥ ግቢ! ስለ​ም​ንስ ራስ​ሽን ለወ​ጥሽ? እኔም የሚ​ያ​ስ​ጨ​ንቅ ወሬ ይዤ ወደ አንቺ ተል​ኬ​አ​ለሁ። 7ሂጂ ለኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም እን​ዲህ በዪው፦ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ከሕ​ዝብ መካ​ከል ለይቼ ከፍ አድ​ር​ጌህ ነበር፤ በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይም ንጉሥ አድ​ር​ጌህ ነበር። 8ከዳ​ዊ​ትም ቤት፤ መን​ግ​ሥ​ቱን ከፍዬ ሰጥ​ቼህ ነበር፤ ነገር ግን በፍ​ጹም ልቡ እንደ ተከ​ተ​ለኝ፥ በፊ​ቴም ቅን ነገር ብቻ እን​ዳ​ደ​ረገ፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም እንደ ጠበቀ እንደ ባሪ​ያዬ እንደ ዳዊት አል​ሆ​ን​ህም። 9ከአ​ን​ተም አስ​ቀ​ድ​መው ከነ​በ​ሩት ሁሉ ይልቅ ክፉ ሠራህ፤ ታስ​ቈ​ጣ​ኝም ዘንድ ሄደህ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክ​ትና ቀል​ጠው የተ​ሠ​ሩ​ትን ምስ​ሎች አደ​ረ​ግህ፤ ወደ ኋላ​ህም ተው​ኸኝ። 10ስለ​ዚህ እነሆ፥ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ቤት ላይ መከ​ራን አመ​ጣ​ለሁ፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ም​ንም አጠ​ፋ​ዋ​ለሁ፤ አጥር ተጠ​ግቶ እስ​ከ​ሚ​ሸን ወንድ ድረስ አላ​ስ​ቀ​ር​ለ​ትም፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ይነ​ግሥ ዘንድ አል​ተ​ወ​ውም፤ ሰው ገለባ እስ​ኪ​ያ​ልቅ ድረስ እን​ደ​ሚ​ያ​ነ​ድድ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ቤት ላይ እሳ​ትን አነ​ዳ​ለሁ። 11እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገረ ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ወገን በከ​ተ​ማ​ዪቱ ውስጥ የሞ​ተ​ውን ውሾች ይበ​ሉ​ታል፤ በሜ​ዳ​ውም የሞ​ተ​ውን የሰ​ማይ ወፎች ይበ​ሉ​ታል። 12እን​ግ​ዲህ ተነ​ሥ​ተሽ ወደ ቤትሽ ሂጂ፤ እግ​ር​ሽም ወደ ከተማ በገባ ጊዜ ልጅሽ ይሞ​ታል። 13ደን​ገ​ጡ​ሮ​ች​ሽም ሊቀ​በ​ሉሽ ይወ​ጣሉ፤ ልጅ​ሽም ሞተ ይሉ​ሻል፥#“ደን​ገ​ጥ​ሮ​ች​ሽም ሊቀ​በ​ሉሽ ይወ​ጣሉ ልጅ​ሽም ሞተ ይሉ​ሻል” የሚ​ለው በዕብ. እና በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ያለ​ቅ​ሱ​ለ​ታል፤ ይቀ​ብ​ሩ​ት​ማል፤ በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ቤት በዚህ ልጅ መል​ካም ነገር ተገ​ኝ​ቶ​በ​ታ​ልና ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም እርሱ ብቻ ይቀ​በ​ራል። 14እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደግሞ የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምን ቤት የሚ​ያ​ጠፋ ንጉሥ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ያነ​ግ​ሣል፤ እር​ሱም ዛሬ ይደ​ረ​ጋል፤ እን​ግ​ዲህ ወዲህ ምን እና​ገ​ራ​ለሁ? 15በዚያ ጊዜም ሸም​በቆ በውኃ ውስጥ እን​ደ​ሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲሁ እስ​ራ​ኤ​ልን ይመ​ታል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ያስ​ቈጡ ዘንድ የማ​ም​ለ​ኪያ አፀድ ተክ​ለ​ዋ​ልና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ከሰ​ጣ​ቸው ከዚች ከመ​ል​ካ​ሚቱ ምድር እስ​ራ​ኤ​ልን ይነ​ቅ​ላል፤ በወ​ን​ዙም ማዶ ይበ​ት​ና​ቸ​ዋል። 16ስለ በደ​ለ​ውና እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ስላ​ሳ​ተ​በት ስለ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አት እስ​ራ​ኤ​ልን ይጥ​ላል።”
17የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ሚስት ተነ​ሥታ ሄደች፤ ወደ ቴር​ሳም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሳሪራ” ይላል። መጣች፤ ወደ ቤቱም መድ​ረክ በገ​ባች ጊዜ ልጁ ሞተ። 18በባ​ሪ​ያ​ውም በነ​ቢዩ በአ​ኪያ እንደ ተነ​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እስ​ራ​ኤል ሁሉ ቀበ​ሩት፥ አለ​ቀ​ሱ​ለ​ትም።
19የቀ​ረ​ውም የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ነገር፥ እን​ዴት እንደ ተዋጋ፥ እን​ዴ​ትም እንደ ነገሠ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል። 20ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም የነ​ገ​ሠ​በት ዘመን ሃያ አራት#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሃያ ሁለት” ይላል። ዓመት ነበረ፥ ከአ​ባ​ቶ​ቹም ጋር አን​ቀ​ላፋ፥ ልጁም ናባጥ#ዕብ. “ናዳብ” ይላል። በፋ​ን​ታው ነገሠ።
የይ​ሁዳ ንጉሥ ሮብ​ዓም
(2ዜ.መ. 11፥5—12፥15)
21የሰ​ሎ​ሞ​ንም ልጅ ሮብ​ዓም በይ​ሁዳ ነገሠ፤ ሮብ​ዓ​ምም ንጉሥ በሆነ ጊዜ የአ​ርባ አንድ ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስሙን ያኖ​ር​ባት ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ በመ​ረ​ጣት ከተማ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ዐሥራ ሰባት ዓመት ነገሠ፤ የእ​ና​ቱም ስም ናዕማ ነበረ፥ እር​ስ​ዋም አሞ​ና​ዊት ነበ​ረች። 22ሮብ​ዓ​ምም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ሠራ፤ አባ​ቶቹ በሠ​ሩት ኀጢ​አ​ትና በደል ሁሉ እንደ አስ​ቀ​ኑት በሠ​ራው ኀጢ​አት አስ​ቀ​ናው። 23እነ​ር​ሱም ደግሞ ከፍ ባለው ኮረ​ብታ ሁሉ ላይ፥ ቅጠ​ሉም ከለ​መ​ለመ ዛፍ ሁሉ በታች መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችን ሠሩ፤ ሐው​ል​ቶ​ች​ንና የማ​ም​ለ​ኪያ አፀ​ዶ​ች​ንም ለራ​ሳ​ቸው አቆሙ። 24በም​ድ​ርም ሁሉ ዐመፅ ነበረ፥#ዕብ. “በም​ድር ውስጥ ሰዶ​ማ​ው​ያን ነበሩ” ይላል። ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያሳ​ደ​ዳ​ቸው የአ​ሕ​ዛ​ብን ርኵ​ሰት ሁሉ ያደ​ርጉ ነበር።
25ሮብ​ዓ​ምም በነ​ገሠ በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ዓመት የግ​ብፅ ንጉሥ ሱስ​ቀም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ ዘመተ። 26የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ መዛ​ግ​ብ​ትና የን​ጉ​ሡን ቤተ መዛ​ግ​ብት ሁሉ ወሰደ፤ ዳዊ​ትም ከሱባ ንጉሥ ከአ​ድ​ር​ዓ​ዛር ልጆች እጅ ወስዶ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ያመ​ጣ​ቸ​ውን የወ​ርቅ ጦሮ​ችና ሰሎ​ሞን የሠ​ራ​ቸ​ውን የወ​ር​ቁን ጋሻና ጦር ሁሉ ወደ ግብፅ ወሰደ። 27ንጉ​ሡም ሮብ​ዓም በፋ​ን​ታው የናስ ጋሾ​ችን ሠራ፤ በፊ​ቱም ለሚ​ሮ​ጡና የን​ጉ​ሥን ቤት ደጅ ለሚ​ጠ​ብቁ የዘ​በ​ኞች አለ​ቆች ሰጣ​ቸው። 28ከዚህ በኋላ ንጉሡ ዘወ​ትር ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ሲገባ ዘበ​ኞች ይሸ​ከ​ሙ​አ​ቸው ነበር፤ መል​ሰ​ውም በዘ​በ​ኞች ቤት ውስጥ ያኖ​ሩ​አ​ቸው ነበር።
29የቀ​ረ​ውም የሮ​ብ​ዓም ነገር፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት ታሪክ መጽ​ሐፍ እነሆ፥ ተጽ​ፎ​አል። 30በዘ​መ​ኑም ሁሉ በሮ​ብ​ዓ​ምና በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም መካ​ከል ጦር​ነት ነበረ። 31ሮብ​ዓ​ምም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፥ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ተቀ​በረ። ልጁም አብያ በፋ​ን​ታው ነገሠ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in