YouVersion Logo
Search Icon

የሉቃስ ወንጌል መግቢያ

መግቢያ
የሉቃስ ወንጌል ውስጥ ብዙ ክርስቶሳዊ ጭብጦችን እናገኛለን፤ ከነዚህም ውስጥ የመዳን ምሥጢር ዋነኛው ጭብጥ ነው። ወንጌሉ መዳን የሰው ልጆችን ሁሉ የሚመለከት መሆኑን አበክሮ ያሳያል። ከዚህም የተነሣ ኢየሱስ ሁሉንም ሰውና ሁሉንም ግዛት የእግዚአብሔር ቤተሰብ አድርጎ ለመሰብሰብ እንደመጣ ይተነትናል። እንዲሁም ኢየሱስ ቀደም ብሎ ይመጣል ተብሎ በነቢያት የተነገረለትና፥ የእስራኤል ሕዝብ ሲጠባበቀው የነበረው “መሢሕ” እንደሆነ ይገልጻል።
የሉቃስ ወንጌልን ከሌሎቹ ወንጌሎች ለየት የሚያደርጉት ነጥቦች አሉ፤ ከነዚህም ውስጥ ለድሆች፥ ለአሕዛብ፥ ለሴቶች የሚሰጠው ልዩ ትኩረት ይገኝበታል። የሉቃስ ወንጌል የምሕረትና የደስታ ወንጌል ተብሎም ይጠራል። ስለ ደጉ ሳምራዊ (10፥25-37)፥ ጠፍቶ ስለ ተመለሰው ልጅ ታሪክ (15፥11-32)፥ ስለ መላእኩ ገብርኤል የማርያም ብሥራት (1፥26-38)፥ ኢየሱስ በልጅነቱ ወደ ቤተ መቅደስ ስለ መሄዱ (2፥41-51)፥ የምናገኘው በሉቃስ ወንጌል ብቻ ነው። ውብ የሆኑ ዝማሬዎች፥ ማለትም፦ የማርያም የምስጋና ጸሎት (1፥46-55)፥ የዘካርያስ ቡራኬ (1፥46-55)፥ የአረጋዊው ስምዖን ቡራኬ (2፥29-35)፥ “ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን! ሰላምም ደስ በሚሰኝባቸው ሰዎች መካከል በምድር ይሁን!” የሚለው የመላእክት ዝማሬ በሉቃስ ውስጥ የምናገኛቸው ናቸው።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መቅድም (1፥1-4)
የኢየሱስ መወለድ (1፥5—2፥52)
ኢየሱስ ለአገልግሎት ያደረገው ዝግጅት (3፥1—4፥13)
አገልግሎቱን በገሊላ መጀመሩ (4፥14—9፥50)
ወደ ኢየሩሳሌም መጓዙና የሉቃስ የጉዞው ትረካ (9፥51—19፥27)
በኢየሩሳሌም የማስተማር አገልግሎት (19፥28—21፥38)
የሕማማቱ ታሪክ (22፥1—23፥56)
የትንሣኤው ታሪክ (24፥1-53)
ምዕራፍ

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in