YouVersion Logo
Search Icon

የማርቆስ ወንጌል 16

16
የኢየሱስ ትንሣኤ
(ማቴ. 28፥1-8ሉቃ. 24፥1-12ዮሐ. 20፥1-10)
1ሰንበት ካለፈ በኋላ መግደላዊት ማርያም፥ የያዕቆብ እናት ማርያምና ሰሎሜ ሄደው የኢየሱስን ሥጋ ለመቀባት ሽቱ ገዙ። 2በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን ጠዋት በማለዳ፥ ገና ፀሓይ እንደ ወጣች፥ ወደ መቃብሩ በመሄድ ላይ ሳሉ፥ 3“ድንጋዩን ከመቃብሩ ደጃፍ ላይ ማን ያንከባልልልናል?” በማለት እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ነበር። 4ቀና ብለው ሲመለከቱ፥ በጣም ትልቅ የነበረው ድንጋይ ከደጃፉ ላይ ተንከባሎ አዩ። 5ወደ መቃብሩ እንደ ገቡም፥ ነጭ ልብስ የለበሰ ጐልማሳ በቀኝ በኩል ተቀምጦ አዩና ደነገጡ። 6እርሱ ግን እንዲህ አላቸው፤ “አትደንግጡ፤ የምትፈልጉት የተሰቀለውን የናዝሬቱ ኢየሱስን ነው፤ እርሱ ተነሥቷል፤ እዚህ የለም፤ እርሱን ያኖሩበት ስፍራ ይኸውላችሁ። 7#ማቴ. 26፥32፤ ማር. 14፥28።ነገር ግን ሄዳችሁ ለደቀ መዛሙርቱና ለጴጥሮስ፥ ቀድሟችሁ ወደ ገሊላ ይሄዳል፤ እንደነገራችሁ እዚያ ታገኙታላችሁ፥ ብላችሁ ንገሯቸው።” 8ሴቶቹም እየተንቀጠቀጡና እየተደነቁ ከመቃብሩ ሸሽተው ወጡ፤ ፈርተው ስለ ነበር ለማንም አንዳች አልተናገሩም።
ኢየሱስ ለመግደላዊት ማርያም እንደ ታየ
(ማቴ. 28፥9-10ዮሐ. 20፥11-18)
9በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን ማለዳ ከሙታን ከተነሣ በኋላ፥ ሰባት አጋንንት ላወጣላት ለማርያም መግደላዊት በመጀመሪያ ታየ። 10እርሷም ሄዳ፥ ከእርሱ ጋር የነበሩት እያዘኑ ሲያለቅሱ አግኝታ እርሱ ሕያው መሆኑንና ለእርሷም መታየቱን ነገረቻቸው፤ 11እነርሱ ግን አላመኗትም።
ኢየሱስ ለሁለት ደቀ መዛሙርት እንደ ታየ
(ሉቃ. 24፥13-35)
12ከዚህ በኋላ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱ ወደ ገጠር ሲሄዱ በሌላ መልክ ታያቸው። 13እነርሱም ተመልሰው ይህንኑ ለቀሩት ነገሯቸው፤ ይሁን እንጂ እነርሱንም አላመኗቸውም።
ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲያስተምሩ መላኩ
(ማቴ. 28፥16-20ሉቃ. 24፥36-49ዮሐ. 20፥19-23የሐዋ. 1፥6-8)
14ከዚያም ዐሥራ አንዱ በማዕድ ላይ ሳሉ ተገለጠላቸው፤ ከተነሣ በኋላ ያዩት ሰዎች የነገሯቸውን ስላላመኗቸው፥ አለማመናቸውንና የልባቸውን ድንዳኔ ነቀፈ። 15#የሐዋ. 1፥8።እንዲህም አላቸው፤ “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፤ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ፤ 16ያመነና የተጠመቀ ይድናል፤ ያላመነ ግን ይፈረድበታል። 17የሚያምኑትን እነዚህ ምልክቶች ይከተሏቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ልሳንም ይናገራሉ፤ 18እባቦችን በእጃቸው ይይዛሉ፤ የሚገድል መርዝ ቢጠጡ እንኳ አይጐዳቸውም፤ እጃቸውንም በሕመምተኞች ላይ ይጭናሉ፤ እነርሱም ይፈወሳሉ።”
ኢየሱስ ወደ ሰማይ እንደ ዐረገ
(ሉቃ. 24፥50-53የሐዋ. 1፥9-11)
19 # የሐዋ. 1፥9-11። ጌታ ኢየሱስ ይህን ከተናገራቸው በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ። 20ከዚያም ደቀመዛሙርቱ ወጥተው፥ በየስፍራው ሁሉ ሰበኩ፤ ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበር፤ ትምህርታቸውንም ተከትለው በሚፈጸሙ ምልክቶች ቃሉን ያጸና ነበር።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in