YouVersion Logo
Search Icon

2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2

2
1ስለዚህ ዳግመኛ በጉብኝቴ እንዳላስቸግራችሁ ወደ እናንተ ላለመምጣት ቆረጥሁ። 2እኔስ ባሳዝናችሁ፥ እንግዲያስ በእኔ ምክንያት ከሚያዝን በቀር ደስ የሚያሰኘኝ ማን ነው? 3ደስታዬ የሁላችሁ ደስታ ነው ብዬ በሁላችሁ ስለምተማመን፥ ደስ ሊያሰኙኝ ወደሚገባቸው በመምጣቴ ማስቸገር እንዳይሆንብኝ ይህንኑ ጻፍኩላችሁ። 4በብዙ መከራና ከልብ ጭንቀት፥ በብዙም እንባ ጽፌላችሁ ነበር፤ ይህም እናንተን አብዝቼ የምወድበትን ፍቅር እንድታውቁ እንጂ እንዳሳዝናችሁ አይደለም።
ለበደለኛ ይቅርታ ስለ ማድረግ
5ነገር ግን ማንም ያሳዘነ ቢኖር፥ እኔን ብቻ ሳይሆን ያሳዘነው፥ ባላጋንነው በተወሰነ መልኩ፥ ሁላችሁንም ነው። 6እንደዚህ ላለ ሰው ይህ ከእናንተ በብዙሃኑ ስለተቀጣ በቂው ነው። 7ከልክ በላይ አዝኖ ተስፋ እንዳይቆርጥ ይቅር ልትሉትና ልታጽናኑት ይገባችኋል። 8ስለዚህ ከእርሱ ጋር ፍቅራችሁን መልሳችሁ እንድታጸኑ እለምናችኋለሁ። 9በሁሉ የምትታዘዙ እንደ ሆናችሁ የእናንተን መፈተን ለማወቅ በማሰብ፥ ስለዚህ ደግሞ ጽፌ ነበር። 10እናንተ ግን ይቅር የምትሉትን እኔም ይቅር እለዋለሁ፤ እኔም ይቅር ካልሁ፥ ይቅር ያልሁትን ስለ እናንተ በክርስቶስ ፊት ይቅር ብዬአለሁ፤ 11ይህን የምናደርገው በሰይጣን መበለጥ እንዳንችል ነው፤ ማናችንም የእርሱን አሳብ አንስተውም።
ስለ አዲስ ኪዳን አገልጋዮች
12 # የሐዋ. 20፥1። የክርስቶስን ወንጌል ለመስበክ ወደ ጢሮአዳ በመጣሁ ጊዜ፥ በጌታ በሩ ተከፍቶልኝ ነበር፤ 13ነገር ግን መንፈሴ ማረፍ አልቻለም፤ ምክንያቱም እዚያ ወንድሜን ቲቶን አላገኘሁትም። ስለዚህ ከእነርሱ ተሰናብቼ ወደ መቄዶንያ ወጣሁ።
14ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን፥ በእኛም በሁሉም ስፍራ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ፥ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። 15በሚድኑትና በሚጠፉት ዘንድ ለእግዚአብሔር የክርስቶስ መዓዛ ነን፤ 16ለእነዚህ ለሞት የሚሆን የሞት ሽታ፥ ለእነዚያም ለሕይወት የሚሆን የሕይወት ሽታ ነን። ለዚህም ነገር የሚበቃ ማን ነው? 17የእግዚአብሔርን ቃል ቀላቅለው እንደሚነግዱ እንደ ብዙዎቹ አይደለንም፤ በቅንነት ግን ከእግዚአብሔር እንደ ተላክን በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ ሆነን እንናገራለን።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Video for 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2