YouVersion Logo
Search Icon

2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3

3
1እንደገና ራሳችንን ልናመሰግን እንጀምራለንን? ወይስ አንዳንዶች እንደሚያደርጉት ለእናንተ ወይም ከእናንተ የተጻፈ የምስጋና ደብዳቤ ያስፈልገን ይሆንን? 2ሰዎች ሁሉ የሚያውቁትና የሚያነብቡት በልባችን የተጻፈ መልእክታችን እናንተ ናችሁ። 3#ዘፀ. 24፥12፤ ኤር. 31፥33፤ ሕዝ. 11፥19፤ 36፥26።እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም ያልሆነ፥ ሥጋ በሆነ በልብ ጽላት እንጂ በድንጋይ ጽላት ያልተጻፈ፥ በእኛም የተገለገለ፥ የክርስቶስ መልእክት እንደ ሆናችሁ የተገለጠ ነው።
4በክርስቶስም በኩል በእግዚአብሔር ያለን መተማመን ይህን ይመስላል። 5ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፥ በገዛ እጃችን የሚሆን አንዳችን ነገር ልናስብ እኛ የበቃን አይደለንም፤ 6#ኤር. 31፥31።እርሱም ደግሞ በመንፈስ እንጂ በፊደል ላልሆነ፥ ለአዲስ ኪዳን አገልጋዮች እንድንሆን አበቃን፤ ፊደል ይገድላል፤ መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል።
7 # ዘፀ. 34፥29። ዳሩ ግን የእስራኤል ልጆች ስለዚያ ስለ ተሻረው፥ ስለ ፊተኛው ክብር የሙሴን ፊት ትኩር ብለው መመልከት እስኪሳናቸው ድረስ፥ ያ በፊደላት በድንጋዮች ላይ የተቀረጸ የሞት አገልግሎት ያን ያህል ክቡር ከሆነ፥ 8የመንፈስ አገልግሎት እንዴት ልቆ የከበረ አይሆንም? 9የኩነኔ አገልግሎት በክብር ከሆነ፥ ይልቁን የጽድቅ አገልግሎት በክብር አብዝቶ ይበልጣል። 10በእርግጥ ያ ከብሮ የነበረው እንኳ እጅግ በሚበልጠው ክብር ምክንያት ክብሩን አጥቶአል። 11ያ ይሻር የነበረው በክብር ከደረሰ፥ ጸንቶ የሚኖረውማ እንዴት ልቆ እጅግ አይከብርም!
12እንግዲህ እንዲህ ያለ ተስፋ ካለን፥ አብዝተን በድፍረት እንናገራለን፤ 13#ዘፀ. 34፥33። ይሻር የነበረውን መጨረሻ ትኩር ብለው የእስራኤል ልጆች እንዳይመለከቱ፥ ፊቱን እንደ ጋረደው እንደ ሙሴ አይደለም። 14ብሉይ ኪዳን ሲነበብ ያ መጋረጃ ሳይወገድ እስከ ዛሬ ድረስ በመኖሩና፥ በክርስቶስ ብቻ የተሻረ ነውና፥ አሳባቸው ደነዘዘ። 15ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ የሙሴ መጻሕፍት በተነበቡ ቍጥር ያ መጋረጃ በልባቸው ይኖራል፤ 16#ዘፀ. 34፥34።ነገር ግን ሰው ወደ ጌታ ፊቱን ሲያዞር መጋረጃው ይወገዳል። 17ጌታ ግን መንፈስ ነው፤ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ። 18እኛም ሁላችን፥ በመጋረጃ በማይሸፈን ፊት፥ የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን፥ የእርሱን መልክ እንድንመስል ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን፥ ይህም መንፈስ ከሚሆን ጌታ የመጣ ነው።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Videos for 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3