መጽሐፈ መዝሙር 63
63
እግዚአብሔርን መፈለግ
1እግዚአብሔር ሆይ! አንተ አምላኬ ነህ፤
አንተን ለማግኘት በብርቱ እናፍቃለሁ፤
ሁለንተናዬ አንተን ይመኛል፤
ውሃ በማጣት ደርቆ እንደ ተሰነጣጠቀ መሬት
ነፍሴ አንተን ተጠማች።
2በመቅደስህ ውስጥ አንተን ተመለከትኩ፤
ኀይልህንና ክብርህንም አየሁ።
3ዘለዓለማዊው ፍቅርህ ከሕይወት እንኳ
የሚሻል ስለ ሆነ አመሰግንሃለሁ።
4በሕይወቴ ዘመን ሁሉ አመሰግንሃለሁ፤
ለጸሎትም እጆቼን ወደ አንተ እዘረጋለሁ።
5ሰው መልካም ምግብ በልቶ እንደሚጠግብ
ነፍሴ በአንተ ትረካለች፤
ስለዚህ የምስጋና መዝሙር በደስታ እዘምርልሃለሁ።
6በመኝታዬም ሆኜ አስታውስሃለሁ፤
ሌሊቱንም ሁሉ የአንተን ነገር አስባለሁ።
7አንተ ረዳት ስለ ሆንከኝ በጥበቃህ ሥር ተጠልዬ፥
በደስታ እዘምራለሁ።
8ወደ አንተ እጠጋለሁ፤
ቀኝ እጅህም ቀና አድርጎ ይደግፈኛል።
9እኔን ለመግደል የሚፈልጉ ሁሉ
ወደ ሙታን ዓለም ይወርዳሉ።
10በሰይፍ ይገደላሉ፤
ሬሳቸውንም ቀበሮዎች ይበሉታል።
11እግዚአብሔር ድልን ስለሚያጐናጽፈው
ንጉሡ ደስ ይለዋል፤
በእግዚአብሔር ስም የሚምሉ ሁሉ
እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ፤ የሐሰተኞች አንደበት ግን ይዘጋል። #1ሳሙ. 23፥14።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 63: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997