YouVersion Logo
Search Icon

መጽሐፈ መዝሙር 62

62
በእግዚአብሔር ጠባቂነት መተማመን
1የሚያድነኝ እርሱ ብቻ ስለ ሆነ፥
እግዚአብሔርን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ።
2ያለ እርሱ የሚጠብቀኝና የሚያድነኝ የለም፤
መከላከያዬም እርሱ ስለ ሆነ ከቶ አልናወጥም።
3እንደ አረጀ ግድግዳና እንደ ተነቃነቀ አጥር
ዐቅም ያነሰውን ሰው፥
ሁላችሁም በእርሱ ላይ አደጋ እየጣላችሁ።
እስከ መቼ ስታጠቁት ትኖራላችሁ?
4እነርሱ የሚፈልጉት ክብሩን ለመሻር ስለ ሆነ
በእርሱ ላይ ሐሰት መናገርን ይወዳሉ፤
በአፋቸው ይመርቁታል፤
በልባቸው ግን ይረግሙታል።
5እግዚአብሔርን ብቻ ጸጥ ብዬ እጠብቃለሁ፤
ተስፋዬም የሚመጣው ከእርሱ ነው።
6የሚያድነኝ ኀያል አምባዬ እግዚአብሔር ብቻ ነው፤
እርሱም እምነት የምጥልበት ምሽጌ ስለ ሆነ አልናወጥም።
7መዳኔና ክብሬ የተገኘው ከእግዚአብሔር ነው፤
እርሱ የመጠጊያዬ አምባና መጠለያዬ ነው።
8ሕዝቦች ሆይ! ዘወትር በእግዚአብሔር ታመኑ፤
እርሱ መጠጊያችን ስለ ሆነ
የልባችሁን ሐሳብ ሁሉ ለእርሱ አቅርቡ።
9ተራ ሰዎች እንደ አየር ናቸው፤
በከፍተኛ ደረጃ ላይ ያሉ ሰዎች ተጨባጭነት እንደሌለው ምኞት ናቸው፤
ሁለቱ በሚዛን ላይ ቢቀመጡ ከነፋስ ሽውታ ይቀላሉ።
10በብዝበዛ አትመኩ፤
በቀማችሁትም ነገር ለመክበር ተስፋ አታድርጉ፤
ሀብታችሁ ቢበዛ እንኳ በእርሱ አትተማመኑ።
11እግዚአብሔር አንድ ጊዜ ተናግሮአል፤
ኀይል የእግዚአብሔር መሆኑን ሁለት ጊዜ ሰምቼአለሁ።
12ጌታ ሆይ! ለሁሉም እንደየሥራው ስለምትከፍል
ዘለዓለማዊ ፍቅር ያንተ ነው። #ኢዮብ 34፥11፤ ኤር. 17፥10፤ ማቴ. 16፥27፤ ሮም 2፥6፤ ራዕ. 2፥23።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in