መጽሐፈ መዝሙር 17
17
1እግዚአብሔር ሆይ!
ትክክለኛ ፍርድ ለማግኘት የማቀርብልህን ጸሎት ስማ፤
ጩኸቴንም አድምጥ፤
በሽንገላ ሳይሆን በእውነት የማቀርበውን
ጸሎት ስማ።
2ዐይኖችህ እውነትን ማየት ስለሚችሉ
አንተ ብቻ ልትፈርድልኝ ትችላለህ።
3ልቤን ብትመረምር፥ በሌሊት ብትጐበኘኝ፥
ብትፈትነኝም፥ ከእኔ ክፋትን አታገኝም፤
አንደበቴም አይስትም።
4የሰዎችን ሥራ በሚመለከት፥
አንተ በተናገርከው ቃል መሠረት፥
እኔ ከዐመፀኞች አካሄድ
ራሴን ጠብቄአለሁ።
5ዘወትር በመንገድህ ተራመድኩ፤
ከመንገድህም ወጥቼ አልባዘንኩም።
6አምላክ ሆይ!
ልመናዬን ስለምትሰማ፥
ወደ አንተ እጸልያለሁ፤
ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤
ቃሌንም ስማ።
7የአንተን ከለላ ለሚፈልጉ፥ በቀኝ እጅህ የምታድናቸው አምላክ ሆይ!
ዘለዓለማዊ ፍቅርህን በአስደናቂ ሁኔታ ግለጥ።
8የዐይን ብሌን በጥንቃቄ የሚጠበቀውን ያኽል ጠብቀኝ፤
በጥበቃህ ውስጥ ሰውረኝ።
9ከበባ አድርገው ከሚያጠፉኝ
ጨካኝ ጠላቶቼ ጠብቀኝ።
10እነርሱ ለርኅራኄ ልባቸውን ዘግተዋል፤
አፋቸውም ትዕቢትን ይናገራል።
11ጠላቶቼ አስጨነቁኝ፤ ከበባም አደረጉብኝ፤
ወደ መሬት ሊጥሉኝም ዐይናቸውን ጣሉብኝ።
12እነርሱ እንደ ተራቡ አንበሶች
ወይም እንደ ሸመቁ ደቦል አንበሶች ናቸው።
13እግዚአብሔር ሆይ! ተነሥና ጣላቸው፤
በሰይፍህም ሕይወቴን ከክፉዎች አድን።
14እግዚአብሔር ሆይ! የሕይወታቸው ድርሻ የዚህ ዓለም ነገር
ብቻ ከሆነ ሰዎች በእጅህ አድነኝ፤
ለምትወዳቸው ምግብን ስጣቸው፤
ልጆቻቸው ብዙ ይኑራቸው፤
የልጅ ልጆቻቸውም የተትረፈረፈ ምግብ እንዲኖራቸው አድርግ።
15እኔ በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፤
በምነቃበት ጊዜም የአንተን አምሳያ በማየቴ እደሰታለሁ።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 17: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997