መጽሐፈ መዝሙር 114
114
እስራኤል ከግብጽ የወጡበት የፋሲካ መታሰቢያ መዝሙር
1የያዕቆብ ዘሮች የሆኑት የእስራኤል ሕዝብ
ከግብጽ በመውጣት የባዕድን አገር በለቀቁ ጊዜ #ዘፀ. 12፥51።
2ይሁዳ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ሆነ፤
እስራኤልም የእግዚአብሔር ርስት ሆነ።
3ባሕር ይህን አይቶ ሸሸ፤
የዮርዳኖስም ወንዝ ውሃ ማፍሰሱን አቁሞ
ወደ ኋላው ተመለሰ። #ዘፀ. 14፥21፤ ኢያሱ 3፥16።
4ተራራዎች እንደ አውራ በጎች ፈነጩ፤
ኰረብቶችም እንደ በግ ግልገል በየቦታው ዘለሉ።
5አንተ ባሕር፥ ምን ሆነህ ሸሸህ?
አንተስ ዮርዳኖስ፥ ስለምን መፍሰስህን አቁመህ ወደ ኋላህ ተመለስህ?
6እናንተ ተራራዎች፥ ስለምን እንደ አውራ በጎች ፈነጫችሁ?
እናንተስ ኰረብቶች፥ ስለምን እንደ በግ ግልገል በየቦታው ዘለላችሁ?
7ምድር ሆይ!
በእግዚአብሔር ፊት፥ በያዕቆብም አምላክ ፊት
በፍርሃት ተንቀጥቀጪ።
8እርሱ አለቱን ወደ ኩሬ ውሃ፥
ጭንጫውንም ሸንተረር ወደ ወራጅ ምንጭ ይለውጣል። #ዘፀ. 17፥1-7፤ ዘኍ. 20፥2-13።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 114: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997