YouVersion Logo
Search Icon

መጽሐፈ መዝሙር 115

115
ለእግዚአብሔር የሚገባ ምስጋና
1እግዚአብሔር ሆይ!
ስለ እኛ ሳይሆን
ስለ ዘለዓለማዊው ፍቅርህና ስለ ታማኝነትህ
ስምህን አክብረው።
2ስለምን አሕዛብ
“አምላካቸው የት አለ?” ይበሉ?
3አምላካችን በሰማይ ነው፤
እርሱ የፈቀደውን ሁሉ ያደርጋል።
4እነርሱ የሚያመልኩአቸው ጣዖቶች ግን በሰው እጅ
ከብርና ከወርቅ የተሠሩ ናቸው።
5አፍ አላቸው፤ አይናገሩም፤
ዐይን አላቸው፤ አያዩም፤
6ጆሮ አላቸው፤ አይሰሙም፤
አፍንጫ አላቸው፤ አያሸቱም፤
7እጅ አላቸው፤ አይዳስሱም፤
እግር አላቸው፤ አይሄዱም፤
ድምፅም ማሰማት አይችሉም።
8የሠሩአቸውና የሚታመኑባቸው ሁሉ
እንደነዚህ ጣዖቶች ናቸው። #መዝ. 135፥15-18፤ ራዕ. 9፥20።
9እናንተ የእስራኤል ሕዝብ ግን
የሚረዳችሁና የሚጠብቃችሁ እግዚአብሔር ስለ ሆነ
በእርሱ ታመኑ።
10እናንተ የእግዚአብሔር ካህናት የአሮን ልጆች
የሚረዳችሁና የሚጠብቃችሁ እርሱ ስለ ሆነ
በእግዚአብሔር ታመኑ።
11እናንተ የምትፈሩት ሁሉ
የሚረዳችሁና የሚጠብቃችሁ እርሱ ስለ ሆነ
በእግዚአብሔር ታመኑ።
12እግዚአብሔር ያስታውሰናል፤ ደግሞም ይባርከናል፤
የእስራኤልን ሕዝብና የእግዚአብሔርን ካህናት
ሁሉ ይባርካል።
13የሚፈሩትን ሁሉ፥
ታላላቆችንም ሆነ ታናናሾችን ይባርካል። #ራዕ. 11፥18፤ 19፥5።
14እግዚአብሔር እናንተና ልጆቻችሁ
እንድትበዙ ያድርጋችሁ!
15ሰማይንና ምድርን የፈጠረ
እግዚአብሔር ይባርካችሁ!
16ሰማይ የእግዚአብሔር ነው፤
ምድርን ግን ለሰው ልጆች ሰጥቶአል።
17ወደ ዝምታ ዓለም፥ ወደ መቃብር የወረዱ ሙታን
እግዚአብሔርን ሊያመሰግኑት አይችሉም።
18እኛ ግን በሕይወት ያለነው
ከአሁኑ ጊዜ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም እናመሰግነዋለን።
እግዚአብሔር ይመስገን!

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in