YouVersion Logo
Search Icon

መጽሐፈ ነህምያ መግቢያ

መግቢያ
መጽሐፈ ነህምያ በሦስት ሊከፈል ይችላል፦
1. ይሁዳን እንዲያስተዳድር በፋርስ ንጉሠ ነገሥት በተላከው በነህምያ መሪነት የኢየሩሳሌም ቅጽሮች መታደሳቸውን የሚያስረዳው ታሪክ ነው፤ ከዚህም በቀር ነህምያ ሥጋዊና ሃይማኖታዊ ተሐድሶዎችንም አካሂዶአል።
2. የእግዚአብሔር ሕግ መጽሐፍ በዕዝራ ስለ መነበቡና ሕዝቡ ኃጢአታቸውን ስለ መናዘዛቸው የሚናገረው ክፍል ነው።
3. ነህምያ የይሁዳ አገረ ገዢ ሆኖ ስላካሄዳቸው ሌሎች ተግባሮች የሚገልጠው ክፍል ነው።
በመጽሐፉ ውስጥ ጐላ ብሎ የሚታየው ነገር ነህምያ በእግዚአብሔር ላይ ስለ ነበረው ጽኑ መታመንና ወደ እግዚአብሔርም ስላቀረባቸው ጸሎቶች የሚያወሳው ታሪክ ነው።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
ንጉሥ አርጤክስስ ነህምያን ወደ ኢየሩሳሌም መላኩ (1፥1—2፥10)
የኢየሩሳሌም ግንብ እንደገና መገንባቱ (2፥11—4፥22)
ነህምያ ስለ ድኾች ማሰቡ (5፥1-19)
የጠላት አድማም እያለ የግንቡ ሥራ ማለቁ (6፥1—7፥3)
የምርኮ ተመላሾች (7፥4-73)
ዕዝራ የእግዚአብሔርን ሕግ ለሕዝቡ ማንበቡ፥ የዳስ በዓልን ማክበራቸው (8፥1-18)
ሕዝቡ ኃጢአቱን መናዘዙ (9፥1-37)
ለእግዚአብሔር ሕግ ለመታዘዝ የስምምነት ውል መፈረማቸው (9፥38—10፥39)
በይሁዳና በየሩሳሌም የሰፈሩ ሰዎች (11፥1-36)
ከምርኮ የተመለሱ ካህናትና ሌዋውያን (12፥1-26)
ነህምያ የከተማውን ግንብ ማስመረቁ (12፥27-47)
ነህምያ ያደረገው ለውጥ (13፥1-31)

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in