YouVersion Logo
Search Icon

መጽሐፈ ነህምያ 3

3
የኢየሩሳሌም ቅጽር እንደገና መሠራቱ
1የከተማይቱ ቅጽር እንደገና የተሠራው በዚህ ዐይነት ነበር፦ ሊቀ ካህናቱ ኤልያሺብና የእርሱ ሥራ ባልደረቦች የሆኑት ካህናት “የበጎች በር” ተብሎ የሚጠራውን ቅጽር በር እንደገና ሠርተው ለእግዚአብሔር የተለየ አደረጉት፤ በሮችንም አበጁለት፤ ቅጽሩንም “መቶ” ተብሎ እስከሚጠራው የመጠበቂያ ግንብና “ሐናንኤል” ተብሎ እስከሚጠራው ሌላ የመጠበቂያ ግንብ ድረስ ለእግዚአብሔር የተለየ አደረጉት።
2የኢያሪኮ ሰዎች የዚያን ተከታይ ክፍል ሲሠሩ፥ ዘኩር የተባለው የኢምሪ ልጅ ከዚያ ቀጥሎ የሚገኘውን ክፍል ሠራ።
3የሃስናአ ጐሣ አባሎች የዓሣ ቅጽር በር የተባለውን ሠሩ፤ ምሰሶዎችንም አቆሙለት፤ በሮችንም ገጠሙ፤ ለበሮቹም መዝጊያ፥ መወርወሪያና ቊልፎችን አበጁ።
4የሀቆጽ የልጅ ልጅ የሆነው የኡሪያ ልጅ መሬሞት ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠራ። (አደሰ ቢሆን ይመረጣል)
የመሼዛቤል የልጅ ልጅ የሆነው የበራክያ ልጅ መሹላም ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠራ፤ ከዚያም ቀጥሎ የሚገኘውን ክፍል የበዓና ልጅ ሳዶቅ ሠራው። (አደሰ ቢሆን ይመረጣል)
5የተቆዓ ከተማ ሰዎች ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠሩ፤ ነገር ግን የከተማይቱ ሹማምንት በተቈጣጣሪዎች የተመደበላቸውን የጒልበት ሥራ መሥራትን እምቢ አሉ።
6የፓሴሕ ልጅ ዮዳሄ፥ የበሶድያ ልጅ መሹላም የይሻናን ቅጽር በር ሠሩ፤ ምሰሶዎችንም አቆሙለት፤ በሮችንም ገጠሙ፤ ለበሮቹም ቊልፎችንና መወርወሪያዎችን አበጁ።
7የገባዖን ተወላጅ የሆነው መላጥያ፥ የሜሮኖት ተወላጅ የሆነው ያዶንና የገባዖንና የምጽጳ ሰዎች የኤፍራጥስ ምዕራብ አገረ ገዢ እስከሚኖርበት ቤት ድረስ ያለውን ክፍል ሠሩ።
8ወርቅ አንጣሪው የሐርሃያ ልጅ ዑዝኤል ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠራ።
ቀጥሎ ያለውንም ክፍል ሽቶ ቀማሚው ሐናንያ ሠራ፤ እነዚህ ሰዎች ኢየሩሳሌምን “ሰፊው ቅጽር” ተብሎ እስከሚጠራው ስፍራ ድረስ ያለውን ሁሉ ሠሩ።
9ከእነርሱም ቀጥሎ ያለውን ክፍል የኢየሩሳሌም ወረዳ እኩሌታ ገዢ የሆነው የሑር ልጅ ረፋያ ሠራ።
10የሐሩማፍ ልጅ የዳያ ከቤቱ ፊት ለፊት የሚገኘውን ክፍል ሠራ።
ቀጥሎ ያለውንም ክፍል የሐሻበንያ ልጅ ሐቱሽ ሠራው።
11የሓሪም ልጅ ማልኪያና የፓሐትሞአብ ልጅ ሐሹብ ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍልና “የእቶን ግንብ” ተብሎ የሚጠራውን ግንብ ሠሩ።
12ቀጥሎ ያለውንም ክፍል የሌላው የኢየሩሳሌም ወረዳ እኩሌታ ገዢ የሆነው የሀሎሔሽ ልጅ ሻሉም ሠራ፤ ሴቶች ልጆቹም ሥራውን ይረዱት ነበር።
13ሐኑንና የዛኖሐ ነዋሪዎች ተባብረው የሸለቆውን ቅጽር በር በማደስ ሠሩ፤ ለቅጽር በሩም መዝጊያዎችን አቁመው ቊልፎችንና መወርወሪያዎችን አበጁለት፤ እስከ ጒድፍ መጣያ ቅጽር በር 440 ሜትር ርዝመት ያለውንም ቅጽር እንደገና ሠሩ።
14የቤትሀካሬም ወረዳ ገዢ የሆነው የሬካብ ልጅ ማልኪያ የጒድፍ መጣያውን ቅጽር በር በማደስ ሠራ፤ በሮችን ገጠመ፤ ለበሮቹም ቊልፎችንና መወርወሪያዎችን አበጀ።
15የምጽጳ ወረዳ ገዢ የሆነው የኮልሖዜ ልጅ ሻሉም የምንጩን ቅጽር በር እንደገና ሠራ፤ ክዳን ከሠራለትም በኋላ መዝጊያዎችን አቆመ፤ ለበሮቹም ቊልፎችንና መወርወሪያዎችን አበጀ፤ በሼላሕ ኩሬ ቅጥር በኩል ከቤተ መንግሥቱ የአትክልት ቦታ ጀምሮ ከዳዊት ከተማ ወደታች እስከሚያወርደው ደረጃ ድረስ ያለውን ክፍል እንደገና ሠራ።
16የቤትጹር አውራጃ እኩሌታ ገዢ የነበረው የዓዝቡቅ ልጅ ነህምያ እስከ ዳዊት መቃብር (ከዳዊት መቃብር ትይዩ ጀምሮ)፥ እስከ ኩሬ፤ እስከ ጀግኖች ሰፈር ድረስ ያለውን ክፍል ሠራ።
በቅጽሩ ሥራ ላይ ተካፋዮች የነበሩት ሌዋውያን
17በቅጽሩ ሥራ ተካፋዮች የነበሩት ሌዋውያን ስም ዝርዝር ከዚህ የሚከተለው ነው፦
የባኒ ልጅ ረሑም ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠራ።
የቀዒላ ወረዳ እኩሌታ ገዢ የሆነው ሐሻብያ ወረዳውን በመወከል ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠራ።
18ከዚያም ቀጥሎ ያለውን ክፍል የሌላው የቀዒላ ወረዳ እኩሌታ ገዢ የሆነው የሔናዳድ ልጅ ባዋይ ሠራው።
19የምጽጳ ወረዳ ገዥ የሆነው የኢያሱ ልጅ ዔዜር በጦር መሣሪያው ግምጃ ቤት ፊት ለፊት ያለውን እስከ ቅጽሩ መመለሻ ማእዘን ድረስ ያለውን ሁሉ ሠራ።
20የዛባይ ልጅ ባሩክም እስከ ሊቀ ካህናቱ ኤልያሺብ ቤት መግቢያ በር ድረስ ያለውን ሠራ።
21የሀቆጽ የልጅ ልጅ የሆነው የኡሪያ ልጅ መሬሞት እስከ ኤልያሺብ ቤት መጨረሻ ያለውን ሠራ።
በቅጽሩ ሥራ ላይ ተካፋዮች የነበሩት ካህናት
22ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ቅጽር የሠሩ ካህናት ስም ዝርዝር ይህ ነው፦
በኢየሩሳሌም ዙሪያ የነበሩት ካህናት ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠሩ።
23ከእነርሱም ቀጥሎ ብንያምና ሐሹብ በመኖሪያ ቤቶቻቸው ፊት ለፊት ያለውን ክፍል ሠሩ።
የዐናኒያ የልጅ ልጅ የሆነውም የመዕሤያ ልጅ ዐዛርያ በራሱ መኖሪያ ቤት አጠገብ ያለውን ክፍል ሠራ።
24የሔናዳድ ልጅ ቢኑይ ከዐዛርያ ቤት አንሥቶ እስከ ቅጽሩ ማእዘን ያለውን ሠራ።
25-26የዑዛይ ልጅ ፓላል ከቅጽሩ ማእዘንና በዘብ መጠበቂያው አደባባይ አጠገብ ከሚገኘው ከላይኛው ቤተ መንግሥት መጠበቂያ ግንብ ጀምሮ ያለውን ክፍል ሁሉ ሠራ።
የፓርዖሽ ልጅ ፐዳያ ደግሞ በውሃው ቅጽር በር አጠገብ ወደምሥራቅ የሚያመለክተውን ስፍራና የቤተ መቅደሱን መጠበቂያ ግንብ ይኸውም የቤተ መቅደሱ ሠራተኞች በሚኖሩበት የከተማይቱ አንድ ክፍል በሆነው “ዖፌል” ተብሎ በሚጠራው ስፍራ አጠገብ ያለውን ክፍል ሠራ።
በሥራው ተሳታፊ የሆኑ ሌሎች ሠራተኞች
27የተቆዓ ሰዎችም ከዚያ ቀጥለው ለሁለተኛ ጊዜ ለቤተ መቅደሱ መጠበቂያ ከተሠራው ከታላቁ ግንብ ፊት ለፊት ጀምሮ በዖፌል አጠገብ እስከሚገኘው ቅጽር ያለውን ሠሩ።
28ሌሎች ካህናትም እያንዳንዳቸው በየመኖሪያ ቤታቸው ፊት ለፊት ያለውን መስመር በመከተል ከፈረስ ቅጽር በር በስተሰሜን በኩል ያለውን ክፍል ሠሩ።
29የኢሜር ልጅ ሳዶቅ በመኖሪያ ቤቱ ፊት ለፊት ያለውን ሲሠራ የምሥራቅ ቅጽር በር ጠባቂው የሸካንያ ልጅ ሸማዕያ ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ሠራ።
30የሼሌምያ ልጅ ሐናንያና የጻላፍ ስድስተኛ ልጅ ሐኑን ለሁለተኛ ጊዜ የተሰጣቸውን ድርሻ ሠሩ።
የበራክያ ልጅ መሹላምም በመኖሪያ ቤቱ ፊት ለፊት በኩል ያለውን ሠራ።
31ወርቅ አንጥረኛው ማልኪያ ተከታዩን መስመር ከቅጽሩ ማእዘን ሰሜናዊ ምሥራቅ ጫፍ አጠገብ እስካለው መቈጣጠሪያ ቅጽር በር በኩል የቤተ መቅደሱ ሠራተኞችና ነጋዴዎች እስከሚገለገሉበት ስፍራ ድረስ ሠራ።
32ወርቅ አንጥረኞችና ነጋዴዎችም ከቅጽሩ ማእዘን ጀምሮ እስከ በጎች ቅጽር በር ያለውን የመጨረሻውን ክፍል ሠሩ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Videos for መጽሐፈ ነህምያ 3