YouVersion Logo
Search Icon

የሉቃስ ወንጌል መግቢያ

መግቢያ
የሉቃስ ወንጌል ኢየሱስን የሚያቀርበው ቀደም ብሎ ይመጣል ተብሎ በነቢያት የተነገረለት ከብዙ ዘመንም የተስፋው ባለቤት የሆነው የእስራኤል ሕዝብ ሲጠባበቀው የነበረው “መሲሕ” እንዲሁም የሰው ዘር ሁሉ “አዳኝ” መሆኑን በመግለጥ ነው። ሉቃስ፥ ኢየሱስን “ለድኾች ወንጌልን እንዲሰብክ” ከአባቱ የተላከ መሆኑንና ይህም ወንጌል ሰዎች ላለባቸው ልዩ ልዩ ችግር መፍትሔ የያዘ መሆኑን ይተርካል። በሉቃስ ወንጌል ውስጥ በተለይም ስለ ኢየሱስ መምጣት በሚያበሥሩት በመጀመሪያዎቹ ምዕራፎችና እንደገናም ስለ ኢየሱስ ወደ ሰማይ ማረግ በሚናገሩት በመጨረሻዎቹ ምዕራፎች ጐልቶ የተነገረው ስለ ደስታ ነው። ከኢየሱስ ወደ ሰማይ ማረግ በኋላ የክርስትና እምነት እንዴት እንዳደገና እንደ ተስፋፋ የሚያስረዳው ታሪክ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ በዚሁ ጸሐፊ ተነግሮአል።
ስለ መላእክት ዝማሬ፥ ኢየሱስ በተወለደ ጊዜ እረኞች እንደ ጐበኙት የሚናገረው ታሪክ፥ ኢየሱስ በልጅነቱ ወደ ቤተ መቅደስ ስለ መሄዱ፥ የርኅሩኍ ሳምራዊና ጠፍቶ የተገኘው ልጅ ታሪክ በሉቃስ ወንጌል ብቻ የሚገኙ ናቸው። በወንጌሉ ውስጥ ከዳር እስከ ዳር ታላቅ ትኲረት የተደረገው ስለ ጸሎት፥ ስለ መንፈስ ቅዱስ፥ ሴቶች በኢየሱስ አገልግሎት ውስጥ ስላላቸው ስፍራና እግዚአብሔር ኃጢአትን ይቅር ስለ ማለቱ ነው።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መግቢያ 1፥1-4
የመጥምቁ ዮሐንስና የኢየሱስ መወለድ 1፥5—2፥52
የዮሐንስ መጥምቁ አገልግሎት 3፥1-20
የኢየሱስ መጠመቅና መፈተን 3፥21—4፥13
ኢየሱስ አገልግሎቱን በገሊላ መጀመሩ 4፥14—9፥50
ከገሊላ ወደ ኢየሩሳሌም 9፥51—19፥27
የመጨረሻው ሳምንት በኢየሩሳሌምና በአካባቢዋ 19፥28—23፥56
የጌታ ትንሣኤ መገለጥና ዕርገቱ 24፥1-53

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in