YouVersion Logo
Search Icon

መጽሐፈ ዕዝራ 2

2
ከምርኮ ወደ ሀገራቸው የተመለሱት ሰዎች ዝርዝር
(ነህ. 7፥4-73)
1የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ማርኮ ወደ ባቢሎን ከወሰዳቸው ሰዎች መካከል ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደየከተማቸውም የተመለሱት እነዚህ ናቸው። 2ለተመለሱትም ስደተኞች መሪዎች ሆነው የመጡት ዘሩባቤል፥ ኢያሱ፥ ነህምያ፥ ሠራያ፥ ረዔላያ፥ መርዶክዮስ፥ ቢልሻን፥ ሚስፓር፥ ቢግዋይ፥ ሬሁምና በዓና ተብለው የሚጠሩት ነበሩ። ከእያንዳንዱ እስራኤላዊ ጐሣ በመሰባሰብ ወደ ሀገር የተመለሱትም ስደተኞች ዝርዝር ከዚህ የሚከተለው ነው፦
3-20ከፓርዖሽ ወገን 2172
ከሸፋጥያ ወገን 372
ከአራሕ ወገን 775
ከፓሐትሞአብ ወገን የኢያሱና የኢዮአብ ዘሮች 2812
ከዔላም ወገን 1254
ከዛቱ ወገን 945
ከዛካይ ወገን 760
ከባኒ ወገን 642
ከቤባይ ወገን 623
ከዓዝጋድ ወገን 1222
ከአዶኒቃም ወገን 666
ከቢግዋይ ወገን 2056
ከዓዲን ወገን 454
በሕዝቅያስ በኩል ከአጤር ወገን 98
ከቤጻይ ወገን 323
ከዮራ ወገን 112
ከሐሹም ወገን 223
ከጊባር ወገን 95
21-35ከምርኮ ከተመለሱትም ሰዎች መካከል በተለይ የቀድሞ አባቶቻቸው ከዚህ በሚከተሉት ከተሞች ይኖሩ የነበሩት ዝርዝር ይህ ነው፦
የቤተልሔም ተወላጆች 123
የነጦፋ ተወላጆች 56
የዐናቶት ተወላጆች 128
የዓዝማዌት ተወላጆች 42
የቂርያትይዓሪም፥ የከፊራና የበኤሮት ተወላጆች 743
የራማና የጌባዕ ተወላጆች 621
የሚክማስ ተወላጆች 122
የቤትኤልና የዐይ ተወላጆች 223
የነቦ ተወላጆች 52
የማግቢሽ ተወላጆች 156
የሌላይቱ ዔላም ተወላጆች 1254
የሓሪም ተወላጆች 320
የሎድ፥ የሐዲድና የኦኖ ተወላጆች 725
የኢያሪኮ ተወላጆች 345
የሰናአ ተወላጆች 3630
36-39ከዚህ የሚከተለው ደግሞ ከምርኮ የተመለሱ የካህናት ቤተሰብ ዝርዝር ነው፦
የኢያሱ ዘር የሆነው የይዳዕያ ቤተሰብ 973
የኢሜር ቤተሰብ 1052
የፓሽሑር ቤተሰብ 1247
የሓሪም ቤተሰብ 1017
40-42ከምርኮ የተመለሱት የሌዋውያን ቤተሰቦች ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፦
የሆዳውያ ዘሮች የሆኑት የኢያሱና የቃድሚኤል ቤተሰቦች 74
የአሳፍ ዘሮች የሆኑት የቤተ መቅደስ መዘምራን ብዛት 128
የቤተ መቅደስ ዘብ ጠባቂዎች የሆኑት የሻሉም፥ የአጤር፥ የጣልሞን፥ የዓቁብ፥ የሐጢጣና የሾባይ ዘሮች 139
43-54ለቤተ መቅደስ ሥራ ከተመደቡትም መካከል ከምርኮ የተመለሱት ጐሣዎች የሚከተሉት ናቸው፦
ጺሐ፥ ሐሱፋ፥ ጣባዖት፥
ቄሮስ፥ ሲዓሃ፥ ፋዶን፥
ለባና፥ ሐጋባ፥ ዓቁብ፥
ሐጋብ፥ ሻምላይ፥ ሐናን፥
ጊዴል፥ ጋሐር፥ ረአያ፥
ረጺን፥ ነቆዳ፥ ጋዛም፥
ዑዛ፥ ፓሴሐ፥ ቤሳይ፥
አስና፥ መዑኒም፥ ነፊሲም፥
ባቅቡቅ፥ ሐቁፋ፥ ሐርሑር፥
ባጽሉት፥ መሒዳ፥ ሐርሻ፥
ባርቆስ፥ ሲሣራ ቴማሕ፥
ነጺሐና ሐጢፋ።
55-57ከሰሎሞን አገልጋዮችም ወገን ከምርኮ የተመለሱት ጐሣዎች፥
ሶጣይ፥ ሀሶፌሬት፥ ፐሩዳ፥
ያዕላ፥ ዳርቆን፥ ጊዴል፥
ሸፋጥያ፥ ሐጢል፥ ፖኬሬት፥
ሐጸባይምና አሚ ተብለው የሚጠሩ ናቸው።
58ለቤተ መቅደስ ሥራ የተመደቡት ወገኖችና የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች ጠቅላላ ድምር 392 ነበር።
59-60ቴልሜላሕ፥ ቴልሐርሻ፥ ከሩብ፥ አዳንና ኢሜር ተብለው ከሚጠሩት ከተሞች ከምርኮ የተመለሱ ነበሩ፤ ነገር ግን የእነርሱ ዘር ከእስራኤል ወገን መሆኑን ሊያስረዱ አልቻሉም። የደላያ፥ የጦቢያና የነቆዳ ጐሣዎች ወገኖችም 652 ነበሩ፤
61-62ከዚህ የሚከተሉት የካህናት ጐሣዎች ሐባያ፥ ሀቆጽና ባርዚላይ የቀድሞ አባቶች እነማን እንደ ነበሩ ካለማወቃቸውም የተነሣ ካህናት ሆነው ለማገልገል ተቀባይነት አላገኙም። (ባርዚላይ ከገለዓዳዊው የባርዚላይ ልጆች አንድዋን አግብቶ በዚሁ ስም ይጠራ ነበር)። 63በኡሪምና በቱሚም የእግዚአብሔርን ፈቃድ መጠየቅ የሚችል ካህን እስከሚነሣም ድረስ እነርሱ የተቀደሰውን ምግብ መብላት እንደማይችሉ ገዢው አዘዛቸው። #ዘኍ. 29፥12-38።
64-67በዚህም ሁኔታ ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች ጠቅላላ ብዛት 42360 ነበር።
የእነርሱም ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮች ብዛት 7337 ሲሆን፥ የወንዶችና ሴቶች መዘምራን ድምር 200 ነበር።
ምርኮኞቹም፦ 736 ፈረሶች፥ 245 በቅሎዎች፥ 435 ግመሎችና 6720 አህዮች ነበሩአቸው።
68እነዚህም ምርኮኞች ተመልሰው በኢየሩሳሌም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ወደነበረበት ስፍራ በደረሱ ጊዜ አንዳንድ የቤተሰብ መሪዎች ቀድሞ በነበረበት ቦታ ቤተ መቅደሱን እንደገና መልሶ ለመሥራት ይረዳ ዘንድ በበጎ ፈቃድ የሚቀርብ የመባ ስጦታ አበረከቱ። 69እነርሱም ለቤተ መቅደሱ ሥራ ማከናወኛ የሚችሉትን ያኽል አዋጥተው ያቀረቡት ስጦታ ሲደመር አምስት መቶ ኪሎ ወርቅ፥ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ሰማኒያ ስድስት ኪሎ ብር ሆነ፤ ለካህናቱም የሚሆን አንድ መቶ የካህናት ልብስ ሰጡ።
70ካህናቱ፥ ሌዋውያኑና ከሕዝቡም አንዳንዱ በኢየሩሳሌም ወይም በአቅራቢያዋ ሰፈሩ፤ መዘምራኑ፥ የቤተ መቅደስ ዘብ ጠባቂዎችና ለቤተ መቅደሱ ሕንጻ የተመደቡት ሠራተኞች በየአቅራቢያው በሚገኙት ከተሞች ሰፈሩ፤ እንዲሁም የቀሩት እስራኤላውያን የቀድሞ አባቶቻቸው በነበሩባቸው ከተሞች ሰፈሩ። #1ዜ.መ. 9፥2፤ ነህ. 11፥3።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in