YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙር 61

61
መዝሙር 61
ለመዘምራን አለቃ፤ በበገናዎች የሚዘመር፤ የዳዊት መዝሙር።
1እግዚአብሔር ሆይ፤ ጩኸቴን ስማ፤
ጸሎቴንም አድምጥ።
2ልቤ በዛለ ጊዜ፣
ከምድር ዳርቻ ወደ አንተ እጣራለሁ፤
ከእኔ ይልቅ ከፍ ወዳለው ዐለት ምራኝ።
3አንተ መጠጊያዬ፣
ከጠላትም የምተገንብህ ጽኑ ግንብ ሆነኸኛልና።
4በድንኳንህ ለዘላለም ልኑር፤
በክንፎችህም ጥላ ልከለል። ሴላ
5አምላክ ሆይ፤ ስእለቴን ሰምተሃልና፤
ስምህን የሚፈሩትንም ሰዎች ርስት ለእኔ ሰጠህ።
6የንጉሡን ዕድሜ አርዝምለት፤
ዘመኑንም እስከ ብዙ ትውልድ ጨምርለት፤
7በእግዚአብሔር ፊት ለዘላለም ይንገሥ፤
ይጠብቁት ዘንድ ምሕረትህንና ታማኝነትህን አዘጋጅለት።
8ስለዚህ ለስምህ ዘወትር ውዳሴ አቀርባለሁ፤
ስእለቴንም በየጊዜው እፈጽማለሁ።

Currently Selected:

መዝሙር 61: NASV

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in