መዝሙር 17
17
መዝሙር 17
የንጹሕ ሰው አቤቱታ
የዳዊት ጸሎት።
1 እግዚአብሔር ሆይ፤ በቅንነት የቀረበውን አቤቱታዬን ስማ፤
ጩኸቴንም አድምጥ፤
ከአታላይ ከንፈር ያልወጣውን፣
ጸሎቴን አድምጥ።
2ጽድቄ ከአንተ ዘንድ ይምጣ፤
ዐይኖችህም ፍትሕን ይዩ።
3ልቤን መረመርኸው፣ በሌሊት ጠጋ
ብለህ ፈተንኸኝ፤
ፈተሽኸኝ አንዳች አላገኘህብኝም፤
አንደበቴም ዕላፊ አልሄደም።
4ከሰዎች ተግባር፣
በከንፈርህ ቃል፣
ከዐመፀኞች መንገድ፣
ራሴን ጠብቄአለሁ።
5አረማመዴ በመንገድህ ጸንቷል
እግሮቼም አልተንሸራተቱም።
6አምላክ ሆይ፤ ስለምትመልስልኝ አንተን እጣራለሁ፤
ጆሮህን ወደ እኔ ጣል አድርገህ ጸሎቴን ስማ።
7ከጠላቶቻቸው መተገኛ ያደረጉህን፣
በቀኝ እጅህ የምትታደግ ሆይ፤
ጽኑ ፍቅርህን ድንቅ አድርገህ ግለጥ።
8እንደ ዐይንህ ብሌን ጠብቀኝ፤
በክንፎችህም ጥላ ሰውረኝ፤
9ከሚያስጨንቁኝ ከክፉዎች፣
ከሚከብቡኝ አደገኛ ባላንጣዎቼ ጋርደኝ።
10ደንዳና ልባቸውን ደፈኑት፤
በአፋቸውም ትዕቢት ይናገራሉ።
11አሳድደው ደረሱብኝ፤ ከበቡኝም፤
መሬት ላይ ሊዘርሩኝም አፈጠጡብኝ።
12እነርሱ ለንጥቂያ እንደሚጓጓ አንበሳ፣
በስውርም እንደሚያደባ ደቦል አንበሳ ናቸው።
13 እግዚአብሔር ሆይ፤ ተነሥተህ ግጠማቸውና ጣላቸው፤
በሰይፍህም ከክፉዎች ታደገኝ።
14 እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዲህ ካሉት ሰዎች በክንድህ አድነኝ፤
ዕድል ፈንታቸው ይህችው ሕይወት ብቻ ከሆነች፣ ከዚህ ዓለም ሰዎች ታደገኝ።
ከመዝገብህ ሆዳቸውን ሞላህ፤
ልጆቻቸውም ተትረፍርፎላቸዋል፤
ለልጆቻቸውም ሀብት ያከማቻሉ።
15እኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፤
ስነቃም ክብርህን አይቼ እረካለሁ።
Currently Selected:
መዝሙር 17: NASV
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጅ መብት © 2001 በ Biblica, Inc.
ፈቃድ የተገኘባቸው ናቸው። መብቱ በመላው ዓለም በሕግ የተጠበቀ።
Holy Bible, New Amharic Standard Version™ (Addisu Medebegna Tirgum™)
Copyright © 2001 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.