YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙር 16

16
መዝሙር 16
እግዚአብሔር ርስቴ
የዳዊት ቅኔ።
1አምላክ ሆይ፤ መጠጊያዬ ነህና፣
በከለላህ ሰውረኝ።
2 እግዚአብሔርን፣ “አንተ ጌታዬ ነህ፤
ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም”
አልሁት።
3በምድር ያሉ ቅዱሳን፣
ሙሉ ደስታ የማገኝባቸው ክቡራን ናቸው።#16፥3 ወይም በምድሪቱ ላሉ አረማውያን፣ ካህናትና ደስ ለተሰኙባቸው መኳንንት ሁሉ ይህን እላለሁ
4ሌሎችን አማልክት የሚከተሉ፣
ሐዘናቸው ይበዛል፤
እኔ ግን የደም ቍርባናቸውን አላፈስስም፤
ስማቸውንም በአፌ አልጠራም፤
5 እግዚአብሔር የርስት ድርሻዬና ጽዋዬ ነው፤
ዕጣዬም በእጅህ ናት።
6መካለያ ገመድ ባማረ ስፍራ ተጥሎልኛል፤
በርግጥም የተዋበች ርስት አግኝቻለሁ።
7የሚመክረኝን እግዚአብሔርን እባርካለሁ፤
በሌሊት እንኳ ልቤ ቀናውን ያመላክተኛል።
8 እግዚአብሔርን ሁልጊዜ በፊቴ አድርጌአለሁ፤
እርሱ በቀኜ ስላለ አልናወጥም።
9ስለዚህ ልቤ ደስ አለው፤ ነፍሴም ሐሤት አደረገች፤
ሥጋዬም ያለ ሥጋት ዐርፎ ይቀመጣል፤
10በሲኦል#16፥10 ወይም በመቃብር ውስጥ አትተወኝምና፤
ቅዱስህም#16፥10 ወይም በአንተ የታመነውን መበስበስን እንዲያይ አታደርግም።
11የሕይወትን መንገድ ታሳየኛለህ፤#16፥11 ወይም ታሳውቀኛለህ
በአንተ ዘንድ የደስታ ሙላት፣
በቀኝህም የዘላለም ፍሥሓ አለ።

Currently Selected:

መዝሙር 16: NASV

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in