ኢሳይያስ 15
15
በሞዓብ ላይ የተነገረ ትንቢት
1ስለ ሞዓብ የተነገረው ንግር ይህ ነው፤
የሞዓብ ዔር ፈራረሰች፤
በአንድ ሌሊትም ተደመሰሰች።
የሞዓብ ቂር ፈራረሰች፣
በአንድ ሌሊት ተደመሰሰች።
2ዲቦን ወደ መቅደሱ ወጣ፤
ሊያለቅስም ወደ ኰረብታው ሄደ፤
ሞዓብ ስለ ናባው፣ ስለ ሜድባም ዋይታ ያሰማል፤
ራስ ሁሉ ተመድምዷል፤
ጢምም ሁሉ ተላጭቷል።
3በየመንገዱም ማቅ ይለብሳሉ፤
በየሰገነቱና በየአደባባዩ
ሁሉም ያለቅሳሉ፤
እንባም ይራጫሉ።
4ሐሴቦንና ኤልያሊ ጮኹ፤
ድምፃቸው እስከ ያሀጽ ድረስ ተሰማ፤
ስለዚህ የሞዓብ ጦረኞች ጮኹ፤
ልባቸውም ራደ።
5ልቤ ስለ ሞዓብ አለቀሰ፤
ስደተኞቿም እስከ ዞዓር፣
እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ሸሹ፤
እንባቸውን እያፈሰሱ
ወደ ሉሒት ወጡ፤
በሖሮናይም መንገድም፣
ስለ ጥፋታቸው ዋይ እያሉ ነጐዱ።
6የኔምሬ ውሆች ደርቀዋል፤
ሣሩ ጠውልጓል፤
ቡቃያውም ጠፍቷል፤
ለምለም ነገር አይታይም።
7ስለዚህ ያገኙትን ሀብት፣
ያከማቹትን ንብረት ከአኻያ ወንዝ ማዶ ተሸክመው ያሻግሩታል።
8ጩኸታቸው እስከ ሞዓብ ዳርቻ ድረስ ያስተጋባል፤
ዋይታቸው እስከ ኤግላይም፣
ሰቈቃቸውም እስከ ብኤርኢሊም ደረሰ።
9የዲሞን#15፥9 የማሶሪቱ ቅጅ ከዚህ ጋር ይስማማል፤ የሙት ባሕር ጥቅልል፣ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕምና የቩልጌት ቅጅ ግን፣ ዲቦን ይላሉ። ወንዞች በደም ተሞልተዋል፤
በዲሞን ላይ ግን ከዚያ ነገር የበለጠ አመጣለሁ፤
ከሞዓብ በሚሸሹት፣
በምድሪቱም ላይ በሚቀሩት አንበሳ እሰድዳለሁ።
Currently Selected:
ኢሳይያስ 15: NASV
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጅ መብት © 2001 በ Biblica, Inc.
ፈቃድ የተገኘባቸው ናቸው። መብቱ በመላው ዓለም በሕግ የተጠበቀ።
Holy Bible, New Amharic Standard Version™ (Addisu Medebegna Tirgum™)
Copyright © 2001 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.