1 ዜና መዋዕል 8
8
የብንያማዊው የሳኦል ትውልድ ሐረግ
8፥28-38 ተጓ ምብ – 1ዜና 9፥34-44
1ብንያም የበኵር ልጁን ቤላን፣
ሁለተኛ ልጁን አስቤልን፣ ሦስተኛ ልጁን አሐራን፣
2አራተኛ ልጁን ኖሐን፣ ዐምስተኛ ልጁን ራፋን ወለደ።
3የቤላ ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፤
አዳር፣ ጌራ፣ አቢሁድ፣#8፥3 ወይም፣ የሁድ አባት ጌራ 4አቢሱ፣ ናዕማን፣ አሖዋ፣ 5ጌራ፣ ሰፉፋ፣ ሒራም።
6በጌባዕ ይኖሩ የነበሩትና በኋላም በምርኮ ወደ መናሐት የተወሰዱት የኤሁድ ዘሮች እነዚህ ናቸው፤
7ናዕማን፣ አኪያ፣ ጌራ፤ በምርኮ ጊዜ እየመራ የወሰዳቸው የዖዛና የአሒሑድ አባት ጌራ ነበረ።
8ሸሐራይም ሚስቶቹን ሑሺምንና በዕራን ከፈታ በኋላ በሞዓብ ምድር ወንዶች ልጆች ወለደ። 9ከሚስቱ ከሖዴሽ ዮባብን፣ ዲብያን፣ ማሴን፣ ማልካምን፣ 10ይዑጽን፣ ሻክያንና ሚርማን ወለደ፤ እነዚህም የቤተ ሰብ አለቆች የነበሩ ልጆቹ ናቸው። 11ሑሺም ከተባለች ሚስቱ አቢጡብና ኤልፍዓል የተባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት።
12የኤልፍዓል ወንዶች ልጆች፤
ዔቤር፣ ሚሻም እንዲሁም ኦኖንና ሎድ የተባሉ ከተሞችን ከነመንደሮቻቸው የቈረቈረ ሻሜድ፣ 13በኤሎን ይኖሩ ለነበሩ ቤተ ሰቦች አለቆችና የጋት ነዋሪዎችን አስወጥተው ያሳደዱ በሪዓና ሽማዕ።
14አሒዮ፣ ሻሻቅ፣ ይሬምት፣ 15ዝባድያ፣ ዓራድ፣ ዔድር፣ 16ሚካኤል፣ ይሽጳና ዮሐ የበሪዓ ወንዶች ልጆች ነበሩ።
17ዝባድያ፣ ሜሱላም፣ ሕዝቂ፣ ሔቤር፣ 18ይሽምራይ፣ ይዝሊያና ዮባብ የኤልፍዓል ወንዶች ልጆች ነበሩ።
19ያቂም፣ ዝክሪ፣ ዘብዲ፣ 20ኤሊዔናይ፣ ጺልታይ፣ ኤሊኤል፣ 21ዓዳያ፣ ብራያና ሺምራት የሰሜኢ ወንዶች ልጆች ነበሩ።
22ይሽጳን፣ ዔቤር፣ ኤሊኤል፣ 23ዓብዶን፣ ዝክሪ፣ ሐናን፣ 24ሐናንያ፣ ኤላም፣ ዓንቶትያ 25ይፍዴያና ፋኑኤል የሻሻቅ ወንዶች ልጆች ነበሩ።
26ሽምሽራይ፣ ሽሃሪያ፣ ጎቶልያ፣ 27ያሬሽያ፣ ኤልያስና፣ ዝክሪ የይሮሐም ወንዶች ልጆች ነበሩ።
28እነዚህ ሁሉ በየትውልድ ሐረጋቸው የተቈጠሩ አለቆችና የቤተ ሰብ መሪዎች ሲሆኑ፣ የሚኖሩትም በኢየሩሳሌም ነበረ።
29የገባዖን አባት#8፥29 አባት ማለት፣ የማኅበረ ሰብ መሪ ወይም የጦር መሪ ማለት ነው። ይዒኤል#8፥29 አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞች (1ዜና 9፥35 ይመ) ከዚህ ጋራ ይስማማሉ፤ ዕብራይስጡ ግን ይዒኤል የሚለውን አይጨምርም በገባዖን ኖረ።
የሚስቱም ስም መዓካ ይባላል። 30የበኵር ልጁም አብዶን ይባል ነበር፤ የእርሱም ተከታዮች ጹር፣ ቂስ፣ ባኣል፣ ኔር፣#8፥30 አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞች (እንዲሁም 1ዜና 9፥36 ይመ) ከዚህ ጋራ ይሰማማሉ፤ ዕብራይስጡ ግን፣ “ኔር” የሚለውን ስም አይጨምርም ናዳብ፣ 31ጌዶር፣ አሒዮ፣ ዛኩርና#8፥31 9፥37 ላይ ዘካርያስ ይላል። 32የሳምአን አባት ሚቅሎት ነበሩ። እነርሱም ደግሞ ከሥጋ ዘመዶቻቸው ጋራ በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ይኖሩ ነበር።
33ኔር ቂስን ወለደ፤ ቂስም ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታንን፣ ሜልኪሳን፣ አሚናዳብን፣ አስበኣልን#8፥33 ኢሽቦሼት በመባልም ይታወቃል። ወለደ።
34የዮናታን ወንድ ልጅ
መሪበኣል ነው፤#8፥34 ሜፈቦሼት በመባልም ይታወቃል። መሪበኣልም ሚካን ወለደ።
35የሚካ ወንዶች ልጆች፤
ፒቶን፣ ሜሌክ፣ ታሬዓ፣ አካዝ።
36አካዝ ይሆዓዳን ወለደ፤ ይሆዓዳም ዓሌሜትን፣ ዓዝሞትን፣ ዚምሪን ወለደ፤ ዚምሪን ሞጻን ወለደ። 37ሞጻ ቢንዓን ወለደ፤ ቢንዓ ረፋያን ወለደ፤ ረፋያ ኤልዓሣን ወለደ፤ ኤልዓሣም ኤሴልን ወለደ።
38ኤሴል ስድስት ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ስማቸውም፦
ዓዝሪቃም፣ ቦክሩ፣ እስማኤል፣ ሸዓርያ፣ አብድዩ፣ ሐናን ይባላል፤ እነዚህ ሁሉ የኤሴል ልጆች ናቸው።
39የወንድሙ የኤሴቅ ወንዶች ልጆች፤
የበኵር ልጁ ኡላም፣ ሁለተኛ ልጁ ኢያስ፣ ሦስተኛ ልጁ ኤሊፋላት። 40የኡላም ልጆች በቀስት መንደፍ የሚችሉ ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ፤ እነርሱም በአጠቃላይ ቍጥራቸው አንድ መቶ ኀምሳ ወንዶች ልጆችና የልጅ ልጆች ነበሯቸው።
እነዚህ ሁሉ የብንያም ትውልዶች ነበሩ።
Currently Selected:
1 ዜና መዋዕል 8: NASV
Highlight
Share
Copy
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapi.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fen.png&w=128&q=75)
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.