YouVersion Logo
Search Icon

1 ዜና መዋዕል 7

7
ይሳኮር
1የይሳኮር ወንዶች ልጆች፤
ቶላ፣ ፉዋ፣ ያሱብ፣ ሺምሮን፤ በአጠቃላይ አራት ናቸው።
2የቶላ ወንዶች ልጆች፤
ኦዚ፣ ረፋያ፣ ይሪኤል፣ የሕማይ፣ ይብሣም፣ ሽሙኤል፤ እነዚህ የየቤተ ሰባቸው አለቆች ናቸው፤ በዳዊት ዘመነ መንግሥት ከቶላ ዘሮች፣ በየትውልድ ሐረጋቸው የተቈጠሩት የቶላ ዘሮች ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ፤ ቍጥራቸውም ሃያ ሁለት ሺሕ ስድስት መቶ ነበረ።
3የኦዚ ወንድ ልጅ፤
ይዝረሕያ።
የይዝረሕያ ወንዶች ልጆች፤
ሚካኤል፣ አብድዩ፣ ኢዩኤል፣ ይሺያ፤ አምስቱም አለቆች ነበሩ። 4ብዙ ሚስቶችና ልጆች ስለ ነበሯቸው፣ ከቤተ ሰባቸው የትውልድ ሐረግ ለውጊያ ብቁ የሆኑ ሠላሳ ስድስት ሺሕ ሰዎች ነበሯቸው።
5ከይሳኮር ጐሣዎች ሁሉ የተመዘገቡት ተዋጊዎች የቤተ ሰቦቹ ትውልድ ቍጥር በአጠቃላይ ሰማንያ ሰባት ሺሕ ነበሩ።
ብንያም
6ሦስቱ የብንያም ወንዶች ልጆች፤
ቤላ፣ ቤኬር፣ ይዲኤል።
7የቤላ ወንዶች ልጆች፤
ኤሴቦን፣ ኦዚ፣ ዑዝኤል፣ ለኢያሪሙት፣ ዒሪ፤ በአጠቃላይ አምስት ሲሆኑ፣ የቤተ ሰብ አለቆች ናቸው፤ በትውልድ ሐረግ መዝገባቸው ሃያ ሁለት ሺሕ ሠላሳ አራት ተዋጊ ሰዎች ተመዝግበዋል።
8የቤኬር ወንዶች ልጆች፤
ዝሚራ፣ ኢዮአስ፣ አልዓዛር፣ ኤልዮዔናይ፣ ዖምሪ፣ ኢያሪሙት፣ አብያ፣ ዓናቶት፣ ዓሌሜት፤ እነዚህ ሁሉ የቤኬር ልጆች ነበሩ። 9በትውልድ ሐረግ መዝገባቸውም ውስጥ የየቤተ ሰባቸው አለቆችና ሃያ ሺሕ ሁለት መቶ ተዋጊዎች ተመዝግበዋል።
10የይዲኤል ልጅ፤
ቢልሐን።
የቢልሐን ወንዶች ልጆች፤
የዑስ፣ ብንያም፣ ኤሁድ፣ ክንዓና፣ ዜታን፣ ተርሴስ፣ አኪሳኦር፤ 11እነዚህ ሁሉ የይዲኤል ልጆች የየቤተ ሰቡ አለቆች ነበሩ፤ እነርሱም ለውጊያ ብቁ የሆኑ ዐሥራ ሰባት ሺሕ ተዋጊዎች ነበሯቸው።
12ሳፊንና ሑፊም የዒር ዘሮች ሲሆኑ፣ ሑሺም ደግሞ የአሔር ዘር ነው።
ንፍታሌም
13የንፍታሌም ወንዶች ልጆች፤
ያሕጽሔል፣ ጉኒ፣ ዬጽር፣ ሺሌም፤ እነዚህ የባላ ዘሮች ናቸው።
ምናሴ
14የምናሴ ዘሮች፤
ሶርያዊት ቁባቱ የወለደችለት ልጁ አሥርኤል ነው። እርሷም የገለዓድን አባት ማኪርን የወለደች ናት፤ 15ማኪርም ከሑፊምና ከሳፊም ወገኖች ሚስት አገባ። እኅቱም መዓካ ትባል ነበር።
ሌላው ዘሩ ሰለጰዓድ ሲሆን፣ እርሱም ሴቶች ልጆች ብቻ ነበሩት።
16የሚኪር ሚስት መዓካ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ፋሬስ አለችው። የወንድሙም ስም ሱሮስ ይባላል፤ ወንዶች ልጆቹም ኡላምና ራቄም ነበሩ።
17የኡላም ወንድ ልጅ፤
ባዳን፤
እነዚህ የምናሴ ልጅ፣ የማኪር ልጅ፣ የገለዓድ ወንዶች ልጆች ናቸው።
18እኅቱ መለኬት ኢሱድን፣ አቢዔዝርንና ማሕላን ወለደች።
19የሸሚዳ ወንዶች ልጆች ደግሞ እነዚህ ነበሩ፤
አሒያን፣ ሴኬም፣ ሊቅሒ፣ አኒዓም።
ኤፍሬም
20የኤፍሬም ዘሮች፤
ሹቱላ፣ ልጁ ባሬድ፣
ልጁ ታሐት፣ ልጁ ኤልዓዳ፣
ልጁ ታሐት፣ 21ልጁ ዛባድ፣
ልጁ ሹቱላ።
ኤድርና ኤልዓድ ከብቶች ለመስረቅ በወረዱ ጊዜ፣ የአገሩ ተወላጆች በሆኑት በጌት ሰዎች ተገደሉ። 22አባታቸውም ኤፍሬም ብዙ ቀን አለቀሰላቸው፤ ዘመዶቹም መጥተው አጽናኑት። 23ከዚያም ወደ ሚስቱ ገብቶ ተኛ፤ እርሷም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች፤ በቤተ ሰቡ ላይ ከደረሰው መከራ የተነሣ ስሙን በሪዓ አለው። 24ሴት ልጁ ስሟ ሲአራ ይባላል፤ እርሷም የታችኛውንና የላይኛውን ቤት ሖሮንንና ኡዜንሼራን የተባሉትን ከተሞች የቈረቈረች ናት።
25ልጁ ፋፌ፣ ልጁ#7፥25 አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞች ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ ዕብራይስጡ ግን፣ ልጁ የሚለውን ቃል አይጨምርም ሬሴፍ፣
ልጁ ቴላ፣ ልጁ ታሐን፣
26ልጁ ለአዳን፣ ልጁ ዓሚሁድ፣
ልጁ ኤሊሳማ፣ 27ልጁ ነዌ፣
ልጁ ኢያሱ።
28ምድራቸውና መኖሪያቸው ቤቴልንና በዙሪያዋ የሚገኙትን ከተሞች፣ በስተ ምሥራቅ ነዓራን፣ በስተ ምዕራብ ጌዝርንና መንደሮቿን፣ እንዲሁም ሴኬምንና መንደሮቿን፣ ከዚያም ዐልፎ ዓያንና መንደሮቿን በሙሉ ያጠቃልል ነበር። 29በምናሴም ወሰን ላይ ቤትሳን፣ ታዕናክ፣ መጊዶና ዶር ከነመንደሮቻቸው ነበሩ። በእነዚህም መንደሮች የእስራኤል ልጅ የዮሴፍ ዘሮች ይኖሩ ነበር።
አሴር
30የአሴር ወንዶች ልጆች፤
ዪምና፣ የሱዋ፣ የሱዊ፣ በሪዓ፤ እኅታቸውም ሤራሕ ትባል ነበር።
31የበሪዓ ወንዶች ልጆች፤
ሐቤርና የቢርዛዊት አባት መልኪኤል።
32ሔቤርም ያፍሌጥን፣ ሳሜርን፣ ኮታምንና እኅታቸውን ሶላን ወለደ።
33የያፍሌጥ ወንዶች ልጆች፤
ፋሴክ፣ ቢምሃል፣ ዓሲት፤
የያፍሌጥ ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ።
34የሳሜር ወንዶች ልጆች፤
አኪ፣ ሮኦጋ፣#7፥34 ወይም፣ ወንድሙ ሳሜር፤ ሮኦጋ ይሑባ፣ አራም።
35የወንድሙ የኤላም ወንዶች ልጆች፤
ጾፋ፣ ይምና፣ ሰሌስ፣ ዓማል።
36የጻፋ ወንዶች ልጆች፤
ሱዋ፣ ሐርኔፍር፣ ሦጋል፣ ቤሪ፣ ይምራ፣ 37ቤጴር፣ ሆድ፣ ሳማ፣ ሰሊሳ፣ ይትራን፣ ብኤራ።
38የዬቴር ወንዶች ልጆች፤
ዮሮኒ፣ ፊስጳ፣ አራ።
39የዑላ ወንዶች ልጆች፤
ኤራ፣ ሐኒኤል፣ ሪጽያ።
40እነዚህ ሁሉ የአሴር ዘሮች ናቸው፤ እነርሱም የቤተ ሰብ አለቆች፣ ምርጥ ሰዎች፣ ብርቱ ተዋጊዎችና ድንቅ መሪዎች ነበሩ። በትውልድ መዝገባቸው እንደ ተጻፈው ለውጊያ ብቁ የሆኑት ወንዶች ቍጥር ሃያ ስድስት ሺሕ ነበር።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Video for 1 ዜና መዋዕል 7