1
ወደ ዕብራውያን 5:14
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
ጠንካራ ምግብ ግን መልካሙንና ክፉዉን ለመለየት በሥራቸው የለመደ ልቡና ላላቸው ለፍጹማን ሰዎች ነው።
Compare
Explore ወደ ዕብራውያን 5:14
2
ወደ ዕብራውያን 5:12-13
መምህራን ልትሆኑ ሲገባችሁ፥ ካመናችሁ ጀምሮ በትምህርት ላይ የቈያችሁ ስለ ሆነ፥ እስከ ዛሬም ገና የእግዚአብሔርን የቃሉን መጀመሪያ ትምህርት ሊያስተምሩአችሁ ትወዳላችሁ፤ ወተትንም ሊግቱአችሁ ትሻላችሁ፤ ጽኑ ምግብንም አይደለም። ወተትን የሚጋት ሁሉ ሕፃን ስለሆነ፥ የጽድቅን ቃል ሊያውቅ አይሻም።
Explore ወደ ዕብራውያን 5:12-13
3
ወደ ዕብራውያን 5:8-9
ልጅም ቢሆን መከራን ስለ ተቀበለ መታዘዝን ዐወቀ። ከተፈጸመም በኋላ ለሚታዘዝለት ሁሉ ሕይወትን የሚሰጥ የዘለዓለም መድኅን ሆነ።
Explore ወደ ዕብራውያን 5:8-9
4
ወደ ዕብራውያን 5:7
እርሱም ሥጋ ለብሶ በዚህ ዓለም በነበረበት ጊዜ፥ በታላቅ ጩኸትና እንባ ከሞት ሊያድነው ወደሚችለው ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፤ ጽድቁንም ሰማው።
Explore ወደ ዕብራውያን 5:7
Home
Bible
Plans
Videos