1
መጽሐፈ አስቴር 6:1-2
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
በዚያኑ ሌሊት ንጉሡ እንቅልፍ አጥቶ ስለ ነበር በቤተ መንግሥቱ መዝገብ ላይ የሰፈሩትን የታሪክ ማስታወሻዎች አምጥተው ያነቡለት ዘንድ ትእዛዝ ሰጠ። ከተነበቡትም ማስታወሻዎች አንዱ ክፍል የንጉሡን መኖሪያ ክፍሎች ይጠብቁ የነበሩት ቢግታናና ቴሬሽ ተብለው የሚጠሩት ሁለቱ ጃንደረቦች ንጉሡን ለመግደል የጠነሰሱትን ሤራ መርዶክዮስ እንዴት እንደ ደረሰበት የሚገልጥ ነበር፤
Compare
Explore መጽሐፈ አስቴር 6:1-2
2
መጽሐፈ አስቴር 6:6
ሃማንም ወደ ውስጥ በገባ ጊዜ ንጉሡ “ታላቅ ክብር ልሰጠው የፈለግኹት አንድ ሰው አለ፤ ታዲያ ለዚህ ሰው ምን ላደርግለት የሚገባ ይመስልሃል?” ሲል ጠየቀው። ሃማንም “ንጉሡ ይህን ክብር ከእኔ ሌላ ለማን ይሰጣል?” ብሎ በልቡ አሰበ።
Explore መጽሐፈ አስቴር 6:6
3
መጽሐፈ አስቴር 6:10
ንጉሡም ሃማንን እንዲህ ሲል አዘዘው፦ “በል እንግዲህ ፍጠን፤ ልብሰ መንግሥቱንና ፈረሱን አዘጋጅተህ ይህን አሁን ያልከውን ክብር ሁሉ አይሁዳዊ ለሆነው ለመርዶክዮስ አድርግለት፤ እርሱንም አሁን በቤተ መንግሥቱ መግቢያ በር አጠገብ ስለምታገኘው ካሳሰብከው ነገር አንድም ሳይቀር ሁሉንም አድርግለት።”
Explore መጽሐፈ አስቴር 6:10
Home
Bible
Plans
Videos