1ኛ ጴጥሮስ: የ5 ቀናት የንባብ ዕቅድናሙና
ጴጥሮስ ደብዳቤውን ሲዘጋ በሁለት የመጨረሻ ማበረታቻዎች ነው፡፡ የመጀመሪያው በትንሿ እስያ ውስጥ ለተበተኑ የቤተክርስቲያናቱመሪዎች ወይም ሽማግሌዎች ነው። ልክ እንደ እነርሱ ጴጥሮስም የቤተክርስቲያን መሪ የሆነና መከራ የተቀበለ ነው፡፡ ነገር ግን ጴጥሮስ ለመሪዎች ይህንኑ እውነት መከራ ወደ ክብር እንደሚመራ ለአባላቶቻቸው እንዲነግሩ ያበረታቸዋል፡፡ እኚህ መሪዎች ዋጋውን ከግምት ባላስገባ ሁኔታ ግልጋሎቻቸውን በፈቃዳቸው መጠበቅ እንዳለባቸውና የኢየሱስ መስዋትና የፅድቅ ህይወት ህያው ምሳሌ እንዲያደርጓቸው ይመክራል፡፡ ኢየሱስ በፈቃድ መምራት በመከራ ውስጥ ማገልገል የክብር መንገድ መሆኑን አረጋግጧል፡፡
የመከራ አስፈላጊነትም ሆነ የመሪዎች እንደ እረኛ ያላቸው መልክ ሁለቱም ጴጥሮስ ከኢየሱስ ጋር ካለው የግል ህይወት ልምምድ ጋር በጥብቅ የተቆራኘ ነው፡፡ ኢየሱስ መከራ መቀበል እንደሚገባው ሲናገር ጴጥሮስ ግን ገሰፀው፤ ኢየሱስም መልሶ አንተ ሰይጣን አለው፡፡ የመከራን አስፈላጊነት የሚክድ ሰይጣናዊ ውሸት ነው፡፡ ኢየሱስን ሦስት ጊዜ ከካደው በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስን ሦስት ጊዜ ደጋግሞ “በጎቼን መግብ” በማለት ወደ ቤተ-ክርስቲያን አመራርነት ሲጠራው እናያለን፡፡ ጴጥሮስ መሪዎች የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን በጎች እንዲጠብቁና በፈቃደኝነት መከራን መቀበል የኢየሱስ ተከታይ ሆኖ ከደረሰበት ጥልቅ ውድቀት የመጣ ነው መሆኑን በመንገር ያበረታታቸዋል፡፡
እነዚህ ጊዜያት ለእነዚህ አብያተ ክርስቲያናት ወጣት አባላት የጴጥሮስን ማበረታቻ ያስገነዝባል። የጴጥሮስን በመከራ ላይ ስላለው ትዕቢት እግዚአብሔር በግልፅ ተቃወመው ማለት ነው፤ ስለዚህ ወጣት የሆኑ አማኞች “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፣ ለትሑታን ግን ይራራላቸዋል” በማለት ያሳስባቸዋል። ጴጥሮስ መምራት ለሚሹ ወጣቶች ኢየሱስ የተዋረደውና በትሕትና የተገዛለት አንድ ጊዜ ብቻ የሥልጣን ቦታ እንደተሰጠው ያስታውሳቸዋል። ትህትናና መከራ መቼም የተጣሉ አይደሉም፡፡ የፀናችው የእግዚአብሔር እጅ ኢየሱስን ከውርደት ሞት አስነስቶታል፤ እንዲሁም ወደፊት በስጋትና በስቃይ ላሉት አማኞችም በእርግጠኝነት ይራራል፡፡
ጴጥሮስ ትህትና ማለት ሞኝነት አለመሆኑን ያስጠነቅቃል፡፡ ሰይጣን በመከራና በውሸቱ እያደነ መከራን ማስወገድ ይቻላል ይላል፡፡ ጴጥሮስ የእርሱ ደቀ-መዛሙርት የእርሱን ስህተት መልሰው እንዳይደግሙ ይፈልጋል፡፡ እኚህ አብያተ-ክርስቲያናት ሰይጣንን መከራ የተሰቀለው የኢየሱስ ተከታዮች እስከሆንን ድረስ የማይቆም በመሆኑ በዕውቀት መቋቋም አለባቸው፡፡ መጪው ዘላለማዊ ክብራቸው ግን የማይቀር ነው።
ጴጥሮስ ደብዳቤውን ሲዘጋው እየፃፈ ያለው ከባቢሎን መሆኑን ይናገራል፡፡ ባቢሎን በእስራኤል ታሪክ ውስጥ የጥንት ከተማ ናት፡፡ በጴጥሮስ ዘመን ጠፍታ የነበረች ቢሆንም ነገር ግን ለእግዚአብሔር የማይታዘዙ ህዝቦች ምሳሌ ሆናለች፡፡ እኚህ አማኞች ዜግነታቸውን ሳያማክል ሁልጊዜ መፃተኞች እንዲሆኑ የመጨረሻ ማሳሰቢያው ነው፡፡ የኢየሱስ ተከታዮች ሁልጊዜ የሌላ ሀገር ዜጎች ናቸው እንዲሁም እንደ አብዛኛው የሌላ ሀገር ዜጎች እንደመሆናቸው ይጠላሉ፡፡
በኢየሱስ ባለን እምነት የማይቀረውን መከራ ለመቀበል ይከብደናል፤ ቤተ-ክርስቲያናቶቻችን የማይገቡበት ወይም ደግሞ የማይበረታቱበትም ነው፡፡ ይሁን እንጂ ለአብዛኛው በዓለም ዙሪያ ለሚገኙት ለኢየሱስ ተከታዮችና በታሪክ አጋጣሚ ሁሉ መከራ እንዳይነካቸው የተሰጣቸው አንዳችም ዕድል አልነበረም፡፡ ጴጥሮስ ህይወትን ያለ መከራ አስቧት አያውቅም ይልቅ የተባረከ ህይወት በመከራ ከፍ ይላል ብሎ ያስረዳል፡፡ ለኢየሱስ ተከታዮች የመከራ አይቀሬነት መልካም የምስራች ነው ምክንያቱ ደግሞ ክብር፣ በረከት፣ እና ኃይል የማይቀሩ ናቸው ይላል፡፡ ጴጥሮስሲናገር ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበልን በኋላ የፀጋ ሁሉ አምላክ አግዚአብሔር ሊያድስ፣ ሊያጠነክረን ሊያፀናን እና በስልጣኑ ለዘላለም ይተክለናል፡፡
በመንግስታት፣ በቤተሰቦች፣ እንዲሁም በጓደኞቻችን የሚደርስብን ስደት ብዙዉን ጊዜ ቁጣና መራርነትን ሊቀሰቅስ ይችላል፡፡ ጴጥሮስ ግን የሚፈልገው የአንተ የመጀመሪያው ምላሽ ሊሆን የሚገባው ደስታ ነው ይለናል፡፡ ጴጥሮስ ስለ ኢየሱስ በመስበኩ በተገፋና በተደበደበ ጊዜ ስለ ኢየሱስ ስም መከራን ለመቀበል የተገባው በመሆኑ ደስተኛ ሆነ፡፡ ያ ማለት ጴጥሮስ ጀግና ስለነበረና ድብደባውም ሳይጎዳው ቀርቶ አይደለም፡፡ (አስታውስ ኢየሱስን ክዶት እንደነበረ!) ጴጥሮስ ስለ ስሙ የተደሰተበት ምክንያት በስሙ መከራ በመንፈሳዊም ሆነ በአካል ከኢየሱስና ከሚመጣው ትንሳኤ ጋር ስለሚጣመር ነው።
መንፈስ ቅዱስ መከራ የተቀበለውንና የሞተውን እግዚአብሔር ወልድን ታይ ዓይኖችህን ያበራ ዘንድ እፀልይልሃለሁ፡፡ ከእርሱ ጋር መከራን ስንቀበል የማይቀረውን ትንሳኤያችንን የሚያረጋግጥልንን አየሱስን ማየት ይሁንልን፡፡
ስለዚህ እቅድ
ተስፋ ተኮር በሆነው ደብዳቤው ለመጀመሪያዋ ክፍለ ዘመን ቤተ-ክርስቲያን ጴጥሮስ በማመን፣ በመታዘዝ እና ፍርድና መከራ ሲገጥመን ፀንተን እንድንቆም ያበረታናል፡፡ ይህን የሚያሳስበን ምክንያት ደግሞ በክርስቶስ ማን እንደሆንን፣ ቅዱስ የሆነውን ኑሮ እንኖር ዘንድ ኃይል የሆነልንና ወደፊት ዘላለምን ለመውረስ የምንችል ነን በማለት ነው፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Spoken Gospel ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ http://www.spokengospel.com/