1ኛ ጴጥሮስ: የ5 ቀናት የንባብ ዕቅድናሙና
ከኢየሱስ ደቀ-መዛሙርት አንዱ የሆነው ጴጥሮስ በዛሬዋ ቱርክ በምንላት በታናሿ እስያ ተበትነው ያሉትን አማኞች ሲደርስ እናያለን፡፡ ምናልባትም እኚህ አማኞች አህዛቦችና የሮሜ ግዛት ዜግነት ያላቸው የነበሩ ቢሆኑም፤ ነገር ግን ጴጥሮስ “በእግዚአብሔር የተመረጡ መፃተኞች” ብሎ ይጠራቸዋል፡፡ እነርሱ በየቦታው የተበተኑ በእግዚአብሔር የተመረጡ የሌላ ሀገር ዜጎች ናቸው፡፡
ጴጥሮስ ይህንን ቃል በዓላማ ሲመርጥ መፃተኛ አህዛቦችን በእግዚአብሔር የተመረጡ ህዝቦች ይኸውም የአይሁድ ታሪክ ውስጥ ይመድባቸዋል፡፡ ልክ እግዚአብሔር እስራኤልን እንደመረጠ እንዲሁ እኚህን ሮማውያንን መርጧል፡፡ ልክ አይሁዳውያን በባቢሎን ምድር እንደተበተኑት እኚህም በኢየሱስ ያመኑቱ በሮማውያን ምድር ተበትነዋል፡፡ ይሁን እንጂ ጴጥሮስ ተመሳሳይ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳያቸውን ብቻ አልነበረም ንፅፅር ውስጥ ያስገባው፡፡ እርሱ እያለ ያለው ልክ እግዚአብሔር አይሁዳውያንን እንደመረጠ ሁሉ አህዛቦችንም መርጧቸዋል ነው፡፡ በባዕድ ምድር የነበረው የመፃተኝነት ታሪክና ከምርኮ መመለስ የእስራኤል ማዕከላዊ ታሪክ ሲሆን ይህ ታሪክ ደግሞ አሁን የሁላችን ታሪክ እንዲሆን እግዚአብሔር አሁን ድረስ እየፃፈው ነው፡፡
በኢየሱስ ያመነ ሁሉ መፃተኛ ነው፡፡ የትኛው ክርስቲያን ከዚህ ምድር ዜግነት የለውም ምክንያቱም እግዚአብሔር በእርሱ ዘንድ መንግስቱን ሊሰጠን መርጦናል፡፡ ጴጥሮስ ጨምሮ ሲናገር እኛ የተመረጥነው በእግዚአብሔር አብ ዘላለማዊ ዕውቀት ነው ይላል፤ ይህም በሚቀድሰው በመንፈስቅዱስሥራ በመታዘዝናበደምበመርጨትነው፡፡ እነዚህ እያንዳንዳቸው ሀረጎች አህዛብን ከተመረጡት የእግዚአብሔር ህዝብ ጋር የሚያስተሳስር አዲስ መንገድ ነው፡፡ ከአብርሃም ጀምሮ እግዚአብሔር ዓለምን ይባርክ ዘንድ አህዛብን የሚያውቅና የመረጣቸው መሆኑን እናያለን፡፡ ወደ መገናኛ ድንኳኑ ሲወርድ የእግዚአብሔር መንፈስ እስራኤልን ቤቱ ትሆን ዘንድ መርጧታል፡፡ ልክ እስራኤል ህዝብ የሆኑ ለታ የእግዚአብሔርም ህዝብ ሊታዘዝ ቃል ሲገባ ሙሴ ደግሞ በደሙ ረጫቸው፡፡ እስራኤል በደሙ ተረጭተው ሀገር እንደሆኑ ሁሉ ማንም የኢየሱስን ደም የሚታመን ደግሞ አዲስ ህዝብ ይሆናል፡፡
እግዚአብሔር መፃተኞች እንሆን ዘንድ መርጦናል፡፡ ከሆነ ነገር ወጣ ብለን የተመረጥን ስለሆንን መልካም ዜና ነው፡፡ ጴጥሮስ እንደሚነግረን እንደመፃተኛ ያለን አዲሱ ማንነት ወደ አዲሱ ቤተሰብ መቀላቀላችንን የሚያበስር ነው፡፡ እኛ ለተወለድንበት ምድር ሞተናል ነገር ግን ፍቅር በሆነው በእግዚአብሔርና በትንሳኤው ህይወት ወደ ተገኘው ወደ ዘላለም ቤተሰብ ዳግም ተወልደናል፡፡ እንደ እግዚአብሔር ልጆችና እንደ እየሱስ ወንድምና እህቶች ዘላለማዊ የሆነውን፣ የማይበላሸውንና የማይጠፋውን በእግዚአብሔር ብቻ የተጠበቀውን ወራሾች ሆነናል፡፡ የእግዚአብሔር መንግስት ተወላጆች ስንሆን በዚህች ዓለም ባለን እንግድነት ደስ ይለናል፡፡
እንደ አብዛኛው የውጪ ዜጋ በእንግድነታችን መከራ እንቀበላለን፡፡ ጴጥሮስ በደብዳቤዎቹ ሁሉ ኢየሱስን ስንከተል ሊኖረን ስለሚገባ ስነ-ምግባርና መንፈሳዊ “ሌላነት ” ዘርዝሮ ያስረዳል፡፡ ለአሁኑ ግን ጴጥሮስ እያሳሰበን ያለው ለዚህች ምድር ያለን እንግድነት የሰማይ ዜግነታችን ማረጋገጫ ነው እያለን ነው፡፡ መከራ ተስፋ ለመቁረጥ ምክንያት አይደለም፤ ፍርዶች ደስተኛ የምንሆንባቸው ምክንያቶች ናቸው፡፡ ወርቅ በእሳት የሚፈተነውን ያህል እኛ በመከራ በፍፁም የተፈተንን አይደለንም፡፡ እንደሰታለን ምክንያቱም መከራ ያጠራናል እንዲሁም የእምነታችንን ትክክለኛነት ይገልፃል፡፡
የኢየሱስ ተከታዮች መከራን ይቀበላሉ፡፡ ኢየሱስ መከራን ተቀብሏል ነገር ግን ወደ ክብር፣ ከሞት ወደ ህይወት እንዲሁም ከእግዚአብሔር ጋር ወዳለው ዙፋን ነበር የመራው፡፡ ምንም እንኳን ኢየሱስን በዓይናችን ባናየውም ስናምነውና ስንወደው ግን እንደሰታለን፡፡ የሚያንገላቱን በፍፁም የመጨረሻ የሚሉን ነገር የላቸውም ምክንያቱም ደህንነታችንን እነርሱ የሚጉዱት አይደለምና፡፡ አስቀድሞ ጴጥሮስ እንዳለው እግዚአብሔር ስለ እናንተ የጠበቀውን ሀገርም ቢሆን ግለሰብ ሊገድለው፣ ሊሰርቀውና ሊያጠፋው አይችልም፡፡
የመዳን መከራና ተመርጦ መፃተኛ መሆን እንግዳ ነገሮች ቢሆኑም ታላቅ እውነቶች ናቸው፡፡ በብሉይ ኪዳን የነበሩ ነቢያት ቅዱሳት መጻሕፍትን ለማወቅ ያለመታከት ፈልገው ነበር። መላእክት ጭምር እግዚአብሔር መከራን እንዴት ወደ ክብርና ደስታ እንደሚቀይር ለማወቅተስኗቸው ነበር። ነገር ግን ነቢያትና መላዕክት ለማየት የተቸገሩትን በኢየሱስ በኩል በግልፅ አየን፡፡ መከራው ወደ ትንሳኤ ሲመራው ሞቱ ደግሞ ወደ ክብር፡፡ ለማንኛውም አማኝ በኢየሱስ ምክንያት መከራውና ሞቱ ሁልጊዜ ወደ ዘላለማዊና መቼም ወደ ማይነጥፍ ወደ ክብር ወራሽነት እንደሚመራው እናውቃለን፡፡
መፃተኛ እንድንሆን የመረጠንን እግዚአብሔርን ታይ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ዓይኖችህን ያብራልህ፡፡ ኢየሱስ ከመከራችን የሚታደገን እንዲሁም በደሙና በትንሳኤው የእርሱ ቤተሰብ እንዳደረገን ማየት ይሁንልህ፡፡
ስለዚህ እቅድ
ተስፋ ተኮር በሆነው ደብዳቤው ለመጀመሪያዋ ክፍለ ዘመን ቤተ-ክርስቲያን ጴጥሮስ በማመን፣ በመታዘዝ እና ፍርድና መከራ ሲገጥመን ፀንተን እንድንቆም ያበረታናል፡፡ ይህን የሚያሳስበን ምክንያት ደግሞ በክርስቶስ ማን እንደሆንን፣ ቅዱስ የሆነውን ኑሮ እንኖር ዘንድ ኃይል የሆነልንና ወደፊት ዘላለምን ለመውረስ የምንችል ነን በማለት ነው፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Spoken Gospel ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ http://www.spokengospel.com/