የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ጥርጣሬዎቻችንና ተስፋ መቁረጦችናሙና

ጥርጣሬዎቻችንና ተስፋ መቁረጦች

ቀን {{ቀን}} ከ5

ጥርጣሬዎቻችን

ዮሐንስ ደቀ-መዛሙርቱ ኢየሱስን እንዲጠይቁት የላከው ጥያቄ በኢየሱስ ማንነት ላይ ጥርጣሬ እንደጀመረው ያሳያል፡፡ ዮሐንስ በአገልግሎቱ ጅማሮ ላይ ኢየሱስ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ መሆኑን እንደለየው እናውቃለን፡፡ አሁን ግን በዚያች አስጨናቂና መፈናፈኛ በሌላት ወይኒ ቤት ዮሐንስ እስካሁን የገጠመው ሁሉ ስህተት ሊሆን ከቻለ ሊገረም እንደሚችል ማሰብ ጀመረ፡፡

እንደ እርሱ ውስን መረዳት አንዱ ለዮሐንስ የጥርጥር ምክንያት የነበረው መሲህ ሲባል በዓለም እንፈፅም የሚጠበቅበት ስላለ በዚህም ዮሐንስ በብሉይ ኪዳን ስለ መሲሁ የተነገረውን የትንቢት ቃል ኢየሱስ ያላሟላ መሰለው፡፡ ለምሳሌ ኢሳያስ እንደተነበየው እስረኞችን ነፃ እያወጣ አይደለም፡፡ የዮሐንሰ ሀሳብ እውነተኛው መሲህ ቢሆን ኖሮ ከንጉስ ሄሮድስ ፍትሕ ያጣ እስር ነፃ ያወጣው ነበር፡፡ ስለዚህ በእስር እየደከመ ዮሐንስ ኢየሱስ እውነተኛው መሲህ ለመሆኑ መጠራጠር ጀመረ፡፡

ይህ ዘወትር እኛ የምንሰጠው ዓይነት ምላሽ ነው፡፡ ዮሐንስ በወይን ያጋጠመውን ዓይነት ጥርጣሬ እኛም ይገጥመናል፡፡ ይህ የሚከሰተው በጭንቀትና በከባድ ጊዜያት አግዚአብሔር በህይወታችን ምን እየሰራ እንዳለ ሳንረዳ ሲቀር ነው፤ በተለይም ልክ ዮሐንስ በወይኒ ሳለ እንደገጠመው ዓይነት እግዚአብሔር ፀሎታችንን ቸል ያለ ሲመስለን፡፡ የዮሐንስ ደቀ-መዛሙርት የዮሐንስን መልዕክት ለኢየሱስ ካደረሱ በኋላ ኢየሱስ ስለ ዮሐንስ ህይወትና አገልግሎት ጠንካራ ምስክርነት ሰጠ፡፡ ኢየሱስ ሲሰሙት ለነበሩት ህዝብ ሁሉ መጥምቁ ዮሐንስ በትንቢተ ሚልክያስ የመሲሁን መምጣት የሚያውጅ የመጨረሻው መልእክተኛ መሆኑን አረጋገጠላቸው፡፡

ኢየሱስ ይህንን ዮሐንስንና አገልግሎቱን የሚያወድሱ ቃላትን መናገሩ ዮሐንስ በህዝቡ ፊት ስለ ኢየሱስ ማንነት ያንፀባረቀው የጥርጥር ስሜት ህዝቡ ስለ ዮሐንስ ያለው አመለካከት ልክ እንደ ወላዋይና በነፋስ ወዲህና ወዲያ እንደሚል ሸንበቆ እንዳያስመስለው ለማድረግ ነው፡፡ ኢየሱስ ስለ ዮሐንስ ጠንካራ ምስክርነት በመስጠት እያለ የነበረው የሐንስ በእስር ቤት ከገጠመው ነገር የተነሳ ጥርጥር እንደያዘው አውቃለሁ፤ ቢሆንም ግድ የለም ማለቱ ነው፡፡ ኢየሱስ በክርስትና ህይወት መጠራጠርኃጢአት እንዳልሆነ በመረዳት ይረዳናል፡፡

የዚህ ምክንያት ደግሞ በክርስትና ህይወት በጥርጣሬና ባለማመን መካከል ልዩነት ስላለ ነው፡፡ መጠራጠር የአእምሮ ጉዳይ ነው፣ አግዚአብሔር ምን እያደረገና እያለ እንዳለ ሳይገባን ሲቀር ወይም እርሱ ይህን እያደረገና እያለ ያለው ለምን እንደሆነ ሳይገባን ሲቀር ነው፡፡ መጠራጠር ማለት እምነታችን እየበሰለና እያደገ ያለበትን ሂደት ያሳያል፡፡ አለማመን ደግሞ በተቃራኒው የልባችንና የፈቃዳችን ጉዳይ ነው፤ ይህ ማለት ሆን ብለን የእግዚአብሔርን ቃል ላለማመን እምቢ ማለትና እንድናደርግ ያዘዘንን አለማድረግ ነው፡፡ ስለዚህ አለማመን ከመጠራጠር በተለየ ከአግዚአብሔር ይለየናል፡፡

ስለዚህ ሁለተኛው ትኩረታችን የሆነው ጥርጣሬ ለመደምደም በዚህ ምዕራፍ ላይ የተገለጠው የዮሐንስ ጥርጣሬ እግዚአብሔር በእኛ ህይወት እየሰራ ያለው ነገር ምንም እየገባን ባልሆነ ጊዜ የምናንፀባርቀው መጠራጠር ነው፡፡ አሁንም ተስፋ አለ ምክንያቱም በዚያ እርግጠኛ ባለሆንበት ቦታ ሊገናኘን ይመጣልና፡፡

ቀን 2ቀን 4

ስለዚህ እቅድ

ጥርጣሬዎቻችንና ተስፋ መቁረጦች

ይህ የአምስት ቀን የንባብ ዕቅድ በኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ በኩል የተገለጠውን በጥርጣሬዎቻችንና በተስፋ መቁረጦች ግዜያት ሁሉ የእግዚአብሔርን ታማኝነት እውነት እያሳየን ያበረታናል፡፡

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Returning to the Gospel - East Africa ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://returningtothegospel.com/