የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ጥርጣሬዎቻችንና ተስፋ መቁረጦችናሙና

ጥርጣሬዎቻችንና ተስፋ መቁረጦች

ቀን {{ቀን}} ከ5

የእኛ ተስፋ መቁረጥ

ትናንትና በእስር ስለነበረው መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስ እያስተማረ ስላለውና እያደረገ ስላለው ስለ ብዙ ነገሮች ሰምቶ ወደ ኢየሱስ መልዕክት በመላክ “የምትመጣው አንተ ነህ ወይስ ሌላ እንጠብቅ ” ብሎ ስላለው ክፍል አንብበናል፡፡ ይህንን ስናነብ በጣም ተደንቀናል ምክንያቱም የዮሐንስ የአገልግሎቱ ዋነኛ ትኩረት የኢየሱስ ክርስቶስ መሲህ ሆኖ ወደ ዓለም ስለመምጣቱ ነውና ነው፡፡

ትንሽ በዮሐንስ ላይ ምን እየተከሰተ እንደነበር ለደቂቃ እናስብ፡፡ ዮሐንስ ዘመኑን ሙሉ በእስራኤል ገላጣ ስፍራ በምድረበዳ ይኖር የነበረ ነው፤ የምድረበዳ ሰው ነው፡፡ አሁን ደግሞ የምናየው በአንዲት በማትመች ጠባብና ትንሽዬ ወይኒቤት ውስጥ በንጉስ ሄሮድስ ታስሮ ነው፡፡ እስቲ ለደቂቃ ዮሐንስ በዚያች ጠባብ ወይኒ ቤት የገጠመውን አስከፊ፣ አስጨናቂና ከልክ ያለፈ ፍርሃት አስብ፡፡

የዛሬው ንባባችን የሚያተኩረው መጥምቁ ዮሐንስ በእስር ቤት ጉዞው እንዳበቃ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ንጉስ ሄሮድስ የገዛ ወንድሙ የፊሊጶስን ሚስት ማግባት እንዳልተፈቀደለትና ነውር መሆኑን ዮሐንስ በድፍረት ስለሞገተው ነበር፡፡ዮሃንስ ተስፋ ቆርጧል ምክንያቱም እርሱ ስለ እግዚአብሔር ፅድቅ ስለቆመ እግዚአብሔርም ለእርሱ እንደሚሸፍነውና እንደሚጠብቀው ተስፋ ያደርግ ነበር፡፡

ይህ ልክ እንደ አንተና እንደ እኔ ከእግዚአብሔር ከምንጠብቀው ነገር የተገላቢጦሽ ሲሆንብን በተለይም በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ እንደሆንን እያወቅን፣ እግዚአብሔር እንድናደርግ የሚፈልገውን እያደረግን፣ ወይም ትክክል የሆነውን ነገር እያደረግን እንዳለ እያወቅን፣ ወይም ደግሞ ስለእግዚአብሔር እውነትና ፍትህ ቆመን ሳለ በዚህ ሁሉ ግን አስቸጋሪ ነገሮች፣ ተቃውሞዎች፣ ተስፋ መቁረጦች እና ተግዳሮቶች ሲገጥሙን እናያለን፡፡

መጥምቁ ዮሐንስ በትንሽዬ ወይኒ ቤት ውስጥ ተስፋ እንደቆረጠው እኛም ተስፋ እንቆርጣለን፡፡ እየሆነብን ካለው የተገላቢጦሽ ነገር ይልቅ ነገሮች ቀላል እንዲሆኑልን እንጠብቃለን፤ ወይም ደግሞ እንደ ክርስቲያን እግዚአብሔር ነገሮችን ጎርባጣና አስቸጋሪ እንዲሆኑብን ባይፈቅድ እንላለን፡፡

እየሆነብን ያለነውን የእኛንም የተስፋ መቁረጥ የሚያንፀባርቅ ነው ብለን መደምደም እንችላለን፡፡ ነገር ግን አስደናቂው የወንጌል ዜና የሚነግረን በህመም ውስጥ መቼም ትቶን እንደማይሄድ ነው፡፡ መቼም ተስፋ አትቁረጥ!

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 1ቀን 3

ስለዚህ እቅድ

ጥርጣሬዎቻችንና ተስፋ መቁረጦች

ይህ የአምስት ቀን የንባብ ዕቅድ በኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ በኩል የተገለጠውን በጥርጣሬዎቻችንና በተስፋ መቁረጦች ግዜያት ሁሉ የእግዚአብሔርን ታማኝነት እውነት እያሳየን ያበረታናል፡፡

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Returning to the Gospel - East Africa ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://returningtothegospel.com/