የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሐዲስ ኪዳን በ 90 ቀናትናሙና

The New Testament in 90 Days

ቀን {{ቀን}} ከ90

የሶስተኛው የዮሐንስ መልእክት መግቢያ

የዚህ መልእክት ጸሐፊ ልክ እንደ ሁለተኛ ዮሐንስ ራሱን “ሽማግሌው” ሲል ጠርቷል። እንደ ታሪክ ምሁራን ከሆነ ደግሞ ዮሐንስ በወቅቱ በእድሜው መጨረሻ አካባቢ የነበረ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም በሕይወት ከነበሩት የመጨረሻዎቹ ደቀ መዝሙርት ውስጥም ይገኝ ነበር። ምናልባትም ይህን መጽሐፍ በ 90 ዓ.ም አካባቢ ከፍጥሞ ደሴት ሆኖ እንደጻፈው ይታመናል። 

ዮሐንስ ይህንን መልእክት የጻፈው በሚያውቀው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ታዋቂ ለነበረው ለጋይዮስ ነው። ዮሐንስ ፤ ጋይዮስ ያጋጠሙትን ችግሮች እንዲፈታ እየረዳው ነበር፤ ከእነዚህም መካከል ዲዮጥራፊስ የተባለውን ቤተ ክርስቲያን ለመቆጣጠር የመጣውን አልፎ ተርፎም ተጓዥ ሚስዮናውያንን የከለከለውን ሰው እንዴት መያዝ እንዳለበት ጭምር ነው። ዲዮጥራፊስ ከዮሐንስ ተግሣጽ አግኝቶ የነበረ ቢሆንም ወደ ተግባር ግን ሳይለውጠው ቀርቷል። 

የይሁዳ መልእክት መግቢያ

የዚህ መጽሐፍ ደራሲ የያዕቆብ ወንድም የሆነው ይሁዳ ነው። ይህም ለኢየሱስ በአንድ ወገን ወንድሙ ያደርገዋል። እንደ ወንድሙ ያዕቆብ፣ ይሁዳም በኢየሱስ ያመነው ከትንሣኤው በኋላ ነበር። ይሁዳ ይህን መጽሐፍ መቼ እንደጻፈ ምንም አይነት ማረጋገጫ ባይገኝም ምሁራን ግን ከ 67-80 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ሊጻፍ እንደሚችል ያምናሉ። 

የይሁዳ ደብዳቤ አጭር እና ግልጽ ነበር። በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን የነበረችው ቤተ ክርስቲያን በመናፍቃን እና በሐሰት ትምህርት ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ወድቃ የነበረችበት ግዜ ነበር፣ ስለዚህ የይሁዳ መልእክት ቤተ ክርስቲያን በእምነታቸው ንቁ በመሆን እራሳቸውን ከመናፍቃን ትምህርት እንዲጠብቁ ለማሳሰብ ነበር። 

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 79ቀን 81

ስለዚህ እቅድ

The New Testament in 90 Days

በቀጣዩ 90 ቀናት ውስጥ የሐዲስ ኪዳንን 260 ምዕራፎች ከ ማቴዎስ ወንጌል በመጀመር የማርቆስ ወንጌልን ፣ የሉቃስ ወንጌልን ፣ የዮሐንስ ወንጌልን በማንበብ እስከ መጨረሻው መጽሐፍ የዮሐንስ ራእይ ድረስ ይዘልቃል።Journey through the 260 chapters of the New Testament over the next 90 days. From the gospels of Matthew, Mark, Luke, and John, all the way to the final book of Revelation, God will speak to you throughout the teachings of those who were transformed by our Savior.

More

ይህ ዋናው የመጽሐፍ ቅዱስ እቅድ የተዘጋጀው እና የቀረበው በ YouVersion ነው።